የጤና አገልግሎት በፍትሃዊነት ለሁሉም ዜጎች ተደራሽ ለማድረግ ባለድርሻ አካላት ተቀናጅተው ሊሰሩ እንደሚገባ የጉራጌ ዞን ጤና መምሪያ አሳሰበ።

የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን የንቅናቄ መድረክ በወልቂጤ ከተማ ተካሔደ።

የጤና ተቋማቱ የፋይናንስ አቅም ለማጎልበት ከህብረተሰቡ የሚሰበሰበው ገንዘብ ለታለመለት አላማ እንዲውል የኦዲት ስራ ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል።

የንቅናቄ መድረኩን የመሩት የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሐመድ ጀማል ዜጎች በህመማቸው ልክ የህክምና አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን ማጠናከርና በዘርፉ ዉጤታማ ስራ መስራት ይገባል ብለዋል።

የዘርፉ ውጤታማነት በማረጋገጥ ህብረተሰቡ ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት ማግኘት እንዲችል በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች ትኩረት ሰጥተው መስራት እንደሚጠበቅባቸው አስረድተዋል።

አያይዘውም አቶ መሐመድ ዜጎች በጤና ተቋማት በፍትሀዊነት ተጠቃሚ እንዲሆኑ የተቋማቱ የፋይናንስ አቅም ለማጎልበት ከህብረተሰቡ የሚሰበሰበው ገንዘብ ለታለመለት አላማ እንዲውል የኦዲት ስራ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።

በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች በማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን ተጠቃሚ ለማድረግ የዞኑ መንግስት በየአመቱ ተጨማሪ በጀት እንደሚበጅት የተናገሩት አቶ መሀመድ የመክፈል አቅም የሌላቸው የደሀ ደሃ የሆኑ ወገኖች በማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አገልግሎት ተጠቃሚ መሆን እንዲችሉ በአግባቡ መለየት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የጉራጌ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ሸምሱ አማን በበኩላቸው ከህብረተሰቡ የሚሰበሰበው ገንዘብ ለህክምና አገልግሎት እንዲውል አስፈላጊውን ክትትል በማድረግ የጤና ተቋማት አገልግሎት ማሻሻል ይገባል ብለዋል።

እንደ አቶ ሸምሱ ገለጻ የተሰበሰበው ገንዘብ በወቅቱ ለተቋማቱ ከደረሰ በቂ መድሀኒት በማቅረብ የተገልጋይ እርካታን ለማሳደግ ያስችላል ብለዋል።

ከማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን ገንዘብ አመላለስ ጋር በተያያዘ በአንዳንድ ወረዳዎች የሚስተዋሉ ደረሰኝን በወቅቱ ያለመመለስ፣ አዳዲስ አባላት በሚፈለገው ደረጃ ያለማፍራት፣ የነባር አባላት የአባልነት መታወቂያ ያለማደስ እንዲሁም የጤና ተቋማት ወጪ በወቅቱ ያለመክፈል ችግሮች ለመፍታት በትኩረት መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

ጤናው የተጠበቀና አምራች ማህበረሰብ ለመፍጠር ዘርፉን ማጠናከር ይገባል ብለዋል።

በመድረኩ የተገኙ አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች በሰጡት አስተያየት በማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን አፈጻጸም ላይ ያለዉን ጥንካሬ በማስቀጠልና የሚስተዋሉ ዉስንነቶችን በመቅረፍ በዘርፉ የተሻለ ስራ ለመስራት ከመቼዉም ጊዜ በላይ ቅንጅታዊ አሰራር ማጠናከር ይገባል ብለዋል።

በ2013 በጀት አመት ህብረተሰቡ በማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን በሚፈለገው መጠን ተጠቃሚ ማድረግ አለመቻሉ የተናገሩት አስተያየት ሰጪዎቹ ለዚህ ደግሞ የተሰጠው ትኩረት አነስተኛ እንደነበር ገልጸዋል።

በመሆኑም ክፍተቶቻቸው ለይተው በመሙላት ህብረተሰቡ ተጠቃሚ ለማድረግ የንቅናቄ መድረኩ ልምድ ለመውሰድና ግንዛቤ እንዲጨብጡ አስችሏቸዋል።

በመድረኩ የ2014 ዓመተ ምህረት የማጤመ የንቅናቄ እቅድ ቀርቦ ውይይት ሰፊ በማድረግ በ2013 የተሻለ አፈጻጸም የነበራቸው ወረዳዎችና ከተሞች እውቅና በመስጠት ተጠናቋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

  • አካባቢህን ጠብቅ!
  • ወደ ግንባር ዝመት!
  • መከላከያን ደግፍ!

በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *