በዘንድሮው ክረምት በተሰራ የበጎ አድራጎት ስራዎች ከ26 ሺህ 2መቶ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉ ተገለጸ።

የጉራጌ ዞን የክረምት ወራት የበጎ አድራጎት የቴክኒክና የአብይ ኮሚቴው እስካሁን የተሰሩ ስራዎችን ገምግሟል።

የጉራጌ ዞን ረዳት የመንግስት ተጠሪ አቶ አለማየሁ ገ/መስቀል እንደተናገሩት የክረምት የበጎ ፈቃድ ስራዎች ውጤታማ ለማድረግ በየመዋቅሩ ያሉ አካላት ስራውን በባለቤትነትና በተፎካካሪ መንፈስ ይዘው መሰራት አለባቸው ብለዋል።

በቀጣይ የተቸገሩ ወገኖችን ለመርዳት አካውንት ተከፍቶ ሀብት የማሰባሰብ ስራ ይሰራል ያሉት አቶ አለማየሁ አብዛኛው ማህበረሰብ በበጎ ስራው አሳታፊ ማድረግ እንደሚያስፈልግም ገልፀዋል።

እንደ አለማየሁ ገለጻ ሁሉም ህብረተሰብ የዚህ ተግባር ባለቤት ቢሆኑም የእምነት ተቋማት፣ ተራዶ ድርጅቶችና ባንክ ቤቶች እንዲካተቱ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ተናግሯል።

የጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ አብዶ ድንቁ ለአረጋውያን ቤት ለመስራት በሁሉም ቀበሌ እና ክፍለ ከተማ በእቅድ በተያዘው መሰረት እስካሁን ድረስ 6 ቤት ተሰርቷል።
3 የመንገድ ድልድይ መገንባቱ፣ ለተቸገሩ ወገኖች 6 ሄክታር መሬት መታረሱና 3መቶ 48 ዩኒት ደም የማሰባሰብ ስራ ተሰርቷል ያሉት አቶ አብዶ በበዓላት ወቅት 1መቶ 33 ከብቶች፣ 60 በጎች እና ፍየሎች እርድ በመፈፀም ለአቅመ ደካሞች ቅርጫ የማከፋፈል ስራ መሰራቱን ገልፀዋል።
አጠቃላይ ተግባሩ ከተጀመረ ጊዜ ጀምሮ በተሰሩ ስራዎች በመንግስትና በህብረተሰቡ ይወጣ የነበረው ከ3ሚሊየን 2መቶ 66 ሺህ ብር በላይ ማዳን ተችሏል ብለዋል።

የአረፋ በአል ምክንያት በማድረግ ግሎባል ዱቄት ፋብሪካ 45 ሺህ ብርና ቢጂአይ በማስተባበር ለአራት መቶ አቅመ ደካሞች ለእያንዳቸው አራት መቶ ሃምሳ ብር ድጋፍ ከመደረጉ በተጨማሪም ቢጂአይ ሶስት መቶ ቲሸርቶችና 18 ጃንጥላ ድጋፍ መደረጉንም አቶ አብዶ አስታውቀዋል።

በወልቂጤ ከተማ ከወሰን ተሻጋሪ ወጣቶች ጋር በመሆን ከተማ የማፅዳት፤ ችግኝ የመትከልና አረጋውያንን የመንከባከብ ስራ እንደተሰራ ጠቁመው ለሶስት ዙር ችግኝ ተከላ ተካሄዷል።

በክረምት በጎ አድራጎት ስራው የችግኝ ተከላ በዞን መዋቅር እስካሁን 4 ነጥብ 1ሚሊዮን ችግኞች መተከላቸው አመላክተዋል።

የሚሰሩ ስራዎች የሚዲያና የኮሚኒኬሽን ሽፋን በመስጠት፣ የኑሮ ውድነት የማረጋጋትና የሰላም ግንባታ እሴት ስራ በማጠናከር፣ የሚሰሩ የአረጋውያን ቤቶች ዲዛይናቸው ተመሳሳይ በማድረግና የአብይና የቴክኒክ ኮሚቴ ስራው እንዲጠናከርና በሌሎችም ሰፊ ውይይት ተካሂዷል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሙኒኬሽን መምሪያ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *