ሁሉም ያማከለ ቀልጣፋና ቴክኖሎጂን መሰረት ያደረገ አገልግሎት በመስጠት የተገልጋዮቹን ፍላጎት ለማሟላት እንደሚሰራ ዘምዘም ባንክ ገለጸ።

ባንኩ የአገልግሎት አድማሱን በማስፋት 20ኛው ቅርንጫፉን በወልቂጤ ከተማ ከፈተ።

የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሀመድ ጀማል ዘምዘም ባንክ የወልቂጤ ቅርንጫፍ ተመርቆ አገልግሎት ባስጀመሩበት ወቅት እንደተናገሩት ባንኩ በሀገሪቱ ሙሉ በሙሉ ከወለድ ነጻ አገልግሎት በመስጠት ቀዳሚ ሲሆን ሁሉም ያማከለ ቀልጣፋና ጥራት ያለው አገልግሎት መስጠት እንዲችል ሊሰራ ይገባል ።

እንደ አቶ መሀመድ ገለጻ ባንኩ አገልግሎት የሚሰጠው ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በመሆኑ የተለያዩ አማራጮች በማስፋት ይበልጥ ተጠቃሚ ማድረግ ይጠበቅበታል ።

በዞኑ በርካታ ባንኮች ቢኖሩም ለወጣቶች የፈጠሩት የስራ እድል አነስተኛ እንደሆነ የገለጹት አስተዳዳሪው ዘምዘም ባንክ ገንዘብ ማስቆጠብ ብቻ ሳይሆን ወጣቱንም ጨምሮ ሰርቶ መለወጥን ለሚፈልግ ማህበረሰብ አማራጮችን የሚያቀርብ በመሆኑ በዞኑ አድማሱን ማስፋት ይጠበቅበታል ብለዋል።

የወልቂጤ ከተማ ከንቲባ አቶ እንዳለ ገብረመሰረቀል በበኩላቸው ከተማው ለኢንቨስትመንት ምቹና ተመራጭ ለማድረግ እየተሰራ ይገኛል። በመሆኑም ዘምዘም ባንክ ጥራት ያለው አገልግሎ መስጠት እንዲችል የኢንቨስትመንት ቦታ ለመስጠት የከተማ አስተዳደሩ ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል።

የባንኩ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ከድር በደዊ ባንኩ ሁሉም ያማከለ ቀልጣፋና ቴክኖሎጂን መሰረት ያደረገ አገልግሎት በመስጠት የተገልጋዮቹን ፍላጎት ለማሟላት ይሰራል ብለዋል።

የማህበረሰቡ የንግድ አሠራር ከሸሪዓው ጋር በተጣጣመ መልኩ እንዲዘምን ያግዛል ያሉት ምክትል ፕሬዝዳንቱ በዚህም የሀገርን ኢኮኖሚያዊ ዕድገት እና ልማት እንፈሚያፋጥን አረጋግጠዋል።

ዘምዘም ባንክ ለደንበኞቹ በተለያዩ ቴክኖሎጂ አማራጮች ተደራሽ ለመሆን ትኩረት ሰጥቶ የሚሰራ መሆኑም አቶ ከድር ገልጸዋል።

የዘምዘም ባንክ የቦርድ ሰብሳቢ ዶክተር ናስር ዲኖ በበኩላቸው ባንኩ አቅም እያላቸው እጃቸው ላይ ገንዘብ የሌላቸው ዜጎችን የመደገፍ ስራ እንደሚሰራ አመልክተዋል።

የባንኩ ደንበኞች በሰጡት አስተያየት ከዚህ ቀደም በባንኮች ኢንዱስትሪ የነበረው የብድር አገልግሎት የሁሉም ዜጎች አቅም ያማከለ ባለመሆኑ በዝቅተኛ የኢኮኖሚ ደረጃ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ወጣቶችንም ጨምሮ ተጠቃሚ የሚያደርጉበት ስርዓት አልነበረም።

ዘምዘም ባንክ ግን የንግድ ስርዓቱ በፍትሀዊነት እና በነጻነት ለማስኬድ የሚያስችል ሲሆን ማንም ከወለድ ነጻ አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆን ያስቻለ ባንክ ነው ብለዋል።

በመሆኑም ባንኩ የሚሰጠው አገልግሎት ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ተደራሽ ለማድረግና ህብረተሰቡ በባንኩ ላይ ያለውን ግንዛቤ ለማሳደግ የተለያዩ የሚዲያ አማራጮች በመጠቀም መረጃዎች ተደራሽ ማድረግ ይገባል ብለዋል።

= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!

በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *