በጉራጌ ዞን አበሽጌ ወረዳ በህብረተሰብ ተሳትፎ የተሰራ ከ12 ኪሎ ሜትር በላይ የጠጠር መንገድ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።

ዛሬ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት የጀመረው መንገድ ናቻ ቁሊት፣ ሁዳድ 4 እና 5 የገጠር ቀበሌዎች እንደሚያገናኝ ተገለጸ።

የአበሽጌ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መላኩ ብርሃኔ በ2014 በጀት ዓመት ከህብረተሰቡ ተሳትፎ ከ20 ሚሊዮን ብር በላይ ክረምት ከበጋ የሚያገለግሉ 80 ነጥብ 8 ኪሎ ሜትር የተለያዩ የጠጠር መንገዶች ተገንብቶ አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ ብለዋል።

የመንገዱ መገንባት አርሶ አደሩ ያመረተውን የግብርና ምርት በፍጥነት ወደ ገበያ ለማቅረብ፣ እናቶች በወሊድ ጊዜ የአንቡላንስ አገልግሎት በማግኘት በጤና ተቋም እንዲወልዱ እንደሚያስችል ተናግረዋል።

በወረዳው በማህበረሰቡ ተሳትፎ እየተገነቡ ያሉ መንገዶች የአርሶ አደሩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ከማሳለጥ ባለፈ ከጊዜ ወደ ጊዜ ምርታማነቱ እያሳደገ መሆኑ ዋና አስተዳዳሪው ገልፀዋል።

የጉራጌ ዞን የዋና አስተዳዳሪ አማካሪ አቶ የህያ ሱልጣን ህብረተሰቡ ተቀናጅቶ ከሰራ የመንግስትን የልማት ክፍተት መሙላት እንደሚቻል በወረዳው የተገነቡ የተለያዩ የመንገድ ልማት ስራዎች ማሳያ መሆናቸውን ገልጸዋል።

የጉራጌ ዞን የትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ ሀላፊ ወይዘሮ ትብለጥ እስጢፋኖስ መንገድ የመሰረተ ልማቶች ሁሉ መሰረት መሆኑን የወረዳው ህዝብ በተግባር ማሳየት መቻሉን ተናግረዋል።

ማህበረሰቡ መንገዶች ከመገንባት ባለፈ ለረዥም ጊዜ ማገልገል እንዲችል በተገቢ መጠበቅና መንከባከብ እንደሚገባውም ጠቁመዋል።

አቶ ተሻለ ጎቴና ወይዘሮ አማን አበራ በአበሽጌ ወረዳ የቁሊት ሁለት ዋሪና የመንገዱ ግንባታ አስተባባሪ ናቸው። ዛሬ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት የጀመረው መንገድ 3 ሚሊዮን 4 መቶ ሺህ ብር በሆነ ወጪ ከህብረተሰቡ በመሰብሰብ መገንባት መቻሉን አብራርተዋል።

የመንገዱ መገንባት የህብረተሰቡ ሲታመም ቶሎ ሀኪም ቤት ለመሄድ፣ እናቶች በጤና ተቋማት እንዲወልዱ፣አርሶ አደሩ ያመረተውን ምርት የተሻለ ገበያ ወዳለበት ወስዶ እንዲሸጥና ግብዓት ያለምንም እንግልት መንደሩ ድረስ እንዲገባለት የሚያስችል መሆኑን አስተባባሪዎቹ ተናግረዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

በመረጃ ምንጭነት ገፃችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን!
= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *