በበጋ የመስኖ ስንዴና በተቀናጀ የተፋሰስ ልማት የተገኙ ውጤቶች የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክቱ የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ርስቱ ይርዳው ገለፁ።

በጉራጌ ዞን ጉመር ወረዳ የበጋ መስኖ ስንዴና የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ያለበት ደረጃ በደቡብ ክልል ርእሰ መስተዳድር በክቡር አቶ ርስቱ ይርዳው የተመራ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ በክልሉ ከሚገኙ ዞናኖችና ልዩ ወረዳ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም በጉራጌ ዞን እና የወረዳ ከፍተኛ አመራሮች ተጎበኘ።

የደቡብ ክልል ርእሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ርስቱ ይርዳው በጉብኝቱ ወቅት እንደገለፁት አካባቢያችንን እና መሬታችንን እያለማን የውሀ ሀብታችንን መንከባከብ ተገቢ በመሆኑ በተግባር የሰራነው ስራ አሁን ላይ ውጤቱን ለማየት በቅተናል።

ወረዳው ከዚህ በፊት በተለያዩ ቅመማ ቅመምና የጓሮ አትክልት ምርታማ እንደነበር የገለጹት ርእሰ መስተዳድሩ መሬቱ ተዳፋታማ በመሆኑ አፈሩ በመሸርሸሩ ምርታማነቱን እንደቀነሰው ገልጸዋል።

ይሁን እንጂ ባለፉት አመታት በተከናወነው የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራዎች መሬቶቹ እያገገሙ በመሆናቸው በበጋ መስኖ ስኔዴና በሌሎችም ዘርፎች የታየው ውጤት አበረታች እንደሆነ ገልጸዋል።

እንደ አቶ ርስቱ ገለፃ በአፈርና ውሀ ጥበቃ ስራ በለሙ አካባቢዎች የገብስና የእንስሳት መኖ ለማምረት የታቀደ ሲሆን የውሀ እጥረትና የመሬት መሸርሸር ያለባቸው አካባቢዎች ጠረጴዛማ እርከን በመስራት ውሀ እንዲረጋጋና በተመሳሳይ የእድገት ደረጃ ተመሳሳይ ምርት እንዲሰጥ ይሰራል ብለዋል።

የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሀመድ ጀማል በበኩላቸው የአርሶ አደሩን ጥያቄ ደረጃ በደረጃ በመመለስ ከልማት እንዳይነጠል በማድረግ ወደፊት የላቀ ውጤት ላይ እንደርሳለን ሲሉ ገልፀዋል።

በዞኑ በበጋ ስንዴ መስኖ ልማት 1 ሺህ ሁለት መቶ 5 ሔክታር መሬት ማልማት እንደተቻለ የተናገሩት አቶ መሀመድ ለዚህ ውጤት መሳካት በቁርጠኝነት ሲሰሩ የነበሩ አመራሮችባለሙያዎች እና አርሶ አደሮችን አመስግነዋል።

የጉራጌ ዞን ምክትል አስተዳዳና የግብርና መምሪያ ሀላፊ አቶ አበራ ወንድሙ እንደገለፁት የተፋሰስ ልማት ስራ በግብርና ስራችን ተጨባጭ ውጤት ከማስመዝገብ በተጨማሪ ምቹ አካባቢያዊ ስነ ምህዳር እንዲኖር አስችሏል።

በጉመር ወረዳ አበሱጃ ቀበሌ ምርት አይሰጥም በሚል ታርሶ የማይታወቅ መሬት አሁን ላይ ከ120 ሄክታር በላይ መሬት በኩታገጠም በበጋ መስኖ ስንዴ ተዘርቶ ከፍተኛ ምርት እየተጠበቀ እንደሚገኝ አቶ አበራ ገልፀዋል።

ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ እና የአፈር ለምነት ለመጠበቅ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ስራዎች ማጠናከር ይገባል ያሉት አቶ አበራ ይህ ኩታገጠም የበጋ መስኖ ስንዴ እና የተሰሩ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ስራዎቾ ተሞክሮው በሁሉም ወረዳና ቀበሌዎች ለማስፋት በትኩረት እየተሰራ መሆኑም ተናግረዋል።

በስፍራው ያነጋገርናቸው አርሶ አደሮች እንደገለፁት ከዚህ በፊት በከብቶች ይረገጥ የነበረው መሬት በተቀናጀ የተፋሰስ ልማት መጠበቅ በመቻላቸው እንዳስደሰታቸው ገልፀው በቀጣይም አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል።

በአበሱጃ ቀበሌ በበጋ መስኖ ስንዴ ማልማት ላይ የተሰማሩ አርሶ አደርች እንደገለፁት በቀጣይ እርሻቸው ለማስፋትና ምርታቸውን በተገቢ ለመሰብሰብ የትራክተር እና የመውቂያ ማሽን በተለያዩ አማራጮች እንዲቀርብላቸውና የአካባቢው የተለያዩ የመሰረተ ልማቶች መንግስት እንዲያሟላላቸው ጠይቀዋል።

በመጨረሻም ርዕሰ መስተዳድሩ በወረዳው የግል ባለሀብት የአቶ ሀሺም ጀማል እተሰራ ያለው የተቀናጀ የግብርና ልማትና የደጋ ፖም ልማት ስራ ጎብኝተዋል ሲል የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ዘግቧል።

በመረጃ ምንጭነት ገጻችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን!!

= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:-
https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *