ከዝናብ ጠባቂነት በመላቀቅ በአመት ሶስት ጊዜ ማምረት መጀመራቸው በጉራጌ ዞን በተለያዩ ወረዳዎች ያነጋገርናቸው አርሶ አደሮች ገለፁ።

በዞኑ ያሉትን ወንዞችና ለሎችም የውሃ አማራጮች በመጠቀም አርሶ አደሩ የመስኖ ተጠቃሚ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑ የጉራጌ ዞን ግብርና መምሪያ አስታወቀ።

መምሪያው የ2014 ዓመተ ምህረት የበጋ የመስኖ ስንዴና መደበኛ የመስኖ ልማት ስራዎች ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካለት ጋር ዛሬ በቀቤና፣ በቸሃና ጉመር ወረዳዎች የበስክ ምልከታ ተካሄደዋል።

አርሶ አደር ጅላልኑር መህዲ እና አርሶ አደር እንዳለ በጉራጌ ዞን ቀቤና ወረዳ ፈረጀቴ ቀበሌ ላይ በመስኖ ስራ የተሰማሩ ናቸው። እንደ አርሶአደሮቹ ገለፃ በመስኖ ስራ በመሰማራት የራሳቸውንና የአካባቢያቸውን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ እየሰራን ነው ብለዋል።

እንደአርሶ አደሮቹ ገለፃ የሽንኩርት ዘርን በማምረትና የበጋ ስንዴን በመስኖ በማልማት ላይ መሆናቸውና ከፍተኛ ውጤት እንደሚጠብቁም ተናግረዋል።

ከቸሀ ወረደ ያነጋገርነው ወጣት አርሶ አደር ዳንኤል ሽፈታ የያሚኒ ማህበር ሰብሳቢ ነው። ከዚህ በፊት በአንድ ሄክታር መሬት ማምረት መጀመራቸውን ገልፀው ወረዳው ባመቻቸላቸው ብድር ዛሬ ላይ 51 ሄክታር መሬት የበጋ መስኖ ስንዴን ጨምሮ በመደበኛ መስኖ የተለያዩ አትክልቶችንና ፍራፍሬ በማምረት ውጤታማ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ወደ ፊትም ከመስኖው ጎን ለጎን እንስሳትን በማደለብ ስራ ለመሰማራት ማቀዳቸውን አርሶ አደር ዳንኤል ገልፀው ቀጣይ እየተደረገላቸው ያለው ድጋፍ በመጠቀም ወደ ኢንቭስትመንት ለመሸጋገር ማቀዳቸውም ጠቁመዋል።

የበጋ መስኖ ስንዴ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደ ዞን የታወጀበት ጉመር ወረዳ አበሱጃ ቀበሌ አርሶ አደር ሸምሱ ኬረታ ከአሁን በፊት በድንች ምርት የሚታወቀው ቀበሌያቸው አሁን ተሞክሮ የማይታወቅ በበጋ መስኖ ስንዴ ማምረት በመቻለቸው እንዳስደሰታቸው ገልፀዋል።

ከ48 ሺህ 700 ሄክታር በላይ መሬት በበጋ የመስኖ ስንዴ እና በመደበኛ በተለያዩ አትክልቶች እለማ መሆኑ የገለፁት የጉራጌ ዞን ግብርና መምሪያ ምክትል ሀላፊና የእርሻ ዘርፍ ሀላፊ አቶ አክሊሉ ካሳ ሀገራችን ከገጠማት የኢኮኖሚ ችግር ለመሻገርና የዜጎች የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ የመስኖ ልማት ስራዎች ማጠናከር ወሳኝ መሆኑ ገልፀዋል።

በዞኑ ያሉትን ወንዞችና ለሎችም የውሃ አማራጮች በመጠቀም አርሶ አደሩ የመስኖ ተጠቃሚ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ የዘርፉ ሀላፊ ተናግረዋል።

ከዚህ በፊት ምርት አይሰጥም ተብሎ ይታሰብ የነበረ መሬት አሁን ላይ በበጋ መስኖ ስንዴ ተዘርቶ ምርት እየተጠበቀ ሲሆን ከዚህ በፊት እንደዞን ያልተሞከሩ አትክልቶችን ማምረት እንደተጀመረ አቶ አክሊሉ ገልፀዋል።

ስንዴው በተለያዩ ተባዮችና በዋግ እንዳይጠቃ የተለያዩ ኬሚካል አቅርቦት ላይ መምሪያው በትኩረት እየሰራ እንደሆነም አስረድተዋል።

የተጀመረው የመስክ ምልከታ በነገ ደረጃ በምስራቅ መስቃን፣ በማረቆና በደቡብ ሶዶ ወረዳዎች እንደሚቀጥል ከመምሪያው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በመረጃ ምንጭነት ገጻችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን!!
= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:-
https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *