የሳይንስና የፈጠራ ስራዎችን በሁሉም አካባቢዎች እንዲስፋፉና ለማህበረሰቡ ቀልጣፋና ውጤታማ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ የጉራጌ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ገለጸ።

የሳይንስና የፈጠራ ስራዎችን በሁሉም አካባቢዎች እንዲስፋፉና ለማህበረሰቡ ቀልጣፋና ውጤታማ አገልግሎት የሚሰጡትን በመለየትና በትንሽ ወጪ ተጠግነው የሚጠቅሙ የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂዎችን በመለየት ጥቅም ላይ እንዲውሉ በትኩረት እንደሚሰራ ተገጿል ።

የጉራጌ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ የ2014 ዓ.ም የ3ኛ ሩብ ዓመት እቅድ አፈጻጸምና የዜጎች ቻርተር ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር በወልቂጤ ከተማ ዉይይት አካሄዷል።

የጉራጌ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ኃላፊ አቶ ደምስ ገብሬ እንደገለፁት መምሪያዉ በሳይንስና ቴክኖሎጂዉ ዘርፍ የሚፈለገዉን ዉጤት እንዲመጣና ማህበረሰቡ ተጠቃሚ እንዲሆን በትኩረት እየተሰራ ነዉ።

በዚህ ሩብ ዓመት በዞኑ ትምህርት መምሪያ ሁሉም ወረዳዎችን ያሳተፈ የተማሪዎች የሳይንስና የፈጠራ ስራዎች ኤግዚቢሽን ማዘጋጀት የተቻለ ሲሆን በዞኑ 1ሺህ 2 መቶ የሚሆን የፈጠራ ስራዎች ማቅረብ የተቻለና የተመዘገቡም እንደሆኑም ተናግረዉ በቅርቡ ዞን አቀፍ በተካሄደዉ የፈጠራ ስራዎች ኤግዚብሽን ዉድድር 80 የሚሆኑ የፈጠራ ስራዎች ለዉድድር መቅረባቸዉም አስረድተዋል።

ከውድድሩ በሻገር አዲስ ፈጠራና ኮፒ የሆኑትን በመለየት እንዲሁም እንዲበረታቱ ፣እንዲሰሩና እንዲባዙ በማድረግ ለህብረተሰቡ ቀልጣፋና ወጤታማ አገልግሎት መስጠት የሚችሉ የፈጠራ ቴክኖሎጂዎችን ማደርስ እንደሆነም ገልጸዋል ።

በትንሽ ወጪ ተጠግነው አገልግሎት የሚሰጡ የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መሳሪያዎችን በመለየት ጥግና በማድረግ አግልግሎት እንዲሰጡና ለአዲስ ግዢ የሚወጣዉን ከፍተኛ ወጪ ለማስቀረት በትኩረት እየተሰራ እንደሆነም አስረድተዋል ።

በየደረጃው ያለው መዋቅር በማብቃት ለማህበረሰቡ ጠቃሚ የፈጠራ ስራዎችን እንዲሰሩ የሚመለከታቸው ባለ ድርሻ አካላት ለዘርፉ ትኩረት መስጠት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

አንዳንድ የውይይቱ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት በዞኑ ያሉ ወረዳዎችና ከተሞች ላይ በሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የፈጠራ ስራዎች ላይ ዉጤታማ ስራ በመስራትና የሚፈለገዉን ዉጤት እንዲመጣ ከመቼዉም ጊዜ በላይ ትኩረት አድርገዉ ሊሰሩበት እንደሚገባም አመላክተዋል።

አለም የደረሰበት የሳይንስና ኢኖቬሽን ቴክኖሎጂ ደረጃ ላይ ለመድረስ እየተሰሩ ያሉትን አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ለማህበረሰቡ አገልግሎት እንዲዉሉ ለማድረግ የዘርፉ ባለድርሻ አካላትና የሁሉም ርብርብ እንደሚጠይቅም አስታዉቀዋል።

በውይይቱምየመምሪያው ሀላፊ አቶ ደምስ ገብሬ ጨምሮ የመምሪያው ባለሙያዎች፣ ከዞን መስሪያ ቤት የተዉጣጡ የሚመለከታቸው ባለ ድርሻ አካላት ተገኝተዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

በመረጃ ምንጭነት ገፃችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን!

= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *