ሴቶች ማህበራዊ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸው ለማሳደግ የልማት ቡድን አደረጃጀቶች ማጠናከር እንደሚገባ የጉራጌ ዞን ሴቶችና ህጻናት ጉዳይ መምሪያ ገለፀ።

የሴቶች የልማት ቡድን ስትሪንግ ኮሚቴ በሴቶች ተጠቃሚነት እና ልማት ቡድን ውጤታማነት ላይ በወልቂጤ ከተማ ውይይት አድርጓል።

የጉራጌ ዞን አስተዳደር ተወካይና የዞኑ ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ሸምሱ አማን እንደተናገሩት የሴቶች የልማት ቡድን በማጠናከር ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን ለማሳደግ የስትሪንግ ኮሚቴ አባላት ትኩረት ሰጥተው መስራት ይጠበቅባቸዋል ።

የሴቶች የልማት ቡድን የዜጎች ፍትሀዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት የተናገሩት አቶ ሸምሱ የስትሪንግ ኮሚቴ አባላት ሴቶች በልማት ቡድን ላይ በንቃት እንዲሳተፉ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።

የዞኑ ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ ወይዘሮ መሰረት አመርጋ በበኩላቸው ሴቶች በልማት ቡድን በመደራጀታቸው ዘርፈ ብዙ ጥቅም የሚያገኙ በመሆኑ አደረጃጀቶቻቸው እንዲጠናከሩ ስትሪንግ ኮሚቴው ትኩረት ሰጥቶ መስራት ይጠበቅበታል ብለዋል።

ሴቶች ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸው ለማሳደግ የልማት ቡድን አደረጃጀቶች ማጠናከር እንደሚገባ የተናገሩት ኃላፊዋ መምሪያው ተጠቃሚነታቸውን ይበልጥ ለማሳደግ ትራክተር፣ ኮምባይነር፣ ጀነሬተርና ሌሎች ምርትና ምርታማነትን የሚያሳድጉ ቴክኖሎጂዎች እንዲያገኙ እየሰራ መሆኑን አስረድተዋል።

የሴቶች የልማት ቡድን አደረጃጀት ተግባራት በወቅቱ እንዲተገበሩ የሚያስችል በመሆኑ ኮሚቴው አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል ማድረግ እንዳለበት ኃላፊዋ ገልጸዋል።

የምክክር መድረኩ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት የሴቶች ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ለማሳደግ መምሪያው እያደረገ ያለው እንቅስቃሴ የሚበረታታ በመሆኑ በቀጣይ በዞኑ ሞዴል አደረጃጀቶች ለመፈጠር ድጋፍ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።

ለልማት ቡድኖች ስኬታማነት በየደረጃው የሚገኙ አስፈፃሚ አካላት እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት የሚጫወቱት ሚና የጎላ በመሆኑ በቀጣይ የሴቶች የልማት ቡድን በመደግፍ ሞዴል አደረጃጀቶች እንዲፈጠሩ ማገዝ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል ።

ባለፉት አመታት የሴቶች የልማት ቡድን በዞኑ ከፍተኛ ውጤት ማስገኘቱን የገለፁት ተሳታፊዎቹ ከለውጡ ወዲህ የተቀዛቀዘው የሴቶች የልማት ቡድን እንቅስቃሴ ለማነቃቃት መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *