ሐምሌ 27/2014 ዓ/ም

ኮሌጆች ውብና ማራኪ በማድረግ የመማርና የማስተማሩ ሂዲት ውጤታማ ለማድረግ የአረንጓዴ ልማት ስራ የበኩሉን አስተዋፅኦ እንዳለው የጉራጌ ዞን ቴክኒክናሙያ ትምህርት ስልጠና መምሪያ አስታወቀ።

በጉንችሬ ክንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ የዞን ቴክኒክናሙያ ትምህርት ስልጠና መምሪያ አመራሮ፣ የከተማው አመራሮች፣ የኮሌጁ የስራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች የችግኝ ተከላ አካሂደዋል።

የጉራጌ ዞን ቴክኒክናሙያ ትምህርት ስልጠና መምሪያ ኃላፊ አቶ አብዱ አህመድ በዞኑ በሚገኙ የመንግስትና የግል ኮሌጆች በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ሰልጠና በመስጠት በቁና ውጤታማ የሰው ኃይል በማፍራት ለሀገር ኢኮኖሚያዊ እድገት የራሳቸው አስተዋፅኦ አያበረከቱ ይገኛሉ ።

ኮሌጆች ውብና ማራኪ በማድረግ የመማርና የማስተማሩ ሂዲት ውጤታማ ለማድረግ የአረንጓዴ ልማት ስራ የበኩሉን አስተዋፅኦ እንዳለው ያስታወቁት አቶ አብዶ አህመድ በዞኑ ያሉ ኮሌጆች የአረንጓዴ አሸራቸውን ለማኖር 22ሺ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞችን ለመትከል አቅደው እስከ ዛሬው እለት 17ሺ ችግኞች መትከላቸውና ቀሪውን በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደሚተከሉ ጠቁመዋል።

ይህም የመማርና የማስተማር ሂዲት የበለጠ ሳቢና ምቹ እንዲሆን ያለው ሚና የጎላ በመሆኑ የኮሌጆች ግቢ በአረንጓዴ ልማት ለማሰዋብ የተጀመረው ስራ በቀጣይ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

በኮሌጁ የሚነሱ የመልካም አስተዳደርና የግብዓት ችግሮችን በተለይም የኮሌጁ ወሰን ለማስከበር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር የበለጠ ተቀናጅተው እንደሚሰሩና እንደሚያስተካክሉ ገልፀዋል።

የጉንችሬ ከተማ ከንቲባ አቶ አብዱልቃድር ሒጅራ አንደገለጹት እንደ ሀገር የተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ መረሃ ግብር እውን ለማድረግ በከተማው የተለያዩ ጠቀሜታ ያላቸው ሀገር በቀል ችግኞችን ህብረተሰቡን በማሳተፍ 287ሺ ችግኞች ለመትከል ታቅዶ እስከ አሁን 265 ሺ ለውበት፣ለጥላና ለምግብነት ጠቀሜታ ያላቸውን ችግኞችን መተከላቸውን አብራርተዋል ።

የጉችሬ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ዋና ዲን አቶ አሸናፊ ሰመርጋ በበኩላቸው ኮሌጆች በዛፎችና በተለያዩ ነገሮች ማስዋብ ለመማር ማስተማር ሂደት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረክታል ብለዋል።

የፍራፍሬ ፣የጥላና የውበት ጠቀሜታ ያለቸውን ከ2 ሺ 65 በላይ ችግኞች ዛሬ ጨምሮ በሁለት ዙር በኮሌጃቸው ግቢ መተከላቸውን የገለፁት ዋና ዲኑ የተተከሉ ችግኞችን የማኔጅመንትና የኮሌጁ አሰልጣኞች ያሳተፈ ኮሚቴ በማቋቋም ተከታታይነት ያለው የእንክብካቤ ስራ እንደሚሰራ ተናግረዋል።

በ2010 ዓ.ም በ2 የስልጠና ዘርፎች ስራ የጀመረው ኮሌጁ አሁን ላይ በጨርቃጨርቅ፣ በአይሲቲ ፣በግንባታ ፣በኢሌትሪክ ኢንስታሌሽንና ብረታብረት ዘርፎች 307 ተማሪዎችን ተቀብሎ እያሰለጠነ ይገኛል ብለዋል።

ኮሌጁ በመማር ማስተማር ሂደት የሚገጥመው የማሸነሪና ሌሎች የማሰልጠኛ ቁሳቁሶች ችግሮች ለመቅረፍ ከወልቂጤ ዮኒቨርሲቲና በአምባሳደር ምስጋናው አርጋ አማካኝነት የተወሰነ ድጋፍ ማግኘታቸውን የገለፁት የኮሌጁ ዲን አቶ አሸናፊ ሰመረጋ እንደ ክልል የሚደረግ ድጋፍ አነስተኛ በመሆኑን በቀጣይ ትኩረት ሊሠጠው ይገባል ብለዋል።

በችግኝ ተከላ ካነጋገርናቸው ተሳታፊዎች መካከል ወ/ሮ ሎሚነሽና አቶ ንጉሱ ደሴ በሰጠት አሰተያየት
ለትውልድ ዘላቂ በሆነው የአረንዴ ልማት ላይ የራሳቸውን አሻራ በማኖራቸው ደስተኛ መሆናቸውን ተናግሯል ።
ከመትከል በሻሻገር የተኩሉትን ችግኝ እንዲፀድቁ ወቅቱን ጠበቀው ተገቢ እንክብካቤ ለማድረግ መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።

በመጨረሻም የዞን ቴክኒክናሙያ ትምህርት ስልጠና የማኔጅመንት አካላት፣የጉንችሬ ከተማ አመራሮች፣ የኮሌጁ የስራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች የኮሌጁ የስራ እንቅስቃሴ ጎብኝተዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን መንግሥት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው ።

በመረጃ ምንጭነት ገፃችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን!
እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub:- https://youtube.com/channel

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *