4 ቢሊዮን ብር አክሲዮኖች ለሽያጭ ማቅረቡንና ከዚህም የ2 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ለአዲስ ባለ አክሲዮኖች ሺያጭ ማዘጋጀቱን ኦሞ ባንክ አስታወቀ፡፡

የኦሞ ባንክ የወልቂጤ ዲሰትሪክት የስራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች፣ የወረዳና ከተማ አስተዳደር የዲስትሪክቱ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጆችን ያሳተፈ የአክሲዮን ሺያጭ መርሀ ግብር በወልቂጤ ከተማ በዛሬው እለት አካሂዷል፡፡

የደቡብ ክልል ኦሞ ባንክ ምክትል ስራ አስኪያጅ እና የብድርና ቁጠባ ዘርፍ ኃላፊ አቶ እጅጉ ኢንጌሱ የአክሲዮን ሺያጭ መርሀ ግብር ባስጀመሩበት ወቅት እንደገለጹት ኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ከዚህ በፊት ለ 25 ዓመታት ለበርካታ ዜጎች የብድርና ቁጠባ ተጠቃሚ ማድረጉን አስታዉሰዋል ፡፡

ባለፈው አመት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ያስቀመጠውን መሰፈርት በማሟላት ሰኔ 14/ 2014 ዓ.ም የባንክ አግልግሎት መስጠት እንደሚችል ከተገለጸበት ጊዜ ጀምሮ የቅድመ ዝግጅት ሳራዎችን ሲያከናዉን ቆይቶ አሁን ላይ የአክሲዮን ሺያጩን በይፋ መጀመሩን ገልጸዋል፡፡

አራት ሚሊዮን አክሲዮኖችን በተመረጡ አራት ባንኮች ለሺያጭ መቅረቡን የተናገሩት አቶ እጅጉ ኢንጌሱ 2 ነጥብ 3 ቢሊዮን ለአዲስ ባለ አክሲዮኖች መዘጋጅቱን ከዚህም እስካሁን 1 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር የአክሲዮን ሺያጭ ውል መፈጸሙን ገልጸዋል ፡፡

እንደ አቶ እጅጉ ኢንጌሱ ገለጻ የወልቂጤ ዲስትሪክት ኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ በነበረበት ወቅት ከክልሉ ካሉ 19 ዲስትሪክቶች በአፈጻጸም ግንባር ቀደም እንደነበረና አሁንም ወደ ባንክ ሲሸጋገር ደንበኞቹን የበለጠ ተጠቃሚ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ እንደሆነና አሁን አክሲዮኑን በመግዛት የባንኩ ባለቤት መሆን እንዳለባቸው መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

የወልቂጤ ኦሞ ባንክ ስራ አስኪያጅ አቶ መለሰ ጸጋዬ እንደተናገሩት የአክሲዮን ሺያጭ በአራት ባንኮች በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፤በኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ፤ በአቢሲንያ ባንክ እና ኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ቅርንጫፎች ኦሞ ባንክ ውል ስለተፈራረመ መስፈርቱን የሚያሟላ ማንኛውም አካል ሄዶ መግዛት እንደሚችል አመላክተዋል፡፡

የኦሞ ባንክ እስካሁን ባደረገው ሰፊ እንቅስቃሴ ከ 12 ቢሊየን 7 መቶ 12 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ሀብት ያለው በመሆኑ የአክሲዮን ገዢዎች የተሻለ ተጠቃሚ ያደርጋቸዋል ብለዋል አቶ መለሰ ጸጋዬ ፡፡

የአክሲዮን ሺያጩ በአንድ ጊዜ መቶ ፐርሰንት መግዛት ላማይችሉ 25 ፐርሰንት ቅድሚያ በመክፈልና ቀሪውን በአራት ዓመት ጊዜ ውስጥ መክፈል እንዲችሉ እድል ማመቻቸታቸውን ያስረዱት አቶ መለሰ ጸጋዬ በዛሬው እለት ከተቋሙ ጋር ለረጅም አመታት አብረው ሲሰሩ ለነበሩ አመራርና ባለሞያዎች ከ 50 ሺህ እስክ 100 ሺህ ብር የሚያወጣ የአክሲዮን ሺያጭ ውል መፈጸሙን ገልጸዋል፡፡

ኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ በከጠርና በከተማ ለሚገኙ ሞዴል ለሆኑ አርሶ አደሮች ፣ ኢንተርፕራይዞች፣ የሴቶችና የወንዶች የወጣቶች ማህበራትና ለሌሎችም በተሻለ መልኩ አገልግሎት እየሰጠ እንደነበር የጠቆሙት አቶ መለሰ ጸጋዬ አሁን በባንክ ደረጃ ሲሸጋገር ደንበኞቹን የተሻለ ተጠቃሚ እንደሚያደርግ አመላክተዋል፡፡

መርሀ ግብሩ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት ኦሞ የካበተ የፋይናንስ ልምድ ያለው የኦሞ ባንክ አክሲዮን በመግዛት የባንኩ ባለቤት በመሆናቸው ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማቸውና በቀጣይ ባንኩን የበለጠ ዉጤታማ ለማድረግ አንደሚሰሩ ተናግረዋል።

ኦሞ ባንክ በ25 አመት በዘርፉ ያፈራው የሰለጠነ የሰዉ ኃይል እና ከ5.7 ሚሊዮን በላይ የቁጠባ ደንበኞች እንዲሁም ከ1.3 ሚሊዮን በላይ የብድር ደንበኞችን እያስተዳደረ የሚገኝ ባንክ በመሆኑ ለባንኩ ቀጣይ ውጤታማነት ከፍተኛ ድርሻ እንዳለው አስተያየት ሰጪዎቹ ተናግረዋል ።

የኦሞ ባንክ አክስዮን መግዛት ለትውልድ የሚተርፍ ቅርስ ከመያዝም በላይ በየዓመቱ የሚያተርፍ የማይነጥፍ ሀብት ምንጭ መሆኑንም ተናግረዋል ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *