በወልቂጤ ከተማ የህብረተሰቡ የኑሮ ውድነት ጫና ለመቀነስ የተጀመረው ከሰንበት እስከ ሰንበት ገበያ ተሞክሮ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የኢፌድሪ ንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ገለፀ።

ከፌዴራል ፣ከአማራ ክልልና ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የተዉጣጡ ባለ ድርሻ አካላቶች የወልቂጤ ከተማ የሰንበት ገበያ የንግድ እንቅስቃሴ ጎብኝተዋል።

የጉራጌ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ሀላፊ አቶ መላኩ ብርሃኔ እንዳሉት ከሰንበት እስከ ሰንበት ገበያ የኑሮ ዉድነትን ለመቀነስ በምንሰራቸዉ ስራዎች የህብረተሰቡ ፍላጎት እያደገ እንዲመጣ አስችሏል።

የግብርና ምርትና ምርታማነት እያደገ በመጣ ቁጥር ገበያዉ ላይ ያለዉ አቅርቦት እየጨመረ የሚመጣ እንደሆነም ተናግረዉ በሰንበት ገበያዎች የሌማት ቱሩፋት ፣ተደራጅተዉ በሚሰሩ ወጣቶች እንዲሁም በኢንቨስተሮችና አርሶአደሮች የሚመረቱ የተለያዩ ምርቶች በስፋት ይቀርባሉ ብለዋል።

የሸማቹ ማህበረሰብ ፍላጎት ለማሟላት የተለያዩ ምርቶች በጥራትና በብዛት እየቀረቡ እንደሆነም ተናግረዉ በዞኑ ከ23 በላይ የሰንበት ገበያ የተቋቋመ መሆኑም አብራርተዋል።

ሸማቹና አምራቹን በማገናኘት ዉጭ ላይ ያለዉ ዋጋ ከፍተኛ ሲሆን ሰንበት ገበያ ላይ በሚሸጡ ምርቶች ላይ በጣም ቅናሽ እንደሆነም አመላክተዋል።

በወልቂጤ ከተማ በዛሬዉ ዕለት ከፌዴራል ፣ ከድሬዳዋና ፣ከአማራ ክልል የመጡ እንግዶች በሰንበት ገበያ ተገኝተዉ ልምድ ልዉዉጥ ያደረጉ ሲሆን በዚህም የልምድ ልውውጥ ማድረጋቸው አቶ መላኩ አብራርተዋል።

በወልቂጤ ከተማ ሰንበት ገበያ በቀረቡ ምርቶች ተዛዙረዉ አይተዉ የተደነቁበት እንደሆነም ተናግዋል።

በልምድ ልዉዉጡ የተገኙት ከንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አቶ ሁንዴ በላይ እንዳሉት በበጀት አመቱ እንደ ሀገር ያለዉን የንግድ ዘርፍ በምን ደረጃ ላይ እንዳለ ለመደገፍ፣ የሱፐርቪዥንና የልምድ ልዉዉጥ ለማድረግ ቲም ተደራጅቶ ወደ ክልሎች ተሰማርተዉ እየሰሩ እንደሆነም አመላክተዋል።

ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ፣ኦሮሚያ እንዲሁም በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በዛሬዉ ዕለት የወልቂጤ ከተማ ሰንበት ገበያ ተዛዙረዉ የጎበኙ ሲሆን በዚህም በገበያዉ እየቀረቡ ያሉ የፍጆታ ምርቶች ከመደበኛዉ ገበያ በተሻለ ሁኔታ በተመጣጣኝ ዋጋ ለሸማቹ ማህበረሰብ እየቀረበ እንደሆነም ተመልክተናል ብለዋል።

በልምድ ልዉዉጡ ከአማራ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ የኢንስፔክሽን ባለሙያ አቶ ይበልጣል ብርሀኑና ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ባለሙያ አቶ ጌቱ ታሪኩ በሰጡት አስተያየት በወልቂጤ ከተማ በሰንበት ገበያ ማዕከል የሚቀርቡ አትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም የኢንዱስትሪ ምርቶች የቀረቡ ሲሆን በንግድ ጽህፈት ቤት በኩል በእነዚህም ምርቶች ዋጋ ተተምኖ መቅረቡ የኑሮ ዉድነት ከማረጋጋት ጋራ የሚኖረዉ ሚና ከፍተኛ እንደሆነም አመላክተዋል።

የወልቂጤ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ሙባሪክ ዘይኑ እንዳሉት
በከተማዉ የኑሮ ዉድነቱን ለማረጋጋት ለሸማቹ ማህበረሰብ በተመጣጣኝ ዋጋ የተለያዩ የፍጆታ ምርቶች እየቀረቡ እንደሆነም ተናግረዉ በከተማዉ በዛሬዉ ዕለት ለጉብኝት የመጡ እንግዶች የሰንበት ገበያ ምርት አቅርቦትና የኑሮ ውድነት ለመቀነስ እየተደረገ ያለው ጥረት ማድነቃቸዉና እንደ ከፍተት የተመለከቱት የጎዳና ላይ ህገወጥ ንግድ መከላከል እንደሚገባ እንዳመላከቱም አስረድተዋል ሲል የዘገበዉ የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን መምሪያ ነዉ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *