ህግ ወጥ የዋጋ ጭማሪ ባደረጉና ያለ ደረሰኝ ሸቀጣሸቀጦች ሲሸጡ በተገኙ ነጋዴዎችና ህገ ወጥ ነዳጅ ቸርቻሪዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ መወሰዱን የጉራጌ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ አስታወቀ።

መምሪያው የ90 ቀናት ዕቅድ ውስጥ የተቀመጡ አቅጣጫዎችና ግቦች ለመተግበርና የተለዩ ችግሮች ለመፍታት ጥረት እያደረገ መሆኑም ጠቁሟል ።

የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ የ90 ቀናት ልዩ እቅድ አተገባበርና ውጤታማነት እንዲሁም እንደ ዞን እየተከሰተ ያለው ሰው ሰራሽ የኑሮ ውድነት ለመከላከልና ከንግድ ስርአቱ ተያይዞ ህዝቡ በየደረጃው የሚያነሳቸው ችግሮች ለመፍታት ምን እየተሰራ ነው ሲል የጉራጌ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ሀላፊ አቶ መሀመድ አማን ጠይቋል።

የመምሪያው ሀላፊ አቶ መሀመድ በበኩላቸው በክልሉ እቅድ መነሻነት የዞኑ ነባራዊ ሁኔታ ታሳቢ በማድረግ የ90 ቀናት እቅድ በማዘጋጃት ከሚመለከታቸው ባለ ድርሻ አካላት ጋር በመወያየትና በመግባባት ህዝቡ ያነሳቸው ቅሬታና ችግሮች ለመፍታት ወደ ስራ መግባቱም ገልፀዋል።

የኑሮ ውድነቱ እንደ ሀገር ብሎም አለማቀፍ በሆነ ሁኔታ አሳሳቢ በሆነበት እንደ ዞን እየተከሰተ ያለው ሰው ሰራሽ የኑሮ ውድነቱ ለመከላከል ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመወያየትና በመግባባት የቀጣይ የመፍትሔ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ የ90 ቀናት እቅድ ታቅዶ ወደ ተግባር መገባቱም ሀላፊው ገልጿል።

እንደ ሀላፊው ገለፃ እንደ ሀገር ከተከሰተው የዋጋ ንረትና የኑሮ ውድነት ባሻገር ሰው ሰራሽ የኑሮ ውድነት እንዳለና ይህ ችግር በጋራ መከላከል እንደሚገባ ከንግዱ ማህበረሰብ ፣ከንግድ ዘርፍ ማህበራት ፣ከማደያ ባለ ንብረቶች ፣ከችርቻሮ ነጋዴዎች ጋር በጉዳዩ አሳሳቢነት ዙሪያ በመወያየት የጋራ መግባባት ላይ ተደርሰዋል።

ከውይይቱ በኅላ የኑሮ ውድነቱ ለማረጋጋት ህገወጥ ደላሎች ለመከላከል በዞኑ ባሉት ከተሞች ቅዳሜ ገበያ ወልቂጤ ከተማ፣ ቡታ ጅራ ከተማ፣ ቡኢ ከተማ፣ እምድብር፣ ጉንችሬ እና በማረቆ ወረዳ ቆሼ ከተማ ላይ በማቋቋም አምራቾች እና ሸማቾችን ደላሎች ሳይገቡ ቀጥታ ማገናኘት መቻሉን ጠቁመዋል ።

እነዚህ ገበያዎች ጥሩ በሚባል ደረጃ በማቀሳቀስ ለከተማ ነዋሪዎች የተለያዩ ምርቶች በማቅረብ ላይ መሆናቸው ገልፀው፤ በሂደት ግን በተለይ የወልቂጤ የቅዳሜ ገበያ ምርት በተፈለገው መጠን ለማቅረብ ተግዳሮቶች እንዳጋጠሙና ችግሮቹ ለመፍታት በቀጣይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እንደሚሰራም ተናግረዋል ።

አክለውም አቶ መሀመድ አማን አሁን ላይ እንደ ሀገር ባለው ነባራዊ ሁኔታ የነዳጅ ምርቶች ዋጋ መጨመሩን ተከትሎ እንዲሁም ቀደም ሲልም አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪ እንዳይደረግ ራሱን የቻለ ግብረ ሀይል በማደራጀት ጥረቶች እየተደረገ ይገኛል ብለዋል።

በመሆኑም በቀጣይም አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪ እንዳይደረግ ግብረ ሀይሉ በትኩረት ይሰራል ብለዋል።

አቶ መሀመድ አክለውም በሌላ መልኩ አለአግባብ የዋጋ ጭማሪ ያደረጉ ስጋ ቤቶችና ነዳጅ ቸርቻሪ ነጋዴዎች ከማስተማር ባለፈ ህጋዊ እርምጃ መውሰድ መጀመሩ እና ህጋዊ እርምጃ ከተወሰደባቸው መካከል ጉመር ወርዳ 11 ስጋ ቤቶች፣ቸሀ ወረዳ 2 ስጋ ቤቶች ና 4 ሸቀጥ ሸቀጥ መደብሮች ያለ ደረሰኝ ሲሸጡ፣ጉንችሬ ከተማ 6 እና ደቡብ ሶዶ ወርዳ 2 ነዳጅ ቸርቻሪ ነጋዴዎች ላይ በማሸግ በነበረው ወጋ እንዲሸጡና አስተዳደራዊ እርምጃ መወሰዱም ገልጿል።

በተመሳሳይ በደቡብ ሶዶ ወረዳ ከመንግስት የቀረበ ፍጆታ ዘይት ደብቆ ሲያጭበረብር በኦዲት ወጥቶ የተደበቀ ዘይት በመገኘቱ ዘይቱ ሙሉ ለሙሉ ተወርሶ ኪሳራው እራሱ እንዲሸፍን ቅጣት በመወሰን አከፋፋዩ ከትስስር እንዲወጣ ተደርገዋል።

በቀጣይም ሌሎችም ህገ ወጥ የንግድ እንቅስቃሴ በሚያደርጉ፣አላግባብ ዋጋ በሚጨምሩና መሸጥ የተከለከሉ የተለያዩ ምርቶችን በሚሸጡ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ እየተወሰደ ይገኛል ብለዋል ሀላፊው በሁሉም አከባቢዎች ላይ ከጸጥታ መዋቅር ጋር በመሆን ህጋዊ እርምጃ የመውሰዱ ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ገልፀዋል ።

ነዳጅ ማደያዎች አካባቢ የተከሰተው የቤንዚን እጥረት ችግር ለመቅረፍ ማታ 1:30 እንደሚታሸጉና ጠዋት 12:30 እንደሚከፈቱ እየተሰራ መሆኑንና ሂደቱም ውጤቶች የተገኙበት በመሆኑ በቀጣይ ይህ አሰራር ትኩረት ተሰጥቶ እንዲተገበር ይሰራል ብለዋል።

ከዘጠና ቀን እቅድ ውስጥ በዚህ አንድ ወር ውስጥ የተለያዩ ተግባራት የተከናወኑ ቢሆንም አሁንም ህብረተሰቡ ከኑሮ ውድነቱ ተያይዞ ሰፊ ቅሬታዎች እየተነሳ መሆኑ ገልፀው ችግሩ በአንድ በኩል አለም አቀፋዊና ሀገራዊ መሆኑ በመገንዘብ በሌላ መልኩ አላግባብና ሰው ሰራሽ የኑሮ ውድነት የሚፈጥሩ አካላት በመታገልና ለማረም በሚሰሩ ስራዎች እገዛ እንዲያደርግ ጠይቀዋል።

አሁን ሀገራችን ላይ ብሎም እንደዞን እየተስተዋለ ያለው የኑሮ ውድነት ዜጎች በከፍተኛ ሁኔታ እየጎዳ ባለበት ሁኔታ ላይ ፍፁም ሰብአዊነት በጎደለውና ህግ በጣሰ ሁኔታ ሰው ሰራሽ ውድነት እየፈጠሩ የሚገኙ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አሳስበዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

በመረጃ ምንጭነት ገፃችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን!

= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *