በጉራጌ ዞን ብልጽግና ፓርቲ በወልቂጤ ማእከል ለሶስተኛ ዙር ሲሰጥ የነበረው የአመራሮች አቅም ግንባታ ስልጠና መጠናቀቁ የጉራጌ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት አስታወቀ።


በጉራጌ ዞን ብልጽግና ፓርቲ በወልቂጤ ማእከል ለሶስተኛ ዙር ሲሰጥ የነበረው የአመራሮች አቅም ግንባታ ስልጠና መጠናቀቁ የጉራጌ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት አስታወቀ።

የጉራጌ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አለማየሁ ገ/መስቀል በሰጡት ማጠቃለያ ሀሳብ በዞኑ “የህልም ጉልበት ለእምርታዊ እድገት” በሚል ርእስ ለ10 ተከታታይ ቀናት በተለያዩ እርሰ ጉዳዮች ላይ ስልጠና ሲሰጥ ቆይቷል።

የስልጠናው ዋና ዓላማ አመራሩ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ፣ የማህበራዊ እና የውጭ ግንኙነት ሥራዎችንና የተቋማት ግንባታ ውጥኖችን ከሀገራዊ ህልም እና ከብሔራዊነት ትርክት ጋር አስተሳስሮ የአገልጋይነት ስነ-ምግባራዊ አመራርን መሰረት ባደረገ መልኩ በውጤታማነት ተግባራዊ እንዲያደርግ ለማስቻል ነው።

ስልጠናው ብቻው ግብ ስለማይሆን ሁሉም ነገን ለመስራት ዛሬ መዘጋጀት ይጠበቅብናል ሲሉ መክረዋል።

በተጨማሪ ፓርቲውንና እና መንግስትን የሚያጠናክሩ፣ ችግር ፈቺ እና ለቀጣይ የብልፅግና ጉዞ አጋዥ የሆኑ ገንቢ ሀሳቦችን በግብዓትነት የተገኘበት መሆኑንም አቶ አለማየሁ ገልጸዋል።

በቀጣይም አመራሩ በስልጠናው ላይ በተነሱ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ በራስ ጥረት የበለጠ አቅሙን አዳብሮ በልማት፣ በመልካም አስተዳደር፣ በሰላም፣ በዲፕሎማሲ፣ በተቋምና በዴሞክራሲ ባህል ግንባታ በአጠቃላይ ሁለንተናዊ ብልፅግናን እውን ለማድረግ የሚደረገውን ትግል ይበልጥ ለማቀጣጠል አስተዋፆ ለማበርከት እንደሚጠበቅም አመልክተዋል።

በሰላምና ጸጥታ እንዲሁም የህዝቡን የደህንነት ማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ አመራሩ በቁርጠኝነት መስራት የሚያስችለውን አቅም መገንባት የሚያስችል ስልጠና እንደነበርም ጠቁመዋል።

የጋራ ትርክቶቻችን የሚጠናከሩበትን አብይ ጉዳዮች በስልጠናው መዳሰስ ተችሏል ያሉት ኃላፊው የፖለቲካ የዴሞክራሲ እምርታ ላይ ያለውን የላቀ ድርሻ ማስገንዘብ ተችሏል ብለዋል።

የአመራር ስርዓቱን በማዘመን በህዝቡ ሁለንተናዊ ህይወት ላይ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት የአመራሩን አቅም መገንባት አብይ ጉዳይ በማድረግ እየተሰራ መሆኑንም ኃላፊው ጠቅሰዋል።

ብልጽግና ፓርቲ ሰው ተኮር ነው ያሉት ኃላፊው በዚህም በበጎ ፍቃድ አገልግሎት ስራ በማከናወን 1መቶ 63 ዩኒት ደም የማሰባሰብ እና 1መቶ 80 ሺ ብር በማሰባሰብ በህክምና ላይ ያሉ ወገኖች ማሳከሚያ ተበርክቷል ብለዋል።

በቀጣይ በሁሉም መስኮች እምርታዊ ለውጥ በማሳየት የዞናችን ህዝብ ተጠቃሚ ማድረግ ይጠበቅብናል ነው ያሉት።
ለዚህ ስልጠና አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላት እና ተቋማት በሙሉ ምስጋናቸው አቅርበዋል።

በውይይቱ የተሳተፉ አካላት እንዳሉት ስልጠናው አመራሩ የሀሳብ እና የተግባር አንድነት እንድይዝ እና ዞናዊ፣ ክልላዊ ሀገራዊና አለም አቀፋዊ ጉዳዮች በቂ ግንዛቤ በመያዝ እንዲሁም የአመራሩ ክህሎት በማሳደግ ለስራ ውጤታማነቱ ከፍተኛ ሚና እንዳለው ገልጸዋል።

በቀጣይም ያገኙት ስልጠና ወደ ተግባር በመቀየር የብልጽግና ጉዞ ለማረጋገጥ እና ህብረተሰቡን በሁሉም ዘርፍ ተጠቃሚ ለማድረግ እንሰራለን ብለዋል።
በመጨረሻም የቀጣይ አቅጣጫዎች እና የአቋም መግለጫዎች በማውጣት መድረኩ ተጠናቋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *