በወልቂጤ ከተማ አስተዳደር የሚገነባው ከማራኪ ካፌ እስከ ኤደን ገነት ያለውን የ1 ነጥብ 8 ኪሎ ሜትር የአስፓልት መንገድ ግንባታ በዛፍራን ኮንስተሰራክሽን ስራ ተጀመረ!!

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ እንዳለ ገብረመስቀል የአስፓልት ግንባታ ስራው ባስጀመሩበት ወቅት እንዳሉት ከመሰረተ ልማት አውታሮች ቀዳሚውን ስፍራ የሚይዘው መንገድ የማህበረሰቡ ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ ከመቆጣጠሩም ባለፈ ተጠቃሚነታቸውን ያጎለብታል።

በዚህ ረገድ በወልቂጤ ከተማ አስተዳደር የውስጥ ለውስጥ የመንገድ ስራዎች በትኩረት እየተሰራ መሆኑንና በአዲስ ለመገንባት የውል ስምምነት የተፈጸመበትን ከማራኪ ካፌ እስከ ኤደን ገነት ያለውን መንገድ ተጠቃሽ ነው ብለዋል።

የ1 ነጥብ 8 ኪሎ ሜትር እርዝመት ያለው የመንገድ ግንባታ ስራ ጥራቱን በጠበቀ መልኩ ከመሰራቱም ባለፈ እስከ 12 ዓመት ያለ ጥገና አገልግሎት መስጠት እንደሚችልም ጠቁሟል።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ሔኖክ አብድልሰመድ በበኩላቸው የማህበረሰቡ የልማት ጥያቄዎች ለመመለስ ከተማ አስተዳደሩ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

የመንገድ ግንባታው ከማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ባለፈ የማህበረሰቡ አንድነትን የሚያጠናክር መሆኑን በመግለጽ የመንገድ ግንባታው በታቀደለት ጊዜ ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት እንዲሆን ማህበረሰቡ እገዛ ማድረግ እንዳለበትም አስገንዝበዋል።

ከመንገድ መሰረተ ልማት በተጨማሪም ቀጣይ ሌሎች የህብረተሰቡን የልማት ጥያቄዎች ወቅቱን በጠበቀ መልኩ ለመመለስ ይሰራልም ብለዋል።

በመረሃ-ግብሩ ላይ የመንገድ ተቋራጭ የስራ ሃላፊዎች፣ የከተማ አመራሮችና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል ሲል መረጃው ያደረሰን የከተማው የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው።

በመረጃ ምንጭነት ገጻችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን!!

= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!

በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:-
https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *