የዞኑ አርሶ አደር ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በግብርናው ዘርፍ የተከናወኑ ተግባራት አበረታች መሆኑን ተጠቁሟል።
በመስክ ምልከታው የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ፣ የዞኑ ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ አለማየሁ ገብረመስቀል፣ የዞኑ ምክትል አስተዳደሪና የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አበራ ወንድሙ፣ የእንደጋኝ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙሉቀን ገዙ፣ የወረዳው የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ሰሙ ዳዊትና ሌሎችም ተገኝተዋል።