መጋቢት 20/2015 ዓ/ም

የጉራጌ ዞን ማዕከል አመራሮች “ድሎችን ማፅናትና ፈተናዎችን መሻገር” በሚል መሪ ቃል ሲደረግ የነበረው የውይይት መድረክ ተጠናቋል።

መድረኩም አጠቃላይ ሀገራዊ፣ክልላዊ እና ዞናዊ ነባራዊ ሁኔታዎችን የገመገመ መሆኑ ተገልጿል።

የደቡብ ክልል የስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ቢሮ ኃላፊ አቶ ቢረጋ ብርሀኑ እንደገለፁት ባለፉት አራት የለውጥ አመታት መሠረታዊ ሊባሉ የሚችሉ ስኬቶች እንደሀገር ተመዝግበዋል። በፖለቲካው በኢኮኖሚው እንዲሁም በማህበራዊ ዘርፍ የተመዘገቡ ለውጦችን የአመራሩን የተግባር እና የአመለካከት አንድነት በመጠበቅ ማስቀጠል ይገባል ሲሉ ገልፀዋል።

አቶ ቢረጋ አክለውም በተግባር አፈፃፀም ሂደትም የሚስተዋሉ ተግዳሮቶችና ስህተቶችን በሰከነ መንፈስ እያረሙ መሄድ እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል።

በተጨማሪም በዞኑ ማዕከል ወልቂጤ የተፈጠሩ ችግሮችን አመራሩ ከህዝቡ ጋር ተቀራርቦ በውይይት መፍታት እንደሚያስፈልግ ኋላፊው ጠቁመዋል።

የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ በበኩላቸው እንደሀገር የተመዘገቡ ለውጦች ለማህበረሰቡ በማሳወቅ ጉድለቶችን ተረባርቦ መፍታት ያስፈልጋል።

እንደዞን ከዚህ ቀደም ከነበረበት አለመረጋጋት በአመራሩ እና ህዝባችን ጥረት አንፃራዊ ሰላም መታየቱን ገልፀዋል።

እንደ አቶ ላጫ ገለፃ አመራሩ የህዝቦችን አንድነት በማስጠበቅ የህዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች መፍታት እንዳለበት ገልፀዋል።

የጉራጌ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መሰለ ጫካ በበኩላቸው የዞኑን የአመራር የአቅም ጉድለቶችንና ውስጣዊ ብልሽቶችን በማረም የተጀመረው ሀገራዊ ለውጥና እድገት ማስቀጠል እንደሚገባ ገልፀዋል።

አቶ መሠለ አያይዘውም እንደ ዞን ህብረብሄራዊ አንድነትን እንዲጠናከርና ወንድማማችነት እንዲጎለብት በትኩረት እንደሚሰራ ገልፀዋል።

የብልፅግና ፓርቲ አባላትንና አመራሩን በተገቢው የማጥራትና አቅም የማጎልበት ስራዎች በመስራት የዞናችንን ህዝብ የሰላም እና የመልካም አስተዳደር ጥያቄ የመፍታት ስራ እንደሚሰራ ጠቁመዋል።

በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ ከተሳታፊ አመራሮች ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ከመድረኩ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል።

በመረጃ ምንጭነት ገፃችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን!
እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *