የከተሞች መልማትና ማደግ ለዜጎች ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነት ያለው ፋይዳ የጎላ መሆኑን በጉራጌ ዞን የአረቅጥ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ።

በከተማው እየተሰሩ ያሉ የልማት ስራዎችና በአረቅጥ ሀይቅ ዙሪያ በሎጅና በሆቴል ኢንቨስትመንት ፈቃድ ወስደው እየተሰሩ ያሉ ፕሮጀክቶች እና ሌሎች የስራ መስኮች በባለድርሻ አካላት ተጎበኘ።

በጉራጌ ዞን የአረቅጥ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ መንግስቱ ሹሜ እንደገለፁት የከተሞች መልማትና ማደግ ለዜጎች ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነት ያለው ፋይዳ ትልቅ እንደሆነ ገልፀዋል።

ከተማዋ በ2014 አመተ ምህረት የፈርጅ ሶስት የከተማ መስተዳደርነት እውቅና ካገኘ ወዲህ በተቋማትና በሰው ሀይል በማደራጀት ወደ ስራ መገባቱን ጠቁመው ከዚህ ጎን ለጎን ከተማዋ በማስተዋወቅ ህብረተሰቡ የልማት ተጠቃሚ ለማድረግ በትኩረት እንደሚሰራም ጠቁመዋል።

አክለውም ከተማውና በከተማው የሚገኘው የአረቅጥ ሀይቅ የቱሪስት መስህብና የመዝናኛ ማዕከል ለማድረግ እየተሰራ እንደሚገኝ አቶ መንግስቱ ገልፀው ፕሮግራሙ ባለሃብቶችን በማሳተፍ ከተማውና ሀይቁን በማስተዋወቅ ኢንቨስትመንት ለመሳብ ያለመ ነው ብለዋል።

እንደ አቶ መንግስቱ ገለፃ ሀይቁ ለመጠበቅ፣ የበለጠ ለማስፋትና ለማልማት ከባለድርሻ አካላት በተለይም ከወልቂጤ ዪኒቨርስቲ፣ ከባለሀብቶች፣ ከአጋር ድርጅቶች፣ ከአከባቢና ደን ጥበቃ ፅህፈት ቤትና ከሌሎችም ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

በከተማው በሀይቁ ዙሪያ ዓሳ በማርባት ለከተማው ማህበረሰብ በማቅረብ እንዲሁም በመዝናኛ ማዕከል የተሰማሩ የስራ እድል የተፈጠረላቸው ወጣቶች መኖራቸውንም ጠቁመው ከዚህ ጎን ለጎን በሎጅ የተሰማሩ የግል ባለሀብቶችም መኖራቸውንም አስረድተዋል።

በዚህም አንዱ ባለሀብት ወደ ማልማት እንቅስቃሴ የገባ ሲሆን ሌላኛው በዝግጅት ላይ እንደሚገኝም አመላክተዋል።

ከተማዋ ባላት መልከአ ምድራዊ አቀማመጥ፣ የአየር ፀባይ፣ሰላሟ የተረጋገጠና ሌሎችም ሁኔታዎች ለኢንቨስትመንት ምቹ ከመሆኗ አንፃር በቀጣይ በአገልግሎት ዘርፍና በልሎችም ዘርፎች ወደ ከተማዋ በመምጣት ኢንቨስት ለማድረግ ለሚፈልጉ ባለሀብቶች የከተማ አስተዳደሩ አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ገልፀዋል።

ከተማው ለማሳደግ በሚደረገው ጥረት የአከባቢው ማህበረሰብ እያደረገው ያለው ተሳትፎ የሚበረታታ መሆኑን የጠቆሙት ከንቲባው በቀጣይም ከመንግስት ጎን በመሆን እገዛው ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም ተናግረዋል።

አርቲስት ደሳለኝ መርሻና አጋዝ አምደብርሃን ገብረማርያም የፕሮግራሙ ተሳታፊ ሲሆኑ በጋራ በሰጡት አስተያየት ከተማው ለማልማት መንግስት የጀመረው እንቅስቃሴ እንዳስደሰታቸው ገልፀዋል።

ከተማዋ ለማልማት የተጀመረው እንቅስቃሴ አበረታች መሆኑን የገለፁት ተሳታፊዎቹ ኢንቨስት ለማድረግ ወደ ከተማዋ ለሚመጡ ባለሀብቶች ቦታው ምቹ ለማድረግና ተመራጭ እንዲሆን በትኩረት መሰራት እንደሚገባም አመላክተዋል።

አስተያየት ሰጪዎቹ አክለውም ከዚህ ጎን ለጎን የአከባቢው ማህበረሰብ በማሳተፍ የልማት እንቅስቃሴዎችን ማፋጠን ያስፈልጋል ሲሉ ተናግረዋል።

በፕሮግራሙም ብርጋዴል ጀነራል ተስፋዬ ሀብተ ማሪያም ጨምሮ አመራሮች ፣ባለሀብቶች፣ ታዋቂ ሽማግሌዎች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ ከከተማው የተውጣጡ የማህበረሰብ ክፍሎች፣የቶቶት የወጣቶች ማህበር አባላትና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!

በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *