ሰኔ12/2015 ዓ.ም
በበጀት አመቱ ከደንበኞቹ ከ80 ሚሊዮን ብር በላይ ማስቆጠብ መቻሉን በኦሞ ባንክ የወልቂጤ ከተማ ቅርንጫፍ አስታወቀ ።

ቀልጣፋና ዉጤታማ የባንክ አገልግሎት ለደንበኞች ለማቅረብ በትኩረት እየሠራ መሆኑን ተጠቁሟል።

በ2015 ዓ.ም ከደንበኞችሁ ከ80 ሚሊየን ብር በላይ ፣ወልቂጤ ኦሞ ባንክ ማስቆጠብ ተችሏል ።

የወልቂጤ ኦሞ ባንክ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ አቶ ደመቀ ይመር እንዳሉት የማይክሮ ፋይናንስ ተቋም ወደ ኦሞ ባንክ ከተሸጋገረ በኋላ አሰራሩን በማዘመን የተሻለ አገልግሎት ለደንበኞች ለመስጠት በትኩረት እየሠራ ይገኛል።

ተጠቃሚዉ ህብረተሰብ በሚያማክለዉ ስፍራ ህንፃ በመከራየት በባንክ ደረጃ የሚመጥን የቁሳቁስና የሰው ኃይል የማደራጀትና ሌሎች የቅድመ ዝግጅት ስራ በመከናወን ወደ ተግባር መገባቱን ገልፀዋል።

የተቋሙ ማደግ ከብድር ስርጭትና ከቁጠባ አሰባሰብ አንፃር ፈጣንና ወቅቱን የሚመጥን ተግባር ለማከናወን አጋዥ ነው ብለዋል።

ሰው ካለው ላይ በመቆጠብ ነገ የተሸለ ለማድረግ የቁጠባን መሠረታዊ ፅንሰ ሀሳብ ላይ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅተው እየሠራን ነው ብለዋል።

በተቋሙ 21ሺህ የቁጠባ ደንበኞች እንዳሉና ከ33 ሚሊየን ብር በላይ የተረጋጋ ቁጠባ ማስቆጠብ መቻሉን የገለፁት አቶ ደመቀ በ2015 ዓ.ም በጥቅሉ ከ80 ሚሊየን ብር በላይ ማስቆጠብ መቻሉን ገልጸዋል።

በቀጣይ ከተጣራ ቁጠባ አሰባሠብና ከብድር አመላለስ ምጣኔ አንፃር ብሄራዊ ባንክ ባስቀመጠው ስታንዳርድ መሠረት በመፈፀም የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ወደ ህብረተሰቡ በተሻለ መልኩ የመቅረብ ስራ ይሰራል ብለዋል።

ባንኩ የመንግስት ሰራተኞች፣ አርሶ አደሮች ፣ተማሪዎችና ሌሎችም የህብረተሰብ ክፍሎችን አዲስ ደንበኛ የማፍራት ስራ መሠራቱን አብራርተዋል።

በወልቂጤ ባንክ አዲስ የቁጠባ ደብተር ሲከፍቱ ካኘናቸው መካከል ተማሪ ትግስት ከተማ ፣ተማሪ ሳረት አሚር እና ተማሪ ይገርማል በንቲ በጋራ በሰጡት አስተያየት ተቋሙ ወዳሉበት ስፍራ በመመጣት ስለ ቁጠባ ግንዛቤ በመፍጠር ቀልጣፋ አገልግሎት በማግኘታው መደሰታቸውን ገልጸዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን መንግሥት ኮሚኒኮሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *