የመንግስት ፋይናንስ አስተዳደርና የቁጥጥር ስርዓት በማሻሻል የዞኑን ምጣኔ ሀብትና እድገት ማፋጠን እንደሚገባ የጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ አስታወቀ።

የጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ፋይናንስ የበጀት ድጋፍ፣ በመንግስት ፋይናንስ አስተዳደርና ቁጥጥር አፈጻጸም ዙሪያ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ውይይት በወልቂጤ ከተማ አካሄዷል።

የጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ኃላፊ አቶ አብዶ ሀሰን እንደገለጹት በ2015 በጀት ዓመት ለዞኑ የተመደበለት 5 ነጥብ 26 ቢሊዮን ብር በግልጽና በፍትሃዊነት በመሸንሸን መደበኛና የካፒታል ፕሮጀክቶችን ለማሳካት ሰፊ ርብርብ ተደርጓል።

የመንግስት ፋይናንስ አስተዳደርና የቁጥጥር ስርዓት በማሻሻል የዞኑን ምጣኔ ሀብትና እድገት ማፋጠን እንደሚገባ ያስታወቁት የመምሪያው ኃላፊ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ተቀናጅቶ ውጤታማ የፋይናንስ ስራዎች መሰራት አለባቸው ብለዋል።

የኦዲቲግ፣ የግዢና የንብረት አስተዳደር፣ የመንግሥት ክፍያና ሂሳብ አስተዳደር ስራዎች ላይ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን በማረምና የፋይናንስ መመሪያና ደንቦችን በመከተል ውስን የህዝብና የመንግስት ሀብት ለታለመለት ዓላማ ብቻ እንዲውል መደረግ አለበት ብለዋል።

ከግብዓት፣ ከብድር፣ ከህትመትና ከውዝፍ ጡረታ ከ360 ሚሊዮን ብር በላይ ከዞኑ ወጪ መርጃ እንደተቆረጠ ያመላከቱት አቶ አብዶ ጉድለቱን በጋራ ገቢ በመሸፈን ስራዎች እንዲሰሩ ተደርጓል ብለዋል።

የተራድኦ ድርጅቶች የስራ እንቅስቃሴ ውጤታማ እንዲሆኑ ሴክተሩ የሚያደርገው ክትትል፣ ድጋፍና ቁጥጥር ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ያሳሰቡት ኃላፊው በበጀት ዓመቱ የተጀመሩ ፕሮጀክቶች ተጠናቀው አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ መደረግ አለበት ተብለዋል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት በአፈፃፀም ሂደት የሚስተዋሉ ክፍተቶች በማረም የመንግስትና የህዝብ ሀብት እንዳይባክን የበኩላቸውን እንደሚወጡ ገልፀዋለል።

የኦዲት ግኝት ለማስመለስ የመራሩ ሚና የጎላ መሆኑንና የካሽ እጥረት ለመቅረፍ ዞኑ የሚያመነጨው ገቢ በአግባቡ መሰብሰብ እንደሚገባ የተናገሩት አስተያየት ሰጪዎች የልማት ስራዎችንና ግዢዎች በወቅቱ ተፈፃሚ እንዲሆኑ በጀት በጊዜ የሚጸድቅበት ሁኔታ መፈጠር አለበት ብለዋል።

በፕሮጀክት ግንባታዎች ቁጥጥር፣ በኦዲት፣ በጫረታና ግዢ፣ በንብረት አያያዝ፣ በክፍያና ሂሳብ አስተዳደር፣ በበጀት አጠቃቀም፣ በድጋፍና ክትትል ስራዎች ላይ ትኩረት ሰጥተው እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

የዞኑ የዋና ዋና የስራ ክፍሎች፣ የተመረጡ ወረዳና ከተማ አስተዳደሮች የ9 ወራት እቅድ አፈፃፀማቸውን አቅርበው ሰፊ ውይይት መደረጉን የዘገበው የጉራጌ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *