ዞኑ የሚያመነጨውን ገቢ በአግባቡ አሟጦ ለመሰብሰብና የተጀመሩ ልማቶችን አጠናክሮ ለማስቀጠል የግብር ከፋዮችና የባለድርሻ አካላት ሚና ወሳኝ መሆኑን የጉራጌ ዞን ገቢዎች ባለስልጣን ዋና ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

የጉራጌ ዞን ገቢዎች ባለስልጣን ዋና ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ከወልቂጤ ከተማ ገቢዎች ባለስልጣን ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ጋር በመተባበር በወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ውስጥ ለሚገኙ ለደረጃ ‘ሀ’ እና ‘ለ’ ግብር ከፋዮች በታክስ አስተዳደር አዋጅ፣ የገቢ ግብር አዋጅና ደንቦች ተከትሎ በወጡ መመሪያዎች ዙሪያ የክህሎት ስልጠና በወልቂጤ ከተማ ተሰጥቷል።

የጉራጌ ዞን ገቢዎች ባለስልጣን ዋና ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሚነወር ሃያቱ እንደገለፁት ዞኑ የሚያመነጨውን ገቢ በአግባቡ አሟጦ ለመሰብሰብና የተጀመሩ ልማቶችን አጠናክሮ ለማስቀጠል የግብር ከፋዮችና የባለድርሻ አካላት ሚና ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።

አቶ ሚነወር አክለውም ነጋዴው ማህበረሰብ ግብር በሚከፍልበት ወቅት ቀልጣፋና ተገቢ አገልግሎት መስጠት እንደሚገባው እና ለዚህም የታክስ ስርአቱ ለማዘመን ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።

አዲስ አበባ መርካቶ ላይ በደረሰኝ አሰጣጥ ላይ የሚስተዋለውን ችግር ለመቅረፍ ከባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ በመሆን በቅንጅት እየተሰራ ይገኛል።

እንደ ኃላፊው ገለፃ ከወጪ ስርአቱ ጋር ተያይዞ ነጋዴው ማህበረሰብ የሚያወጣቸውን ወጪዎችን በአግባቡ መዝግቦ መያዝ አለበት ብለዋል።

የጋራ ገቢ የሚያሳውቁት አክሲዮን ድርጅቶች ወልቂጤ ከተማ ላይ ማዕከል በመክፈት ታክሳቸውን እንዲያሳውቁ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን የተጀመሩ ስራዎች መኖራቸውና ችግሩንም ለመቅረፍ በትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል።

አያይዘውም ከውሃና ከመብራት ጋር የሚስተዋለውን ችግሮችን በዘላቂነት ለመቅረፍ እየተሰራ መሆኑንም አቶ ሚነወር አመላክተዋል።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሰፋ ዘይኑ በበኩላቸው ህብረተሰቡ የሚያነሷቸው የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ ከተማው የሚያመነጨውን ገቢ አሟጦ መሰብሰብ ያስፈልጋል ብለዋል።

አክለውም የስልጠናውም አላማ ግብር ከፋዩ ማህበረሰብ በቂ ግንዛቤ አግኝቶ የታክስ ህጎች፣ መመሪያዎችና ደንቦችን ተገንዝቦ በእውቀት ስራዎቻቸውን እንዲሰሩ ለማስቻል መሆኑን አስረድተዋል።

በስልጠናው የተገኙ ተሳታፊዎቹ እንዳሉት ስልጠናው ጥሩና ወቅቱን የጠበቀ መሆኑን አንስተው እንዲህ አይነት ስልጠናዎች በግብር አከፋፈል ዙሪያ ላይ የሚስተዋለውን ችግር ለመቅረፍ ሚናው ትልቅ መሆኑንም ጠቁመዋል።

አክለውም በስልጠናውም በቂ ግንዛቤ እንዳገኙበትና በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ጠይቀዋል።

አስተያየት ሰጪዎቹም በደረሰኝ አሰጣጥ ዙሪያ የሚስተዋለውን ችግር በተለይም የመርካቶ የደረሰኝ አሰጣጥ ችግር፣ በከተማው የሚስተዋለውን የመብራትና የውሃ ችግር፣ አክሲዮን ድርጅቶች ታክሳቸውን ለማሳወቅ እስከ ሀዋሳ በመሄድ እየተንገላቱ በመሆኑ ወልቂጤ ከተማ ላይ ቅርንጫፍ ቢከፈት እና ሌሎችም ጥያቄዎችን አንስተው ከመድረኩ ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል።

በስልጠናውም የጉራጌ ዞን ገቢዎች ባለስልጣን ዋና ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሚነወር ሃያቱና የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሰፋ ዘይኑ ጨምሮ የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር የደረጃ ‘ሀ’ እና ‘ለ’ ግብር ከፋዮች የዞኑና የከተማ አስተዳደር የገቢ ሴክተርና የንግድ ባለሙያዎች እና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!

በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *