በንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት፣ በዘመናዊ መስኖ ልማትና በሌሎች ዘርፎች ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ሊያደርጉ የሚችሉ ስራዎች አየሠራ መሆኑን የጉራጌ ዞን ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ መምሪያ ገለፀ።

መምሪያው በ2014 ዓ.ም የ6 ወራት አፈፃፀምና በቀጣይ አቅጣጫዎች ዙሪያ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቡታጀራ ከተማ ጉባኤውን አካሂዷል።

የጉራጌ ዞን ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ መምሪያ ኃላፊ አቶ ፍስሃ ዳምጠው በመድረኩ እንደገለፁት በንጹህ መጠጥ ዉሃ፣በዘመናዊ መስኖ ልማት፣በማዕድን ሀብትና በአማራጭ ኢነርጂ ልማት ህብረተሰቡ ን ተጠቃሚ የሚያደርጉ በርካታ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑንና ሴክቶሪያል የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት እየሰራ መሆኑን ገለፀዋል።

ለወረዳና ለከተማ አስተዳደር አመራርና ባለሙያዎች የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና በመስጠትና ችግር ፈቺ ድጋፍና ከትትል በማጠናከር የተሻለ አገልግሎት መስጠት እንዲቻል እየተደረገ ይገኛል።

የህብረተሰቡን የንጹህ መጠጥ ውሃና የመስኖ ልማት ችግር መሠረት ያረጉ ጥራት ያላቸዉ የጥናትና ዲዛይን በማዘጋጀት ሀብት በማፈላለግ ረገድ ያሉ አማራጮችን መጠቀም እንዲቻል በትኩረት እንደሚሠራ ተናግረዋል።

በሃዉ ተቋማት ግንባታ አንፃር ተቋራጮች ውል ገብተው ወደተግባር ከገቡ በኋላ የሚገጥማቸውን የተለዩ ችግሮች በመቅረፍ ፕሮጀክቶቹ ለውጤት ሊበቃ የሚያስችል ጠንካራ የድጋፍና ክትትል ስራ እንደሚያስፈልግ አበክረው ገልፀዋል ።

የዞኑን የውሃ አቅርቦት ሽፋን ከፍ ለማድረግ እንደ ዞን ከሌላ ጊዜ የተሻለ በጀት መድቦ የተንቀሳቀሰ ቢሆንም አሁን ካለዉ የህብረተሠብ ፍላጎት ጋር ለማመጣጠን እንዳልተቻለ የገለፁት አቶ ፍስሀ ዳምጠው ችግሩን ለመቅረፍ የሚመለከታቸዉ ባለድርሻ አካላትንና ተጠቃሚዉን ህብረተሰብ የጋራ ርብርብ ማድረግ ይኖርባቸዋል።

የጉራጌ ዞን ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ መምሪያ ምከትል ኃላፊ አቶ ዮሓንሰ መሠለ የዉሃ ተቋማት ብልሽት ሲያጋጥማቸው በፍጥነት ጥገና በማድረግ ተገቢውን አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግ ያስፈልጋል።

በተለያዩ ደረጃ የሚገኙ የውሃ ፕሮጀክቶች ተጠናቀው አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ ወረዳና የከተማ አስተዳደር አቅማቸውን አሟጠው በመጠቀም በየደረጃው የሚመለከታቸው የመንግስትና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት የአካባቢው ባለሀብት ለማስተፍ የተጀማመሩ ተግባራት በተጠናከረ መልኩ ሊቀጥሉ ይገባል ብለዋል ።

በተለይም ከንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦትና ከመስኖ ፕሮጀክት ግንባታ አንፃር ህብረተሠቡን ተጠቃሚ ለማድረግ በሚደረገዉ ጥረት የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የድርሻውን እንዲወጣ በተገዉ የማሣተፍ ስራ በቀጣይ በስፋት ይሰራል ብለዋል።

ባለፋት 6 ወራት ከተከናወኑ ተግባራት መካከል 4ጥልቅ የውሀ ጉጓድ ቁፋሮ ግንባታ፣41 መለስተኛ ጥልቅ የውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ መከናወኑንና ከህብረተሰብ ተሳትፎ አንጻር በአዲስ ግንባታና በነባር ተቋሟት የሚያደርገው የጉልበት የገንዘብ አስተዋጽኦ በማጠናከር ከ8,ሚሊዮን ብር በላይ ማሳተፍ መቻሉን በሪፖርቱ ተመላክቷል።

ከመድረኩ ተሳታፊዎች መካከል አቶ ዘካሪያስ ዶቲ ፣ አቶ ኡስማን በድሩና አቶ ተሻ ከፋ በጋራ በሰጡት አስተያየት መምሪያው በስሩ የሚገኙ የወረዳዎችና ከተማ የውሃ ፅህፈት ቤቶችን ለማብቃት የባለሙያው አቅም በመገንባትና ለሚቀርቡ ጥያቄዎቾ እንደዞን የሚሠጡ ተገቢነት ያላቸው ምላሽ የመስጠት ሂደት ለሌሎች ተቋማት አስተማሪ በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጠል እንደሚገባ ተናግረዋል።

ከውሃ ተቋማት አስተዳደር አንጻር መረጃን በማሰባሰብ ፣ችግሩን አጥንቶ መፍትሄ ከማፈላለግ ረገድ ቀቤና የተገኘው ተሞክሮ በሌሎችም አካባቢ ተግባራዊ ሊደረግ ይገባል ።

የህብረተሰቡን ችግር መሠረት ያደረገ ጥራት ያለው የጥናትና ዲዛይን ስራ በመስራት ሀብተ በተቀናጀ መለኩ የማፈላለጉና ሌሎች ስራዎችን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር የበለጠ ተቀራርበው ለመስራት መዘጋጀታቸውን አስተያየት ሰጪዎቹ ተናግረዋል ።

መደረኩ እርበርስ እንደተማማሩበትና ያጋጠሟቸውን ጉድለቶችን ለማረም እንዲሁም በቀጣይ የተሻለ አፈፃፀም በማስመዝገብ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ የጋራ ርብርብ እንደሚያደርጉ ተናግዋል።

= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!

በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡

Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *