በጉራጌ ዞን ከዘቢዳር አትሌቲክስ ክለብ በሀገርና በአለም አቀፍ ደረጃ ሊሳተፊ የሚችሉ ብቁና ተወዳዳሪ አትሌቶቾን ለማፍራት እየተሰራ እንደሆነ የጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ አስታወቀ።

የጉራጌ ዞን አስተዳደር፣ የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ እና የዞኑ ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ በጋራ በመሆን 5መቶ ሺ ብር ግምት ያለው የስፖርት ትጥቅና ቁሳቁሶች ሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በዛሬው እለት በአረቅጥ ከተማ ለአትሌቶቹ አስረክቧል።

የጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ አወል ጁሟቶ በዚህ ወቅት እንዳሉት ክለቡ ለሀገራችን በርካታ አትሌቶች ማፍራቱ አስታውሰው ከዚህ በፊት የነበረቡት በርካታ ችግሮች ተለይተው መሰል ድጋፎች በመደረጋቸው ለውጦች እየታዩ ነው ብለዋል።

የዘቢዳር አትሌቲክስ ክለብ በሀገርና በአለም አቀፍ ደረጃ ብቁና ተወዳዳሪ አትሌቶቾን ለማፍራት ከዞኑ አስተዳደር፣ከወልቂጤ ዩኒቨርስቲ፣ ከባለሀብቶች፣በውጭና በሀገር ውስጥ ያሉ የአካባቢው ተወላጆች እና ከሌሎችም ጋር በመቀናጀት በትኩረት እየተሰራበት እንደሆነ አቶ አወል ተናግሯል።

ይህንን ታሳቢ በማድረግ በዛሬው እለት 5መቶ ሺ ብር የሚገመት የተለያዩ የስፖርት ቁሳቁሶች ድጋፍ መሰጠቱ ገልጸው ቀጣይም አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ እንደሚደረግ አሳውቋል።
የጉራጌ ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሰፋ አካሉ እንደተናገሩት ክለቡ በሀገር የሚታወቅበት ዝነኛ ስሙን አስጠብቆ ለማስቀጠልና አትሌቶቹ ወደተሻለ ደረጃ እንዲደርሱ የዞኑ አስተዳደር በትኩረት ይሰራል ነው ያሉት።

የአትሌቲክሱ ዘርፍ የበለጠ ውጤታማ ለማድረግ የግል ጥረት ይጠይቃል ያሉት አቶ አሰፉ በየ ጊዜው የሚደረጉ ውድድሮችን በድል ለመወጣት በሀገራዊ ፍቅርና ስሜት መስራት እንደሚጠበቅባቸው ለአትሌቶቹ መክረዋል።

የወልቂጤ ዩኒቨርስቲ የምርምርና የማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ዩሀንስ ገብሩ ዩኒቨርስቲው ከዚህ በፊት ለስፖርቱ ዘርፍ የተለያዩ ድጋፎች እንዳደረገ አስታውሰው ቀጣይም ክለቡ ለማገዝ ፖሮፖዛሎችን ቀርጾ እየተንቀሳቀሰ እንደሆነ ነው አስታውቀዋል።

የጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ምክትልና የስፖርት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አደም ሽኩር እንደገለፁት ዞኑ ለአትሌቲክስ ስራ ምቹ መሆኑ በዚህ ክለብ ወጥተው በሀገር ደረጃ የሚወዳደሩ አትሌቶች ማሳያ ናቸው ብለዋል።

ከዚህ በፊት የነበሩ የአደረጃጀትና የአሰራር ችግሮች ለመቅረፍ ስራ ተሰርቷል ያሉት አቶ አደም ቀጣይ በሀገር ደረጃ የተሻሉ አሰልጣኞች የመቅጠር፣የምግብ አቅርቦት ችግር በመቅረፍ፣ የስፖርት ቁሳቁስ፣የመሮጫ ትራክ የማደርያ ቦታ እና ሌሎችም እንዲስተካከሉ ይደረጋል ሲሉ ገልጸዋል።

ተተኪ አትሌቶችን ለማፍራት በተደረገው እንቅስቃሴ ከዚህ በፊት 18 አትሌቶች የነበሩ ሲሆን አሁን ግን 29 ማድረስ ተችሏል።

አቶ አደም አክለውም አትሌቲክስ ክለቡ የዞኑ ባህልና እሴት የሚያስተዋውቅ በመሆኑ ሁሉም ባለድርሻ አካል ዘርፋ እንዲደግፍ አሳስበዋል።

የጉራጌ ዞን አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሰብሳቢ አቶ ሞሳ አብራር የዘቢዳር አትሌቲክስ ክለብ ኢትዩጵያ ውስጥ ካሉ አትሌቲክስ ክለቦች ውስጥ አንዱ እንዲሆን እየሰሩ መሆኑ ተናግሯል።

በተጨማሪም ለአትሌቲክስ ክለቡ ምቹ የሆኑ ማሰልጠኛ ቦታዎች እንዲኖር፣ለአትሌቶቹ የተሻለ ነገር ለመፍጠር እንዲሁም ማግኘት ያለባቸው መሰረታዊ ጉዳዮች እንዲያገኙ ጥረት ይደረጋል ብለዋል።

አትሌት ዘበሩ በርታ፣አትሌት መለሰ ገብሬ አትሌት ሰላም አበበ የክለቡ አትሌቶች ሲሆኑ በተደረገላቸው ድጋፍ መደሰታቸው ገልጸዋል።

ቀጣይ ግን በክለቡ የበለጠ ውጤት እንዲመጣ ልምድ ያለው አሰልጣኝ እንዲመደብላቸው፣የመዝናኛ ቦታ እንዲሰራ፣ምቹ ትራክ እንዲሰራ፣በቂ የሆነ ማደሪያ ቤት እንዲኖር፣የስፖርት ቁሳቁሶችና ሌሎችም እንዲሟላላቸው ጠይቋል ሲል የዘገበውየጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው ።
= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *