የእናት ሀገራቸው ጥሪ ተቀብለው ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ ትውልደ ኢትዮጵያውንና የዞኑ ተወላጅ ዳያስፖራዎች ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት መዘጋጀቱን የጉራጌ ዞን ኢንቨስትመንት ማስፋፊያ ጽህፈት ቤት ገለጸ።

የጽ/ቤቱ ሀኃላፊ አቶ ዘነበ ደበላ የዳያስፖራው የእናት ሀገር ጥሪ ተቀብሎ መምጣቱ ተከትሎ ለኢኮኖሚው ዘርፍ የሚያደርገው እገዛ ለማጠናከር ወደ ዞኑ በመምጣት ኢንቭስት እንዲያደርጉ በዞኑ ያሉ አማራጮች አስመልክተው መግለጫ ሰጥተዋል።

ዳያስፖራው በየትኛውም ሰአት ቢመጣ ለማስተናገድ በገጠርና በከተማ ከ5 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት የተዘጋጀ መሆኑና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት ዝግጅት መጠናቀቁ ፅ/ቤቱ ዝግጁነቱን አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ ገልፀዋል።

ለኢንቨስትመንት ምቹና ተመራጭ ከሆኑ የሀገሪቱ ክፍሎች አንዱ ጉራጌ ዞን ነው።

ዞኑ ለኢንቨስትመንት ተመራጭ ከሚያደርጉት ነገሮች መካከል በዞኑ በየደረጃው የሰለጠነ የሰው ኃይል መኖሩ፣ለማእከላዊ ገበያው በቅርብ እርቀት መገኘቱ፣ለኢንዱስትሪ፣ለግብርና እና ለአገልግሎት ዘርፍ የተዘጋጁ በቂ ቦታዎች መኖራቸው፣የምዕራብ ኢትዮጵያ የልማት ኮሪደር መሆኗ፣እንዲሁም የስልክ፣የመብራት፣ የውሃና የመንገድ መሰረተ ልማቶች መስፋፋትና የተለያዩ ባንኮችና አነስተኛ የቁጠባና ብድር አገልግሎት የሚሰጡ የገንዘብ ተቋማት መኖራቸው በዋነኛነት ይጠቀሳሉ ሲሉ አቶ ዘነበ ደበላ ገልፀዋል።

ዞኑ ሰላም የተረጋገጠበት፣ምቹና ለም መሬት የሚገኝበት እንዲሁም ሶስቱም የአየር ፀባይ የሚገኝበት በመሆኑ በየትኛውም ዘርፍ ለሚሰማሩ ባለሀብቶች ትርፋማ ስለሚያደርግ በዞኑ መዋዕለ ነዋያቸውን የሚያፈሱ ባለሀብቶች ለመቀበል ዝግጅቱን አጠናቋል ብለዋል።

የዞኑ አስተዳደር የእናት ሀገር ጥሪን ተቀብለው ወደ ሀገራቸው ብሎም ወደ ዞኑ ለሚመጡ የዞኑ ወላጆችና ኢትዮጵያውያን በሙሉ የእናት ሀገራቸው ጥሪ በመቀበላቸው እንኳን ደህና መጣችሁ እያለ ያለው ክብርና አድናቆት እየገለጸ ከውስጥም ከውጭም ለተከፈተብን ሁሉ አቀፍ ጦርነት በድል ለማጠናቀቅ ዳያስፖራው ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ መሆኑ አስታውሰዋል።

እስካሁኑ በዞኑ ለኢንቨስትመንት በሶስቱም ዘርፎች በድምሩ 389 ፕሮጀክቶች የኢንቨስትመንት ፍቃድ የተሰጣቸው ሲሆን ከእነዚህም በግብርና 131 ኢንዱስትሪ 123፣በአገልግሎት ዘርፍ ደግሞ 81 በድምሩ 335 የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች በስራ ላይ ይገኛሉ ብለዋል የዞኑ የኢንቨስትመንት ማስፋፊያ ጽህፈት አቤት ኃላፊነት አቶ ዘነበ ደበላ ።

በነዚህ ፕሮጀክቶች ባለሀብቶቹ ከ6 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በለይ መዋዕለ ነዋያቸው ለማፍሰስ ፍቃድ የተሰጣቸው ሲሆን ከዚህ ውስጥ ከ4 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር በላይ ኢንቭስት ማድረግ መቻላቸው ኃላፊው አክለው ገልጸዋል፡፡

እንደ አቶ ዘነበ ገለፃ እነዚህ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች በጊዜያዊና በቋሚነት ለ 20 ሺህ 450 ዜጎች ስራ ዕድል መፍጠር ችለዋል።

በመሆኑም አሁንም ዞኑ ውስጥ ካለው አቅምና ፍላጎት አንፃር ገና ያልተነካ እድል በግብርናው፣በማኑፋክቸሪንግ፣በሆቴልና ሎጅና በሌሎችም ዘርፎች መኖሩና አሁንም ለኢንቨስትመንት ምቹ የሆነና ዳያስፖራው በየትኛውም ሰአት ቢመጣ ለማስተናገድ በገጠርና በከተማ ከ5 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት የተዘጋጀ ሲሆን መዋዕለ ነዋያቸውን ለሚያፈሱ ዳያስፖራዎች መልካም አጋጣሚ እንደሆነም አስታውሰው የዞኑ መንግስት ለዚህም በሩ ከፍቶ እየጠበቀ መሆኑ ተናግረዋል።

በመጨረሻም ሀላፊው በድጋሚ የእናት ሀገር ጥሪን ተቀብላችሁ ወደ አገራችሁ ለመጣችሁ ውድ የቁርጥ ቀን ልጆች እንኳን ደህና መጣችሁ፣የትንቢት፣የምጣብኝ፣በላለዲ የምጣ፣ሀበይ ወገሬቱ ብለዋል።

= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!

በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *