4ኛዉ ዙር የኬሮድ ታላቁ ሩጫ የማህበረሰባችን አብሮነትን ሰላም ፍቅርን የወንድማማችነትና የእህትማማችነት ያጠናከርንበት መሆኑ የጉራጌ ዞን አስተዳደር አስታወቀ።


4ተኛው ዙር የኮሮድ ታላቁ የጎዳና ላይ ሩጫ በወልቂጤ ከተማ በደማቅ ተካሄዷዋል።

የኢፌዴሪ ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት በፕሮግራሙ ተገኝተዉ እንዳሉት የጉራጌ ዞን በከፍተኛ መረጋጋትና ሰላም የሰፈነት ሲሆን መላዉ ህዝብና ወጣቱ ለሰላም ቅድሚያ በመስጠት ከዞኑና ከከተማ አስተዳደር ጋር በመቆም ከተማዉ ወደ ልማት በማስገባት ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴ እየተካሄደበት ይገኛል።

ለሀገር ግንባታና ሰላም ከተማ አስተዳደሩና ወጣቱ ህብረተሰብ እጅ ለእጅ ተያይዘዉ እያደረጉት ላለዉ አጠቃላይ እንቅስቃሴ አድንቀዉ የጉራጌ ማህበረሰብ ብርቱና ጥሮ አዳሪ ሀገሩን አክባሪና በሚሄድበት ቦታ ተቻችሎ የሚኖር ማህበረሰብ እንደሆነም አብራርተዋል።

የጉራጌ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ አበራ ወንድሙ በኬሮድ ታላቁ ሩጫ ዉድድሩ ተገኝተዉ እንዳሉት የኬሮድ የልማትና የስፖርት ማህበር ለኢትዮጵያ ሰላም እንሩጥ በሚል መሪ ቃል ለ4ኛ ጊዜ በወልቂጤ ከተማ ያካሄደው የ15 ኪሎ ሜትር ሩጫ የማህበረሰባችን አብሮነትን ሰላም ፍቅርን የተሰበከበት የወንድማማችነትና እህትማማችነት እንዲሁም አንድነትን የተጠናከረበት እንደሆነ አብራርተዋል።

የዞኑ ማህበረሰብ በስፓርት ልማት ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንዲሁም ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳዎቹ ከፍተኛ በመሆኑን ለስፖርት ልማቱ ልዩ ትኩርት በመስጠት እየተሰራበት ይገኛል ብለዋል።

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተሳታፊና ተወዳዳሪ የሆነ የወልቂጤ ከተማ እግር ኳስ ክለብ፣ የወልቂጤ ቅርጫት ኳስ ክለብና የዘቢዳር አትሌቲክስ ክለቦች በማህበረሰቡ ዘንድ ተወዳጅ ቢሆኑም አደረጃጀቶቹንና አሰራሮቹን በማዘመን ህዝባዊ መሰረት በማስያዝ የበለጠ በመጠናከር እንደሚሰራ ተናግረዋል።

በሀገራችን ብቁ አትሌቶችን በማፍራትና ተፎካካሪ በመሆን በአለም አደባባይ ደምቀንና ጎልተን እንድንወጣ የኬሮድ ታላቁ ሩጫ የበኩሉን አስተዋጽኦ እያበረከተ የሚገኝ እንደሆነም አመላክተዉ የኦሎምፒክ ሻምፒዮና ኮማንደር ሰለሞን ባረጋ ፣ሙክታር እድሪስና ሌሎችም በርካታ አትሌቶች ሞዴልና የሀገር ባለዉለታዎቻች ናቸዉ ብለዋል።

ዉድድሩን ለመታደም ወደ ዞኑ የመጡ የማህበረሰብ ክፍሎች ዞኑ ለማልማት ለኢንቨስትመንት፣ ለመዝናናት፣ ለመጎብኘት ፣ ጥናትና ምርምር ለማድረግ ምቹ ከመሆኑም አልፎ የተለያዩ የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ ቱባ ባህሎቻችንና ዕሴቶቻችን ማለትም ጥንታዊ ገዳማትና አብያተ ክርስቲያናት፣ ታሪካዊ መስጅዶች፣ ሰንሰለታማ ተራሮች፣ ህይቆች፣ ፓርኮችና ዋሻዎች ሌሎችም ዕሴቶች በብዛት ይገኛሉ ብለዋል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ዘሪሁን እሸቴ እንዳሉት ስፖርት የሰው ልጆችን አዕምሮ ለማሳደግና በህዝቦች ዘንድ ትስስር የሚፈጥር መሆኑን ገልፀው የኬሮድ የጎዳና ላይ ሩጫ ከውድድር ባለፈ የሰላምና የመቻቻል መድረክ ነው ብለዋል።

በክልሉ በተለያዩ አከባቢዎች ስፖርትን በማስፋፋት ህብረተሰቡ በስፖርት ጤናውን እንዲጠብቅና አምራች ዜጋ እንዲፈጠር በትኩረት እየተሰራ እንደሆነም አብራርተዋል።

የወልቂጤ ከተማ ከንቲባ አቶ እንዳለ ስጦታዉ እንዳሉት በወልቂጤ ከተማ ለ4ተኛ ጊዜ የተዘጋጀው የ15ኪሎ ሜትር የኬሮድ የጎዳና ላይ ሩጫ ዉድድር ሁሉንም ማኅበረሰብ ያሳተፈና ለሀገርችን ተተኪ አትሌቶች ለማፍራት የሚያግዝ እንደሆነም ተናግረዋል።

በርካታ ቁጥር ያላቸዉ ታዋቂና ወጣት አትሌቶች ያሳተፈዉን የኬሮድ ታላቁ ሩጫ የከተማዉን ገጽታ በመቀየር ረገድ ትልቅ አስተዋፆ እያበረከተ ይገኛል ብለዋል።

በከተማዉ የሚገኙ ወጣቶችና አጠቃላይ ማህበረሰብ እንግዶችን በተገቢዉ ተቀብሎ በማስተናገድ ረገድ ላደረጉት ከፍተኛ አስተዋፆ በከተማ አስተዳድር ስም ምስጋና አቀርባስሁ።

ታላቁ የኬሮድ ሩጫ ዉድድር በከተማዉ መካሄዱ የማህበረሰቡ ባህል እንዲሁም የቱሪዝም ሀብቶች እንዲጎበኙ ያደረገና ሌሎችም እሴቶቻችን የበለጠ ጎልተዉ እንዲተዋወቁ የአንበሳውን ድርሻ እንደሚወጡም ይታወቃል፡፡

አትሌትና አሰልጣኝ ተሰማ አብሽሮ በበኩሉ ኬሮድ አድማሱን እያሰፋ በሌሎችም ዞኖችና ክልሎች የሩጫዉን ዉድድር የሚያስቀጥልም እንደሆነም አስታዉቀዋል።
በዛሬው እለት በድምቀትና በሰላማዊ ሁኔታ የተካሄደው የጎዳና ሩጫ አስተዋጽኦ ላደረጉ ተቋማትና ድርጅቶች እንዲሁም ግለሰዎች መስጋናቸውን አቅርበዋል።

 በመጨረሻም የውድድሩ አሸናፊዎችና ሽልማት በ15 ኪሎ ሜትር

በሴቶች
1ኛ መብራት ግደይ (የወርቅ ሜዳሊያና 100 000 ብር )
2 ኛ መቅደስ ሽመልስ ( የብር ሚዳሊያና 50000)
3ኛ ጉተን ሽንቆ (የነሓስ 25000)

  @ በወንዶች የ15 ኪሎ ሜትር ሩጫ 

1ኛ ጨምቤሳ ደበላ ( የወርቅ ሜዳሊያና 100000ብር)
2ኛ ዘነበ አየለ ( የብር ሜዳሊያና50000) ብር
3ኛ ጃክሳ ታደሰ (የነሀስ ሜዳሊያና 25000) ብር

በማህበረሰብና በፓራሊምክስ ዉድድሮች ከ1ኛ እስክ 3ኛ ለወጡ ወንዶችና ሴት ተወዳዳሪዎች ከ2 ሺህ እስከ 5 ሺህ ብር የገንዘብና የሜዳሊያ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል ሲል የዘገበዉ የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ነዉ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *