በስፖርቱ ዘርፍ የሚፈለገዉን ዉጤት እንዲመጣና ተተኪ ስፖርተኞች ለማፍራት የስፖርት ባለሙያተኞችና አሰልጣኞች ሚና የጎላ መሆኑም የጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ አስታወቀ።

የጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ከወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ለተከታታይ 15 ቀናት ለስፖርት ባለሙያተኞችና ለስፖርት ሳይንስ ተማሪዎች ሲሰጥ የነበረዉ የአንደኛ ደረጃ የአሰልጣኞች ስልጠና በዛሬዉ ዕለት ተጠናቀቀ።

ሰልጣኞች በቆይታቸዉ ያገኙትን እዉቀትና ልምድ ወደ ተግባር በመለወጥ በስፖርቱ ዘርፍ ተጨባጭ ዉጤት ማምጣት እንዳለባቸዉም ተመላክቷል።።

በስልጠናዉ ማጠናቀቂያ ላይ የተገኙት የጉራጌ ዞን ወጣቶችና እስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ አወል ጅማቶ እንደገለጹት መምሪያዉ ከወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በሶስት የስፖርት አይነቶች በአትሌቲክስ ፣ በቅርጫት ኳስና በቮሊቦል የስፖርት አይነቶች የአንደኛ ደረጃ የአሰልጣኞች ስልጠና ለሁለት ሳምንት ሲሰጥ እንደነበረና በዘርፉም የሚስተዋለውን የአቅም ውስንነት ለመቅረፍ ታስቦ የተዘጋጀ እንደሆነም ተናግረዋል።

ስልጠናውን የተከታተሉ ባለሙያተኞች የቀሰሙትን እውቀት በየአካባቢያቸው በዘርፉ የሚስተዋለዉን ዉስንነት በመቅረፍና ተተኪ ወጣቶች ለማፍራት ጠንክረው መስራት እንዳለባቸዉም አሳስበዋል።

አቶ አወል ጅማቶ አክለውም በእውቀት የዳበረ ታዳጊ ስፖርተኞችን ታች ድረስ ወረዶ በማሰልጠንና በማብቃት በሀገር እና በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ወጣቶች ለማፍራት ከመቼዉም ጊዜ በላይ ትኩርት ሰጥተዉ መስራት እንዳለባቸዉም ገልፀዋል።

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር ሀብቴ ዱላ በስልጠናው መዝጊያ ወቅት እንዳሉት በስፖርት የዳበረ ፣በስነ ምግባር የታነጸ ታዳጊ ወጣት ለማፍራት ሁሉም የበኩሉን ድርሻ መወጣት ይኖርበታል ብለዋል።

ስፖርት ለራስ ጤንነትና የገቢ ምንጭ መሆኑን ጠቀሰው ከዚያ ባሸገር ሀገራን ለማስተዋወቅና ለማስጠራት ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚኖርው ዶክተር ሀብቴ ዱላ አብራርተዉ በዘርፉም የሚፈለገዉ ዉጤት እንዲመጣ ቅንጅታዊ ስራዉ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም አመላክተዋል ።

የዩኒቨርሲቲዉ የስፖርት ትምህርት ክፍል ኃላፊ ዶከተር አብዱላዚዝ ሙሰማ በበኩላቸዉ የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ከጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ጋር በቅንጅት በመሆን በስፖርቱ ዘርፍ ለማጠናከር ወደፊት ትኩረት ሰጥተው እንደሚሰሩና በአሁኑ የአንደኛ ደረጃ የአሰልጣኞች ስልጠና 87 የሚሆኑ ሰልጣኞች መሳተፋቸውም ጠቁመዋል ።

አክለውም በቀጣይ ጊዜያት ዩኒቨርሲቲው ከተለያዩ መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር በመነጋገር በስፖርቱ ዘርፍ ያለውን ሳይንሳዊ ስልጠና እና የስፖርት ማዕከል ለመግንባት ትኩረት የሚሰጠው ጉዳይ እንደሆነም ጠቁመዋል።

ያነጋገርናቸው ሰልጣኞች እንደተናገሩት በቆይታቸዉ በተግባርና በንድፈ ሀሳብ ያገኟቸውን እውቀቶች ወደ ተግባር ለመለወጥ እንደሚሰሩበትም አመላክተዉ ስልጠናዉም የነበረባቸውን የአቅም ውስንነት እንደቀረፈላቸዉና በአካባቢያቸዉ ተተኪ ወጣቶች ለማፍራት ተግተው እንደሚሰሩ ገልፀዋል።

በማጠቃለያ ፕሮግራሙ ለአሰልጣኞች እና ስልጠናቸውን በአግባቡ ለተከታተሉ ሰልጣኞች የእውቅና ምስክር ወርቅት ተበርክቶላቸዋል ።

በፕሮግራሙ የኢትዮጵያ የቅርጫት ኳስ ፌድሬሽን ተወካይ ፣የአትሌቲክስና የቮሊቦል የክልል የፌድሬሽን ተወካዮች ፣የዞኑ የስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች እንዲሁም የዩኒቨርሲቲው የስራ ኃላፊዎችና ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

በመረጃ ምንጭነት ገፃችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን!

= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *