የጉራጌ ዞን ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴዎች በተመረጡ ወረዳዎችና ከተሞች የመጀመሪያው ግማሽ አመት እቅድ አፈፃፀም የመስክ ምልከታ ግምገማ አካሄዱ።

የጉራጌ ዞን ምክር ቤት የሶስቱም ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴዎች በተመረጡ ወረዳዎች፣ከተሞችና ቀበሌዎች የመጀመሪያው ግማሽ አመት እቅድ አፈፃፀም የመስክ ምልከታ የተለያዩ ተቋማት አስፈፃሚዎች እና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ገምግመዋል።

መድረኩን የመሩት የጉራጌ ዞን ምክርቤት ዋና አፈጉባኤ ክብርት ወይዘሮ አርሺያ አህመድ እንደገለፁት አገልጋይነታችን ለመረጠን ህዝብ እንደመሆኑ መጠን ተግባራቶችን በመደገፍ በመከታተልና በመቆጣጠር ማስፈፀም ይገባል።

ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ማለት የቴክኖሎጂ አጠቃቀም፣ የግብዓት አቅርቦት፣መሠረታዊ የልማት ስራዎች እና የእዳ አመላለስ ጉዳዮች ላይ በትኩረት መስራት እንዳለብን ምልከታው አነሳሽ ነው ሲሉ ክብርት አፈጉባኤዋ ገልጸዋል።

አስፈፃሚ ተቋማት በመቀራረብ፣የመረጃ ፍሰቱን በማሳለጥ፣ ቅንጅታዊ አሰራር በማጠናከር የዞኑ ህዝብ ፍትሀዊ ተጠቃሚ እንዲሆን ወደ ኋላ የቀሩ ተግባራቶችን ማከናወን እንዳለባቸው አስረድተዋል።

በጉራጌ ዞን ምክርቤት የሴቶች ወጣቶች እና ማህበራዊ ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ አህመድ ሀሰን እንደገለፁት በየደረጃው ከሚገኙ አስፈፃሚዎች ጋር ግልፀኝነት ለመፍጠርና በልማት በመልካም አስተዳደርና በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የተሻለ ውጤት ለማምጣት ምልከታው አስፈልጓል።

በምልከታው በጥንካሬ የሚገለፁ የአገልግሎት አሰጣጥና ቅንጅታዊ አሰራር ማየት ተችሏል የሚሉት የተከበሩ አቶ አህመድ የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በየደረጃው ያሉ አመራሮች ችግሮችን እየለዩ ለመፍታት የሚያደርጉት ጥረት አበረታች ነው።

ቋሚ ኮሚቴው በጉድለት ካያቸው እቅድን ለማሳካት ህዝቡ ላይ ግንዛቤ ከመፍጠር አንፃር እና የተገኙ ውጤቶችን ወጥነት ባለው መልኩ ተቋማትን ከመቀራረብ አንፃር ውስንነት መኖሩን የተከበሩ አቶ አህመድ አክለው ገልፀዋል።

በምክርቤቱ የኢኮኖሚ ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ አለምይርጋ ወልዴ በበኩላቸው በምልከታው በርካታ ጠንካራ ተግባራቶችን በመንገድ፣በውሃና በመስኖ ፕሮጀክቶች እና በበጋ የመስኖ ስንዴ መመልከት እንደቻሉም ገልፀዋል።

ትኩረት ከሚሹ ጉዳዮች መካከል የስራ እድል ፈጠራ ላይ የሴቶች ተሳትፎ ማነስ፣በበጋ የስንዴ መስኖ ሁሉም የታረሰ መሬት አለመሸፈኑ፣ትኩረት የሚፈለረጉ የመስኖና ሌሎችም የፕሮጀክት ስራዎች መኖራቸውና ከመንገድና ንፁህ ውሃ ተደራሽነት ተያይዘው የሚነሱ ችግሮች እና የፕሮጀክቶች ማስፈፀም ችግሮች መኖራቸው የተከበሩ አቶ አለሜይርጋ አክለው ገልጸዋል።

በምክር ቤቱ የህግ፣ፍትህና የመልካም አስተዳደር ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ ወይዘሮ ሄሪያ ወርቁ እንዳሉት በመስክ ምልከታው ወቅት በዞኑ የተጀመሩ ፣ሰላምና ፀጥታ የማስጠበቅ፣የህግ የበላይነት የማስከበር፣የፍርድ ቤቶች ውሳኔ ሰጪነት እየተሻሻለ መሆኑ እና ሌሎችም ስራዎች መጠናከር አለባቸው።

በሌላ መልኩ በዚህ ዘርፍ የተቋማቱ፣ አደረጃጀት፣ ከሰብአዊ መብት አያያዝ አንፃር በምልከታው ችግሮች ማስተዋል ችለናል ብለዋል።

አክለውም የስጋት አካባቢዎችን እና አካላትን በመለየት ስራ ከመስራት አንፃር ያለው ውስንነት፣ እንዲሁም የፍታብሔርና የወንጀል ጉዳዮችን ለይቶ ያለመመልከትና ሌሎችም ውስንነቶች ማረምና ማሻሻል እንደሚገባ ክብርት ሄሪያ ወርቁ ገልፀዋል ።

በግምገማው የተሳተፍ የሴክተር አመራሮች በበኩላቸው ከተቋማቶች አንፃር የታዩትን የአሰራርና የተግባር ጉድለቶች በመሙላት ቀጣይ ለተሻለ ተግባር እንድንዘጋጅ ያግዛል ሲሉ ገልፀዋል።

ህዝቡ ፍትሀዊና ቀልጣፋ በሆነ መልኩ አገልግሎት ማግኘት እንዲችል በቀጣይ ትኩረት ተሰጥተው እንደሚሰሩም ተሳታፊ አመራሮቹ ገልጸዋል።

በመረጃ ምንጭነት ገጻችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን!!

= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!

በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡

Facebook:-
https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *