በከተማው ህብረተሰቡና መንግስት በመቀናጀት የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች እየተከናወኑ እንደሆነ የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ።

በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ በህብረተሰቡና መንግስት ትብብር እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎች የመስክ ምልከታ ተደርጓል።

የጉራጌ ዞን ኢንቨስትመንት እና ኢንድስትሪ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ናስር ሀሰን እንደገለፁት በአመቱ በከተማው በግሉ ዘርፍ፣በኮንስትራክሽን፣በሆቴልና ቱሪዝም፣በኢንቨስትመንት እና በሌሎች ዘርፎችም መነቃቃት ታይቷል ነው ያሉት።

ለአብነትም በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ መሬት ከተሰጣቸው ውስጥ አብዛኞቹ ወደ ስራ እየገቡ ሲሆን ይህም ተወላጅ ባለሀብቱ ወደ አካባቢው ገብቶ የመስራት ፍላጎት እየጨመረ መሆኑ አመላካች መሆኑን አቶ ናስር ሀሰን ጠቁመዋል።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ እንዳለ ስጦታው በከተማው ህብረተሰቡ፣ባለሀብቱ እና መንግስት በመቀናጀት በመንገድ፣በትምህርት ፣በሆቴልና ቱሪዝም ፣በኢንቨስትመን በአጠቃላይ በከተማ መሰረተ ልማት ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ስራዎች ሲሰሩ እንደነበር አመላክተዋል።

አያይዘውም በ3ቱም ክፍለ ከተሞች ከዚህ በፊት አዳሪ የነበሩ ፕሮጀክቶች በማስጨረስ በ2016 ደግሞ 14ቱ ፕሮጀክቶች እንዲጠናቀቁ በርካታ እንቅስቃሴ መደረጉ ገልጸው በሌሎች በተሰሩ ተግባራት አመርቂ ለውጦች ማምጣት መቻሉ አብራርተዋል።

አቶ እንዳለ አክለውም ዛሬ ከታዩት በግል ባለሀብቶች ብቻ ከ2መቶ 45 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ እያደረጉ ሲሆን ለአብነትም መንግስት በመንገድ ብቻ ከ6 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ተደርጎ የመንገድ ከፈታ መደረጉ ተናግረዋል።

እነዚህም የልማት ስራዎች የከተማዋ የልማት እድገትና የህብረተቡ ተጠቃሚነትን ያረጋገጡ ናቸው ያሉት አቶ እንዳለ የህብረተሰቡ፣ የማህበረሰቡ እና የመንግስት አቅም አቀናጅቶ በመጠቀም በ2017 የበለጠ ስራ ለመስራት አቅደን እየተንቀሳቀስን ነው ብለዋል።

የወልቂጤ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ስራ አስከያጅ አቶ ይብጌታ ንዳ እንዳሉት በከተማው በማቺንግ ፈንድ የሚሰሩ ስራዎችም ከሌላ ጊዜ አንጻር በቂ በጀት ተመድቦ በዘርፉ አመርቂ ለውጦች እየታዩ እንደሆነና ከ20 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ተደርጎ መጠናቀቃቸው አክለዋል።

በአመቱ በህብረተሰቡ፣በመንገድ ፈንድ እና በሴተፍትኔት ትብብር 20 ኪሎ ሜትር የጠጠር መንገድ ስራ የተሰራ ሲሆን በቀጣይ በሌሎች የአስፋልትና የኮብል ንጣፍ ስራዎች ላይ በትኩረት እንደሚሰራ ገልጸዋል።

ከመጸዳጃ ቤት ግንባታ፣የኮብልና የጠጠር ንጣፍ ስራ፣የውሃ እና የመብራት ዝርጋታ፣በሴፍቲ ታንክ ዘርፎች ላይ እየተሰሩ ያሉ ስራዎቸ ውጤታማ ሲሆኑ በመሬት አቅርቦት ደግሞ በማህበርና በሊዝ 450 ሰዎች የመኖረያ ቤት ተጠቃሚ መደረጋቸው አብራርተዋል።

የከተማው የገቢ አሰባሰብ በየአመቱ እየጨመረ መሆኑና ይህም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የገለጹት አቶ ይብጌታ በከተማው እየተስተዋል ያለው የቆሻሻ አወጋገድ ችግር እንዲቀረፍ ህብረተሰቡ የበኩሉን እንዲወጣ አሳስበዋል።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ግርማ ንቅበሸዋ የካፒታል ፕሮጀክቶች በጊዜ፣በመጠን እና በጥራት ተሰርተው ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገለጸዋል።

የመንገድ ከፈታ፣የጠጠር ንጣፍ፣የትምህርት፣የሆቴልና ቱሪዝም ፣የኮንስትራክሽንና ግንባታ፣የመሬት አቅርቦት፣የካፒታል ፕሮጀክቶችና የመሰረተ ልማት ስራዎች የበለጠ እንደሚጠናከሩ ገልጸዋል።

በኢንቨስትመንት በበጎ አደራጎትና በሁሉም መሰረተ ልማቶች የተጀማመሩ ስራዎች አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ያሉት አቶ ግርማ ከተማዋ በሁሉም ዘርፍ ውጤታማ ለማድረግ ህብረተሰቡ እና መንግስት ተቀናጅተው መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

በከተማው አግኝተን ያነጋገርናቸው የህብረተሰብ ክፍሎች እንደገለፁት በወልቂጤ ከተማ በሚከናወኑ አዳዲስ የመሰረተ ልማት ስራዎች ህብረተሰቡ ተጠቃሚ እያደረጉ መሆኑ ተናግሯል።

እየተሰሩ ያሉ የካፒታል ፕሮጀክት ስራዎች በጥራት እና በፍጥነት ተሰርተው ለአገልግሎት ክፍት መደረጋቸው የከተማው እድገት እንዲሻሻል እያደረጉ በመሆኑ ተጠናክረው እንዲቀጥሉ አስታውቀዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *