የአንደኛ ደረጃ የእግር ኳስ ስፖርት የዳኝነት ስልጠና በቂ እዉቀትና ልምድ ያገኙበት ስልጠና መውሰዳቸው በጉራጌ ዞን ከተለያዩ ወረዳዎችና ከተማ መስተዳድር የተዉጣጡ ሰልጣኝ ዳኞች አስታወቁ።

የጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ በዳኝነት ሙያ ላይ ለተከታታይ ሰባት ቀናቶች ሲሰጥ የነበረዉ የአንደኛ ደረጃ የእግር ኳስ ስፖርት የዳኝነት ስልጠና በዛሬዉ እለት ተጠናቀቀ።

በስልጠናዉ ማጠናቀቂያዉ ላይ የተገኙት የጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ምክትልና የስፖርት ዘርፍ ሀላፊ አቶ አደም ሽኩር እንዳሉት በስፖርቱ ዘርፍ የሚፈለገዉ ዉጤት እንዲመጣ ለማስቻል የዳኞች አቅም በስልጠና ማገዝ ያስፈልጋል ።

የእግር ኳስ ዉድድሮች በሚዳኙ ዳኞች ላይ የሚስተዋለዉን ችግር ለመቅረፍና የዳኞች እዉቀታቸዉን በማሻሻልና በዞኑ ተተኪ ስፖርት ለማፍራት አጽዕኖት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሆነም አብራርተዋል።

በዘንድሮ አመት ለዳኞች የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠታቸዉም አስረድተዉ በዚህም በዞኑ በእግር ኳስ ዳኝነት ላይ የሚሰማሩ ዳኞች የአንደኛ ደረጃ ስልጠና ወስደዉ ያጠናቀቁ ሰልጣኞች ቀጣይ ወደ ፌዴራል ዳኝነት የሚገቡ ሲሆን ሁሉም ስልጠናዉን የወሰዱ ዳኞች ወደ አካባቢያቸዉ በመሄድ ቀበሌ ድረስ በመዉረድ የተለያዩ ዉድድሮችን ሲኖሩ በተግባር የተማሩትን ተግባራዊ ማድረግ እንዳለባቸዉ አሳስበዋል።

በዞኑ በሚካሄዱ የእግር ኳስ ዉድድሮች ላይ እንዲዳኙ የማድረግ ስራም ከሚመለከተዉ አካል ጋር ተነጋግረዉ እንዲሳተፉ የማድረግ ስራም እንደሚሰራም የተናገሩት አቶ አደም በዚህም የሚሳተፉ ዳኞች የቆይታ ጊዜያቸዉ ሲያበቃ በመምሪያዉ አማካኝነት የፌዴራል ዳኝነት እንዲሳተፉ ምቹ ሁኔታዎች እንደሚፈጠርም አመላክተዋል።

ተተኪ ስፖርተኞች ለማፍራት ታች ድረስ በመዉረድ እዉቀታቸዉንና ልምዳቸዉን ማጋራት እንዳለባቸዉም አብራርተዉ በትምህርት ቤቶች አካባቢና በየቀበሌዉ የሚደረጉ ዉድድሮች በተገቢዉ በመዳኘት የሚፈለገዉ ዉጤት እንዲመጣ መስራት እንዳለባቸዉም አመላክተዋል።

ሰልጣኝ ዳኞች በሙያቸዉ ከታች ጀምረዉ በመስራት በወረዳ ፣ በዞንና በክልል ደረጃ በሚደረጉ ዉድድሮች አቅማቸዉን ታይቶ እንዲሳተፉ የማድረግ ስራም እንደሚሰራም አብራርተዋል።

በዞኑ ከሁሉም ወረዳዎችና ከተማ መስተዳድር የተዉጣጡ 58 የሚሆኑ ዳኞች ለሰባት ተከታታይ ቀናት የአንደኛ ደረጃ ስልጠናዉ ካጠናቀቁ በኋላም ፈተና መዉሰዳቸዉም አስረድተዋል።

አሰልጣኝ ኮሚሽነር ቸሩ ጠበል በበኩላቸዉ በእግር ኳስ ዳኝነት ወቅት የሚስተዋሉ ችግሮች ለመቅረፍ የተሰጠዉ ስልጠና አጋዥ እንደሆነም አስረድተዋል።

በዚህም ሰልጣኝ ዳኞች በቆይታቸዉ በቂ እዉቀትና ልምድ የተጋሩበት እንደሆነም አመላክተዉ ስልጠናዉ የወሰዱ ዳኞችም በቀጣይ ያገኙትን ልምድ ታች ድረስ ወርደዉ ዉጤታማ ስራ መስራት እንዳለባቸዉም አሳስበዋል።

በስልጠና የተሳተፉ አንዳንድ ዳኞች በሰጡት አስተያየት ስልጠናዉ የዳኞችን እዉቀትና አቅም በማሻሻል በዞኑ የሚካሄዱ ዉድድሮች በተሻለ ዳኝነት እንዲመሩ የሚያስችልና አዳዲስ ነገሮችን ያወቁበት ስልጠናም እንደሆነም አስረድተዋል።

በአሰልጣኝ በኮሚሽነር ቸሩ ጠበል ያገኙት አንደኛ ደረጃ የእግር ኳስ ስፖርት የዳኝነት ስልጠና እዉቀት በተለያዩ ዉድድሮች ላይ ዉጤታማ ስራ መስራት እንደሚያስችላቸዉም አብራርተዉ ስልጠናዉን ያመቻቸላቸዉ የዞኑ ወጣቶችና ስፖርት መምሪያም አመስግነዋል ።

በመጨረሻም ለሰልጣኞች የምስክር ወረቀት በመስጠት ስልጠናዉ መጠናቀቁም የዘገበዉ የጉራጌ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን መምሪያ ነዉ።

= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!

በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡

Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *