የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንገዶች ባለስልጣን ለመንገድ ሀብት ልማትና አስተዳደር ዋና የስራ ሂደት ባለሙያተኞች የክህሎትና የአቅም ግንባታ ስልጠና በወልቂጤ ከተማ ለ3 ተከታታይ ቀን እየተሰጠ ነዉ።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንገዶች ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያ ኢንጅነር ምስጋናዉ ማቲዮስ ስልጠናዉ አስመልክተዉ እንዳሉት የምናስጠግናቸዉ የመንገድ አሴቶቻችን ቋሚ ሀብቶቻችን ሲሆኑ እነዚህ ሀብቶች በምን አይነት ሁኔታ ላይ እንደሚገኙና የድልድዬች ዲፌክታቸዉ ምንድነዉ የሚለዉ በደንብ ለይተዉ መጠገን እንዲቻል የክህሎት ስልጠና እየወሰዱ ይገኛል።
በምንሰራቸዉና በምንጠግናቸዉ መንገዶች ላይ የትራፊክ ፍሰት ቆጠራ በሚደረግበት ወቀት ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ እነዚህ ቆጠራዎች መጠንገን እንዲቻልና በአጠቃላይ በክልሉ ያሉ መንገዶችን በካርታ ወይም በጂአይኤስ ጥናት በማጥናት ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ ዲጂታላይዝድ ለማድረግና በቀላሉ ኮምፒተር ላይ ማግኘት እንዲቻልና እያንዳንዱ አካባቢዎች ያሉት መንገድ በዳታቤዝ ማስገባት እንድንችል የሚያደርግ ስልጠናም እንደሆነም አብራርተዋል።
ስልጠናዉ በዛሬ እለት በወልቂጤ ከተማ ዮናስ ሆቴል የጀመረ ሲሆን ለተከታታይ ሶስት ቀናት የሚሰጥም እንደሆነ ታዉቋል ሲል የዘገበዉ የጉራጌ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን መምሪያ ነዉ።