የጤና ተቋማት አገልግሎት አሰጣጥ ጥራት ለማሻሻል ህብረተሰቡ የላቀ ሚና መጫወት እንዳለበት የጉራጌ ዞን ጤና መምሪያ አሳሰበ።የመምሪያው የ11 ወራት እቅድ አፈጻጸም የምክክር መድረክ በወልቂጤ ከተማ መካሄዱን ተመልክቷል።የመምሪያው ኃላፊ አቶ ፋሲካ አለሙ ባለፉት 11 ወራት ህብረተሰቡ ቀልጣፋና ጥራት ያለው አገልግሎት ለመስጠት በተሰራው ስራ አበረታች ውጤት ማስመዝገብ ተችሏል።በዞኑ የቅድመ ወሊድ ክትትል የሚያደርጉ እናቶች ቁጥር እያደገ መሆኑን የተናገሩት አቶ ፋሲካ እርግዝናቸው ካረጋገጡ እናቶች መካከል 80 በመቶ የሚሆኑት በጤና ተቋም የቅድመ ወሊድ ክትትል ያደረጉ ሲሆን በሰለጠነ የጤና ባለሙያ የወሊድ አገልግሎት ያገኙ እናቶች ቁጥር ደግሞ ከ76 በመቶ በላይ እንደሆነ አስረድተዋል።አምራች፣ ጤናው የተጠበቀ እና ብቁ ዜጋ ለማፍራት ጥራቱን የጠበቀ ክትባት ለዜጎች ተደራሽ ማድረግ ይገባል ያሉት አቶ ፋሲካ ባለፉትት 11 ወራት የቢጫ ወባ፣ የፖሊዮ፣ የኩፍኝ ወረርሽኝና ሌሎች ተላላፊ በሽታዎች አስቀድሞ ለመከላከል የክትባት አገልግሎት መስጠት እንደተቻለም አስረድተዋል። በመሆኑም የዞኑ የክትባት ሽፋን 98 በመቶ ሲሆን ጥራቱን ለማሻሻል በትኩረት ይሰራል ብለዋል አቶ ፋሲካ ።የጤና ተቋማት ለህብረተሰቡ ቀልጣፋና ጥራት ያለው አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ ህብረተሰቡ በተቋማቱ አፈጻጸም ላይ አስተያየት ከመስጠት ጀምሮ ክፍተቶቹን ለመሙላት ህብረተሰቡ ድጋፍ በማድረግ የድርሻውን ሚና ሊወጣ ይገባል ብለዋል።አያይዘውም ኃላፊው በጤና ተቋማት የሚስተዋሉ የመረጃ ጥራት መጓደል፣ የቲቢ ህሙማን ልየታ አናሳ መሆኑ፣ የጤና ተቋማት አገልግሎት አሰጣጥ ጥራት ማሻሻል ትኩረት የሚሹ ተግባራት በመሆናቸው በቀጣይ የተቋማቱ የቦርድ አባላትና ባለድርሻ አካላት ትኩረት ሰጥተው መስራት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።የኮቪድ19 በሽታ የሚያሳድረው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጫና ለመቀነስና ስርጭቱን ለመከላከል የጤና ባለሙያዎችና የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች ላበረከቱት አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበው በቀጣይ ህብረተሰቡ ተገቢውን ጥንቃቄ በማድረግ ስርጭቱን ለመከላከል የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።አቶ መሀመድ አሚን ጀማል የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ጤና ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሲሆኑ የህብረተሰቡ ጤና ለማሻሻል የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራሞች ከፍተኛ ፋይዳ ያላቸው በመሆኑ ባለሞያዎቹ በሁሉም ቀበሌዎች ተደራሽ እንዲሆኑ መስራት ይገባል ብለዋል።በወረዳው የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች እጥረት በመኖሩ የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራሞች ማሳካት እንዳልተቻለ የተናገሩት አቶ መሀመድ አሚን ፓኬጆቹ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ባለመደረጋቸው በህብረተሰቡ ጤና መጎልበት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ አሳድረዋል ብለዋል። በመሆኑም በቀጣይ የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች በተለያዩ የዞኑ ወረዳዎች ተዟዙረው የሚሰሩበት ስርዓት እንዲዘረጋ ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል።የእነሞርና ኤነር ወረዳ ጤና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ እርስቱ ደምስስ በበኩላቸው በበጀት አመቱ እናቶችና ህጻናት ሞት ከመቀነስ በተጨማሪ ነፍሰጡር እናቶች በሰለጠነ የጤና ባለሙያ የወሊድ አገልግሎት እንዲያገኙ እየተሰራ ነው ብለዋል።እንደ አቶ እርስቱ ገለጻ በወረዳው ሞዴል ቀበሌ ለመፍጠር እንዲሁም የጤና ባለሙያዎች ለህብረተሰቡ የሚሰጡት የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራት ለማሻሻል በትኩረት ይሰራል ብለዋል።አክለውም አስተያየት ሰጪዎቹ በምክክር መድረኩ የቀረቡ ጠንካራ አፈጻጸም ለማስቀጠል እና ክፍተቶቻቸው በማረም ለየህብረተቡ ጤና ለማጎልበት እንሰራለን ብለዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።
- Our Visitor
- Today's visitors: 11
- Today's page views: : 12
- Total visitors : 5,420
- Total page views: 6,745
-
Recent Posts
- በጉራጌ ዞን አበሽጌ ወረዳ በተያዘው የክረምት ወራት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ከ21 ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ ለማድረግ እንደሚሰራ የወረዳው አስተዳደር አስታወቀ።
- ከፌደራል፣ ከክልልና ከከተማ አስተዳደር የተወጣጡ የወጣቶች ሊግ ጽህፈት ቤት ኃላፊዎችና ስራ አስፈጻሚዎች የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት ንቅናቄና የብልፅግና ትሩፋት ለወጣቶች ተጠቃሚነት በሚል በጉራጌ ዞን ከእምድብር ከተማ አስተዳደርና ከቸሃ ወረዳ ወጣቶች ጋር የልምድ ልውውጥ ተካሄደ።
- የትምህርት መሰረተ ልማትና ግብአት ማሟላት በሀገር አቀፍ ደረጃ ብቁና ተወዳዳሪ ዜጋ ለማፍራት ሚናው የላቀ መሆኑን የኢፌድሪ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ዴኤታ ክቡር አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ገለጹ።
- (no title)
- ሐምሌ 14/2016 ዓመተ ምህረት ታላቁ የጎዳና ላይ የ15 ኪሎ ሜትር ሩጫ በወልቂጤ ከተማ እንደሚካሄድም ታዉቋል ።
Archives
- July 2024
- June 2024
- May 2024
- April 2024
- March 2024
- February 2024
- January 2024
- July 2023
- June 2023
- May 2023
- April 2023
- March 2023
- January 2023
- November 2022
- October 2022
- September 2022
- August 2022
- July 2022
- May 2022
- April 2022
- March 2022
- February 2022
- January 2022
- December 2021
- November 2021
- October 2021
- September 2021
- July 2021
Categories