ሀገር የገባችበትን የህልውና ጦርነት በድል እንዲጠናቀቅ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ሚናቸውን ሊወጡ እንደሚገባ የደቡብ ክልል ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ቢሮ አስታወቀ።

ቢሮው በወልቂጤ ከተማ ለተከታታይ ቀናት ሲያደርገው ነበረው ውይይትና የምክክር መድረክ ተጠናቀቀ።

ቢሮው በወቅታዊ ሀገራዊና ክልላዊ ስራዎችን ከሴክተሩ የልማት ስራዎች ጋር በማተሳሰር ለማከናወን ከዞን፣ ከልዩ ወረዳ የተወጣጡ ኃላፊዎችና የኮሌጅ ዲኖች በተገኙበት የጋራ የግምገማ መድረክ በወልቂጤ ከተማ አካሄዷል።

የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት ያስተላለፉት የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ እንዳለ ገ/መስቀል እንደገለጹት የሀገራችን ትልቁ ፈተና የሆነው ድህነት ተጠቅመው ምዕራብያውያን የከፈቱብንን ጫና ለመመከት የወልቂጤ ከተማ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ዘርፈ ብዙ ስራዎች በተለይም በከተማው የሚገኘው የስራ አጥ ቁጥር ለመቀነስ የሁሉም ባለድርሻ አካላት ርብርብ እያደረገ ነው።

የደቡብ ክልል ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር እንዳልካቸው ጌታቸው እንደተናገሩት ዜጎች የሙያ ባለቤት በማድረግ በአጭር ጊዜ ወደ ገበያ ለማሰማራት ራሳቸውን፣ ቤተሰባቸውንና ሀገራቸውን በቴክኖሎጂና በኢኮኖሚ ደረጃ ለማሳደግ የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ዘርፍ ትልቅ ሚና እየተጫወተ ይገኛል ብለዋል።

ሀገር የገባችበትን የህልውና ጦርነት በድል እንዲጠናቀቅ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ሚናቸው ሊወጡ እንደሚገባም ጠቁማል።

አክለውም የክልሉ ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ሴክተር የተሰጠውን ተልዕኮ ለማሳካትና ለክልሉ ብሎም ለሀገር እድገት የጎላ አስተዋጽኦ የሚያበረክት ብቁ ዜጋ ለማፍራት እቅዶ እየሰራ እንደሚገኝም ገልፀዋል።

የቴክኒክና ሙያ ተቋማት መንግስትና ህዝቡ የሚፈልገውን ወቅቱን የሚመጥን የህብረተሰቡን ችግር ሊፈታ የሚችል አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በመፍጠር የኢኮኖሚ ጦርነቱ መዋጋት እንዳለባቸው ተናግረዋል።

የወልቂጤ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ ኸይሩ አህመዲን በበኩላቸው የወልቂጤ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መጎብኘቱ አሁን ላይ ከሚሰሩ ስራዎች በተሻለ ሀገራዊ ወቅታዊ ሁኔታ የሚመጥን ስራዎችን ለመስራት ያግዛል ብለዋል።

በኮሌጁ ውስጥ ሀገራዊ ወቅታዊ ሁኔታ ያገናዘበ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ተናግረው ለሀገር መከላከያ ሰራዊት የተለያዩ ድጋፎችን ከማድረጋቸውም በተጨማሪ የዘማች ቤተሰቦችን አዝመራ በቴክኖሎጂ በመታገዝ ለመሰብሰብ እየተሰራ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

የጉራጌ ዞን ቴክኒክና ትምህርት ስልጠና መምሪያ ኃላፊ አቶ ፈቱ አብዶ እንደተናገሩት የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ከተሰጣቸው ተልዕኮ ጎን ለጎን የሀገሪቱን ወቅታዊ ሁኔታ የሚመጥን ስራዎችን መስራት አለባቸው ብለዋል።

በወልቂጤ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የታየው ምርጥ ተሞክሮ በሌሎችም የዞኑ ኮሌጆች ለማስፍት እንደሚሰራ አስረድተዋል።
የመድረኩ ተሳታፊዎች በጋራ በሰጡት አስተያየት በሀገራችን የተቃጣውን ጦርነት ለመመከት በየረጃው የሚገኙ ሁሉም ቴክኒክና ሙያ ተቋማት በመቀናጀት የተሻለ ስራ መስራት አለባቸው ብለዋል።

አክለውም ቴክኒክና ሙያ ተቋማት የመንግስት ካዝና ብቻ ከመጠበቅ ወጥተው የውስጥ ገቢያቸውን በማሳደግና የኮሌጁ አቅም በማሳደግ በስራ እድል ፈጠራ ላይ ትልቅ አስተዋጽኦ ማበርከት እንዳለባቸውም ጠቁመዋል።

ውይይቱ የተሻለ ተሞክሮ ያላቸውን ተቋማት ልምድ በመውሰድ ለሌሎችም ለማስፋት እንደሚያግዝና በቀጣይም የተቀራረበ የተቋማት አደረጃጀት ለመፍጠር ሚናው የጎላ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ከክልል፣ ከዞንና ከልዩ ወረዳ የተወጣጡ የስራ ኃላፊዎችና ዲኖች በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ተገኝተው የልምድ ልውውጥ አካሂደዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

  • አካባቢህን ጠብቅ !
  • ወደ ግንባር ዝመት !
  • መከላከያን ደግፍ !

በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡

Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *