የኮቪድ 19 በሽታ በሀገሪቱ እያስከተለ ያለው ጫና እየጨመረ በመምጣቱ ህብረተሰቡ ለሁለተኛ ጊዜ የሚሰጠው ክትባት ተከታትሎ መከተብ እንደሚያስፈልግ የጉራጌ ዞን ጤና መምሪያ አሳሰበ።

የካቲት 9/2014 ዓ.ም
የኮቪድ 19 በሽታ በሀገሪቱ እያስከተለ ያለው ጫና እየጨመረ በመምጣቱ ህብረተሰቡ ለሁለተኛ ጊዜ የሚሰጠው ክትባት ተከታትሎ መከተብ እንደሚያስፈልግ የጉራጌ ዞን ጤና መምሪያ አሳሰበ።

መምሪያው ከነገ ጀምሮ የሁለተኛ ዙር የኮቪድ 19 ክትባት ለሚሰጡ የጤና ባለሙያዎች ኦረንቴሽን በዛሬው እለት በወልቂጤ ከተማ ሰጥቷል።

የጉራጌ ጤና መምርያ ኃላፊ አቶ ሸምሱ አማን ዛሬ በሰጡት መግለጫ የኮቪድ 19 በሽታ በሀገሪቱ እያስከተለ ያለው ጫና እየጨመረ በመምጣቱ ህብረተሰቡ ለሁለተኛ ጊዜ የሚሰጠው ክትባት ተከታትሎ መከተብ እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።

ከዚህ በፊት በዞናችን በህክምና የተረጋጡ ከ3ሺ 100 በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች በበሽታው ሲያዙ 54 ሰዎች በኮቪድ መሞታቸው አስታውሰዋል።

በዞኑም በኮቪድ 19 በሽታ የመያዝ ምጣኔ በአማካይ 16 ፐርሰንት መሆኑንም አቶ ሸምሱ አማን አመላክቷል ።

በሽታው ባለፉት ሳምንታት ጉንፋን ነው እየተባለ ብዙ ሰዎች ለህመም መዳረጉ አስታውሰዋል።

ክትባቱ እንደ ሀገር በእርዳታ አለያም በመዋጮ ብቻ የሚገኝ በመሆኑ እንደ እድል ተጠቅሞ ሁሉም ሰው መከተብ እንዳለበት አሳስበዋል።

አቶ ሸምሱ አክለውም ክትባቱ ሙሉ ለሙሉ ኮቪድ እንዳይዘን ያደርጋል ማለት ሳይሆን በሽታው የመከላከል አቅም በመጨመር በሰዎች ላይ የሚያደርሰው ጉዳት በኛ ላይ እንዳይደርስ በማድረግ እንደጉንፋን አደርጎ ሊያሳልፍልን የሚችል አቅም ያለው ክትባት መሆኑን አስገንዝበዋል።

በሀገራችንም በከፍተኛ ሁኔታ እየሞቱ ያሉት ክትባቱ ያልወሰዱ የህብረተሰቡ ክፍሎች በመሆናቸው ክትባቱ ከተወሰደ ፋይዳው እጅግ የጎላ ነው ያሉት አቶ ሸምሱ አማን።

በከተሞች አካባቢ እድሜያቸው ከ12 አመት በላይ የሚሆኑ ተማሪዎች ክትባቱ እንዲወስዱ ምቹ ሁኔታ ስለተፈጠረ የትምህርት አካላትና ወላጆች ማገዝ እንዳለባቸው ጠቁመዋል ።

ለመጀመርያ ጊዜ ክትባቱ የወሰዱ የህብረተሰቡ ክፍሎች አሁንም የመውሰድ እድል ስላላቸው ካርዳቸው ይዘው በመገኘት መከተብ ይችላሉ ብለዋል።

የዞኑ ማህበረሰብ በበሽታው የባሰ እንዳይጎዳ የጤና ባለሙያዎች፣የሀይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ለዚህ ተግባር በትኩረት እንዲሰሩ ጥሪ አስተላልፈዋል።

አቶ ሸምሱ በመጨረሻም ወደ መከተቢያ ቦታ ሲመጡ ማስክ በማድረግ ሳኒታይዘር በመጠቀም እጅን በሳሙና በመታጠብና የተለያዩ ጥንቃቄዎች ማድረግ እንደሚያስፈልግ በመግለጫቸው አሳውቋል።

አቶ ቸሩ አስፋው የመምርያው የእናቶችና ህጻናት ጤናና ስርአተ ምግብ አስተባባሪ እንዳሉት በመጀመሪያ ዙር ክትባት ዘመቻ ከ2መቶ 75ሺ በላይ የህበረተሰብ ክፍሎች መከተባቸው አስታውሰው በዚህ ዙር ደግሞ ለ4መቶ 32 ሺ 2መቶ 15 የህብረተሰብ ክፍሎች ክትባቱ ይሰጣል ብለዋል።

ኮለኔል አበበ ሱሙት እና አቶ ታደሰ በስር የመምርያው ባለሙያ ናቸው።ለ3ኛ ጊዜ እንደተከተቡ ገልጸው ለበሽታው መከላከልም አስተዋጾ አድርጎልናል ያሉ ሲሆን ብዙ ሰዎች የተሳሳተ መረጃ ቢሰጡም ምንም ተጽኖ እንደሌለው ተናግሯል።

ክትባቱ ከመጣ ጊዜ ጀምሮ ህብረተሰቡ የመያዝ ቁጥር ባይቀንስም የሞት መጠን ግን ቀንሷል ነው ያሉት።

ወ/ሮ ዙርያሽ ሀይሌ የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያ ሲሆኑ ከዚህ በፊት ምንም ያልወሰዱት ጆንሰን ክትባት ለሌሎቹ ደግሞ ፋይዘር እና አስትራዛኒካ ክትባት እንደሚሰጡ አመላክቷል።

ክትባቱ ከነገ (10/6/2014 ዓመተ ምህረት)ጀምሮ በሁሉም ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች የሚሰጥ ይሆናል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው ።

= አካባቢህን ጠብቅ!
=ወደ ግንባር ዝመት!
= መከላከያን ደግፍ!

በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *