ዋርካ ኢትዮጵያ የተሰኘ ሀገር በቀል የበጎ አድራጎት ድርጅት ከአሜሪካን የሙስሊም ተራድኦ ድርጅት በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ነፃ የአይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ጥገና ህክምና በወልቂጤና አካባቢው ለሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል መስጠት መጀመሩን አስታወቀ።

በፕሮግራሙ ከ1 ሺህ 350 በላይ የአይን ሞራ ግርዶሽ ተጠቂ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ነፃ የቀዶ ጥገና ህክምና አገልግሎት ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ተገለጸ ።

የወርካ ኢትዮጵያ የበጎ አድራጎት ድርጅ ስራ አስኪያጅ አቶ ውበይድ ኩመል ህክምናውን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ የአይን ሞራ ግርዶሽ ችግር ኖሮባቸው ከፍለው መታከም የማይችሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ነፃ የአይን ሞራ ቀዶ ጥገና የህክምና አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑን ተናግረዋል።

ይህ ፕሮግራም አሜሪካን አገር ከሚገኝ የሙስሊም ተራድኦ ድርጅት በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ የዞኑ ጤና መምሪያ፣ የወልቂጤ ዩኒቨርስቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከዋርካ ኢትዮጵያ የበጎ አድራጎት ድርጅት ጋር በመተባበር እየተሰጠ መሆኑን ስራ አስኪያጁ ገልጸዋል።

ዋርካ ኢትዮዽያ ፕሮጀክት የመቅረጽ፣ ረጂ ድርጅቶችን የማፈላለግ አንዲሁም የሀኪሞች ቡድን የማዋቀር ስራ መስራቱን የገለጹት አቶ ውበይድ ኩመል በመጀመሪያ ዙር ለ150 የተለያዩ የህብረተሰብ ከፍሎች የአይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ህክምና የተሰጠ ሲሆን በሁለተኛ ዙር ለ1 ሺህ 350 ሰዎች ለማከም እየተሰራ ነው ብለዋል።

እንደ አቶ ውበይድ ገለፃ በቀጣይ የአይን ሞራ ግርዶሽ የነፃ ህክምና አገልግሎት አድማስ በማስፋት በቡታጅራ፣ በጉንችሬና በመሃል አምባ ከተሞች እና በዙሪያቸው ለሚገኙ የህብረሰብ ክፍሎች የሚሰጥ መሆኑን ተናግረዋል።

የወልቂጤ ዩኒቨርስቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ስራ አስኪያጅ ዶ/ር አብድራሂም በድሩ በበኩላቸው የአይን ሞራ ግርዶሽ ለአይነ ስውርነት የሚዳርግ በመሆኑ የማህበረሰቡ አምራችነት በፍተኛ ደረጃ የሚቀንስ መሆኑን ተናግረዋል።

በመሆኑም የችግሩ አሳሳቢነት በመገንዘብ ለህብረተሰቡ እየተሰጠ ያለውን የነፃ ህክምና አገልግሎት እንዲሳካ ሆስፒታሉ የአይን ስፔሻሊስት ሀኪም እንዲያክም ከመመደብ ጀምሮ ምቹ ሁኔታ የመፍጠር ስራ መስራቱን አብራርተዋል።

ሆስፒታሉ ከዋርካ ኢትዮጵያ በጎ አድራጎት ድርጅት ጋር በመተባበር የአይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ጥገና ህክምና የተደረገላቸው ሰዎች በቀጣይ አስፈላጊዉን ክትትል የሚደረግላቸው መሆኑን የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ ገልፀዋል።

በወልቂጤ ዩኒቨርስቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የአይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ጥገና ህክምና ሲደረግላቸው አግኝተን ያነጋገርናቸው አንዳንድ የህብረሰብ ክፍሎች በሰጡት አስተያየት ከጤና ጣቢያ ምርመራ ተደርጎላቸው የአይን ሞራ ግርዶሽ እንዳለባቸው ተለይቶ ዋርካ ኢትዮጵያ ከትራንስፖርት ጀምሮ ባዘጋጀው የነፃ ህክምና ተጠቃሚ መሆን መቻላቸውን ተናግረዋል።

እንደ ታካሚዎቹ ገለጻ ዋርካ ኢትዮዽያ ነፃ ህክምና ዕድል ባያመቻችላቸው ኖሮ በራሳቸው ወጪ የመታከም አቅም ያልነበራቸው መሆኑን ጠቁመው ለተደረገላቸው የነፃ ህክምና አገልግሎት ምስጋና አቅርበዋል።

የዋርካ ኢትዮጵያ የበጎ አድራጎት ድርጅት ስራ አስኪያጅ አቶ ውበይድ ኩመል ለፕሮግራሙ መሳካት አስፈላጊውን እገዛ ላደረጉ ለዞኑ አስተዳደር፣ ለጤና መምሪያና ለወልቂጤ የኒቨርሲቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ላቅ ያለ ምስጋና አቅርበዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

በመረጃ ምንጭነት ገጻችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን!!
= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:-
https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *