በህልውና ጦርነቱ ወቅት የታየው ህዝባዊ አንድነትና ሀገር የማዳን ስራ በድህረ ጦርነቱም አጠናከሮ ማስቀጠል እንደሚገባ የጉራጌ ዞን አስተዳደር ገለፀ።

አመራሩ በየአካባቢው የሚነሱ የልማትና መልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት በቁርጠኝነት መስራት እንደሚገባም ተገልፀዋል

የዞንና የወረዳ ከፍተኛ አመራሮች በወቅታዊና ሀገራዊ ጉዳይ ለ3 ተከታታይ ቀናት በቡታጀራ ሲያደርጉት የነበረው በውይይት ዛሬ ተጠናቋል ።

የደቡብ ክልሉ የመንግስት ረዳት ተጠሪ አቶ ይሁን አሰፋ በመድረኩ ማጠቃለያ ወቅት እንዳሉት በጦርነቱ የታየውን ሀገራዊ አንድነትና የመደጋገፍ ባህላችን በድህረ ጦርነቱም ማስቀጠል አለብን ብለዋል።

የፀጥታና ደህንነት ጉዳዮችን ትኩረት ተሰጥቶ መሰራት አለበት የሚሉት አቶ ይሁን የሚዲያ ስራዎቻችንና የመልሶ ማቋቋም ስራው በእቅድ መመራት እንዳለበት አሳስበዋል።

አቶ ይሁን አክለውም አመራሩ የዞኑ ህዝብ የሚያነሳቸው የልማትና መልካም አስተዳደር ችግሮች እንዲሁም የሰላምና የህግ የበላይነት ጥያቄዎች ለይቶ በትኩረት መስራት አለበት ብለው የዞኑ ህዝብ የጠየቃቸው የአደረጃጀት ጥያቄዎች በህግና በአሰራሩ መሰረት ምላሽ ያገኛል ሲሉም ጠቁመዋል።

የደቡብ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት የዲሞክራሲ ሰርዓት ማሰተባበሪያ ማዕከል ምርምር ሰልጠና ሱፐርቪዠን ዘርፍ ሀላፊ አቶ ዘሪሁን እሸቱ እንደገለፁት ድሉ የመላው ኢትዮጵያውያን በመሆኑ ህብረ ብሄራዊ አንድነታችን እንዲበለፅግ ወደፊትም በጋራ መቆም አለብን ብለዋል።

ያሳለፍነው ውስብስብና የጦርነት ጊዜያቶችን የሚክስ የብልጽግና ጉዞ መጀመር አለብን የሚሉት አቶ ዘሪሁን እሸቱ ኢትዮጵያ የራሷን ብቻ ሳይሆን የጎረቤት ሀገራትን ሰላም ማስጠበቅ የምትችል ሀገር በመሆኗ በቀላሉ አትፈርስም ብለዋል።

የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሀመድ ጀማል በበኩላቸው ያሳለፍነው የጦርነት ጊዜ በቀጣይ ተቀናጅቶ እና ተናቦ በመስራት አመርቂ ውጤት ላይ መድረስ እንደሚያስችል ትምህርት የተወሰደበት ነበር ብለዋል ።

በጦርነቱ የወሰድናቸው ጥሩ ልምዶች ይዘን በድህረ ጦርነቱ ሊያጋጥሙን የሚችሉ ችግሮች ነቅሰን በማውጣት ከድል ሽሚያና ከፖለቲካ ክፍፍል አመራሩ በመጠንቀቅ በየአካባቢያችን ያሉ ህገወጥነቶች በማስቆም ለተሻለ ውጤት መትጋት አለብን ብለዋሎ ።

አቶ መሀመድ አክለውም የዞናችን ማህበረሰብ በርካታ ችግሮችን ያሳለፈ፣በንቃት አካባቢው ሲጠብቅና ሲያለማ የቆየ እንዲሁም ከሁሉም ነገር በላይ የሀገር ጉዳይ አስቀድሞ ሲረባረብ መቆየቱ ገልፀው በቀጣይ ወቅቶች ህዝቡ በየደረጃው የሚያነሳቸው መሰረታዊ የሆኑ የልማትና መልካም አስተዳደር እንዲሁም የአደረጃጀት ጥያቄዎችን በተገቢውና በአሰራር መፍታት እንደሚገባም አመላክተዋል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው መድረኩ የአመራሩን ቁመና በመፈተሽ ለተሻለ ተግባር እንዲነሳሱ መነቃቃትን የፈጠረ ነው ብለዋል።

በቀጣይ በድህረ ጦርነቱ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮች ቀድመን በመከላከል የስራ እድል ፈጠራ፣ የገቢ አማራጮች፣ የበጋ መስኖ፣ በግብርናው ምርትና ምርታማነትን እና የኑሮ ውድነትና የዋጋ ግሽበትን ለመከላከል ትኩረት ሰጥን እንሰራለን ብለዋል።

= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!

በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *