አቶ ላጫ ይህንን ያሉት በጉራጌ ዞን ብልጽግና ፓርቲ በወልቂጤ ማእከል ለሶስተኛ ዙር ሲሰጥ የነበረው የአመራሮች አቅም ግንባታ ስልጠና ማጠቃለያ ፕሮግራም ላይ ተገኝተው ንግግር ባደረጉበት ወቅት ነው፡፡
የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ እንዳሉት ስልጠናው እንደ ሀገር ብሎም እንደ ክልል ለተጀመረው ሁለንናዊ ብልፅግና ጉዞ ዘርፈ ብዙ ጥቅም ያለው ነው።
የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ለመዳረሻችን ብልፅግና አቅም የሚሆኑ የሰው ሀይል እና የተፈጥሮ ሀብት ፀጋዎች ባለቤት ነው ያሉት አቶ ላጫ ይህንን እምቅ አቅም የተግባርና የአስተሳሰብ አንድነት በማጎልበት መጠቀም ያስፈልጋል ብለዋል።
አቶ ላጫ አክለውም እንደ ጉራጌ ዞን ህብረተሰቡን በማስተባበር በመንገድ ፣በትምህርት ፣በጤና በውሃ፣ በመብራት እና በሌሎችም ሞዴል ስራዎች መሰራቱ አንስተው ይህንን በቀጣይም አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ብለዋል።
የጉራጌ ማህበረሰብ አስተማሪ የሆኑ ባህል፣ታሪክ ፣ወግ እና እሴት ያለው ማህበረሰብ ነው ያሉት አቶ ላጫ ይህንን ለትውልድ እንዲሸጋገር መስራት እና ዞኑ ለኑሮ አመቺ ማድረግ ያስፈልጋል።
በዞኑ ያሉ ሀብቶች በአግባቡ በመጠቀም የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ይጠበቅብናል።
ሲቭል ሰርቫንቱ እና አመራሩ ግብረ ገብነትና ስነ ምግባርን በመላበስ፣ ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት፣ የመልካም አስተዳደር ችግር በመቅረፍ እና ህብረተሰቡን ልማታዊ ተጠቃሚ ማድረግ እንደሚገባ መክረዋል።
በዞኑ አሁን አንጻራዊ ሰላም ቢኖርም በተወሰኑ አካባቢዎች የሚስተዋሉ የጸጥታ ችግሮች በዘላቂነት በማስተካከል ሰላምና ጸጥታ እንዲረጋገጥ መንግስት ምላሽ ለመስጠት በትኩረት እየሰራ ሲሆን ለዚህም ሁሉም አካል የበኩሉን እንዲወጣ አሳስበዋል።
የህዝቦች አንድነት እንዲጠናከር እና ሰላምና ጸጥታ እንዲረጋገጥ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን እየተሰራ መሆኑን በመጠቆም።
አቶ ላጫ አክለውም ስልጠናው በተግባር በመቀየር በሁሉም መስኮች እምርታዊ ለውጥ በማሳየት ዞናችን የብልጽግና ተምሳሌት ማድረግ ይጠበቅብናል ነው ያሉት።
በቀጣይ የወባ በሽታ መከላከል፣የስራ እድል ፈጠራ ፣የመከላከያ ሰራዊት ምልመላ፣የደረሱ ሰብሎች በአፋጣኝ መሰብሰብ ፣የገጠር መሬት አስተዳደር ፣የከተማና የገጠር የኮሪደር ልማት ስራ ላይ በትኩረት እንዲሰራባቸው መመሪያ ሰጥተዋል።