በእዉቀት የዳበረና የተሻለ አንባቢ ትዉልድ ለመፍጠር በወጣት ማዕከላት ደረጃቸው የጠበቁ ቤተመፅሀፍቶች ማደራጀት እንደሚገባ የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ አስታወቀ።

ዩኒቨርሲቲዉ ከ4 መቶ ሺህ ብር በላይ ወጪ በማድረግ በዞኑ ለሚገኙ ለወጣት ማዕከላትና ለተማሪዎች የሚዉሉ ከ3 መቶ በላይ የተለያዩ ወቅታዊና አጋዥ መጽሀፍቶች ለዞኑ ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ አስረክቧል።

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ ክፍሌ ለንቲሮ የመጽሀፍት ድጋፍ ባደረጉበት ወቅት እንዳሉት በወጣቶች ዙሪያ ዩኒቨርሲቲዉ የተለያዩ ስራዎች እየሰራ ሲሆን በዚህም የወጣቶች ስብዕና ግንባታ፣የጤና አጠባበቅ ላይ ከዞኑ ሴቶችና ህጻናት መምሪያ ጋር በመተባበር ልዩ ልዩ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች መስጠት ተችሏል።

የወጣቱን ስብዕና መቅረጽ የሚችሉ የተለያዩ መጽሐፍቶች የማሰራጨት ስራ መሰራቱም አስታዉሰዉ አሁን ላይ ከጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ጋር በመሆን ለወጣቶች ማዕከላት የሚሆን ከ4 መቶ ሺህ ብር በላይ ወጪ በማድረግ ከ3 መቶ በላይ መጽሀፍቶች ለወጣቶች ድጋፍ ማድረጋቸዉም አስረድተዋል።

ተማሪዎች ቅዳሜና እሁድን አለባሌ ቦታ እንዳይሉ ወጣት አደረጃጀት ዉስጥ የማንበብ እድል እንዲፈጠርላቸዉ የተሻለ አንባቢ ትዉልድ ለመፍጠር በቅንጅት እየሰሩ እንደሆነም አብራርተዋል።

ወጣቶች በተገቢዉ ሁኔታ ተኮትኩተዉ እንዲያድጉ የመምህራን ድጋፍ ወሳኝ እንደሆነም አስረድተዉ የመምህራን ስነ ምግባር ጥሩ እንዲሆን ስልጠና በመስጠት አቅም እንዲኖራቸዉ ለማድረግ ስልጠና መሰጠቱም አስታዉሰዋል።

በዞኑ የሚገኙ የአንደኛ ደረጃ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በቤተ ሙከራና ቤተ መጽሀፍቶቻቸዉ እንዲደራጁና ወጣቶችም በዚህም ተጠቃሚ እንዲሆኑ የማድረግ ስራ እየሰሩ እንደነበረም አስረድተዋል።

በዞኑ በተለያዩ አካባቢዎች በበጎ ፍቃድ አገልግሎት ተሰማርተዉ የተቸገሩን ወገኖች የሚደግፉ ወጣቶች ዩኒቨርሲቲዉ የቆርቆሮ፣ የፍራሽ ድጋፍ እንዳደረጉም አስታዉሰዉ ወጣቶች የጀመሩት የበጎ ፍቃድ ስራ አጠናክረዉ ማስቀጠል እንዳለባቸዉም ጠቁመዋል።

የጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ምክትል ሀላፊና የወጣቶች ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብዱ ድንቁ በርክብክቡ ወቅት እንዳሉት የወጣቶች ስብዕና ልማት ማዕከላት ከወቅቱ ፍላጎት እና ሀገራችን ከደረሰችበት የዕድገት ደረጃ ጋር የሚጣጣም ሁሉን አቀፍ፣ሳቢ፣ምቹና ጥራታቸው የጠበቁ አገልግሎት ለወጣቶች መስጠት አስፈላጊ ነው፡፡

የወጣቶች ስብዕና ልማት ማዕከላት ወጣቶች የእረፍት ጊዜያቸውን የሚያሳልፍባቸው፣ የተለያዩ መረጃዎች የሚያገኙባቸው፣ ከቴክኖሎጂ ጋር የሚተዋወቁበትና የንባብ ባህላቸውን ከሚያሳድጉባቸው ቦታዎች ውስጥ አንዱ ቤተ መፅሀፍት እንደሆነም አስረድተዋል።

የወልቂጤ ዩንቨርሲቲ በዞኑ ውስጥ ያሉ ለወጣት ማዕከላት የሚሆን ማጣቀሻ መፅሀፍቶች ድጋፍ እንዲያደርጉላቸዉ ጠይቀዉ ዩኒቨርሲቲዉም ወዲያዉ ምላሽ በመስጠት 3 መቶ 15 የተለያዩ መፅሀፍት በመግዛት ዛሬ ድጋፉ መረከባቸው አስረድተዋል።

ወልቂጤ ዩንቨርሲቲ ያበረከተልን የተለያዩ መፅሀፍቶች በዞኑ አገልግሎት እየሰጡ ባሉ የወጣት ማዕከልና ለማረሚያ ቤቶች የሚሰራጭ ሲሆን ዩኒቨርሲቲዉም ላደረገላቸዉ ድጋፍ በዞኑ ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ስም ከፍ ያለ ምስጋና አቅርበዋል ሲል የዘገበዉ የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነዉ፡፡

በመረጃ ምንጭነት ገጻችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን!!

= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:-
https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *