የካቲት 12/2014 ዓ.ም

ተተኪ አትሌቶችን ለማፍራት የዘቢዳር አትሌቲክስ ክለብ መጠናከር በሀገር ደረጃ ተፎካካሪ አትሌቶችን ለማፍራት እንደሚያስችል የጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፓርት መምሪያ ገለጸ ።

መምሪያው ከከተማና ከወረዳ የመጡ አትሌቶችን በአጭር፣በመካከለኛ እና በርጅም ርቀት ወደ ዘቢዳር አትሌቲክስ ክለብ ለማስገባት በወልቂጤ ከተማ በዛሬው ዕለት አወዳድሯል።

በዝግጅቱ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት ረዳት ፕሮፌሰር መለሰ እጥፉ እንደገለፁት የአትሌቲክስ ዘርፍ ትልቅ ጠቀሜታ አለው።

አክለውም በሀገራችን ብሎም በአለም ላይ ታዋቂ የሆኑት አትሌቶች ከገጠራማው የማህበረሰብ ክፍል ወጥተው ስኬታማ በመሆናቸው ከራሳቸው አልፈው በተለያዪ አከባቢዎች ኢንቨስት እያደረጉ ለማህበረሰቡ ህይወት የሚቀይር ስራ እየሰሩ ይገኛሉ ብለዋል።

የዘቢዳር አትሌቲክስ ክለብን ለማጠናከር ጠንክሮ መስራት እንደሚገባና ለቴክኒካዊ ድጋፎች ዩኒቨርሲቲው ከጎናቸው እንደሆነም አመላክተዋል ።

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና የማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ዶክተር የኃንስ ገብሩ እንደገለጹት በሀገራችን ያሉ አትሌቶች መነሻቸው ከታች በመሆኑ ተተኪ አትሌቶች መቼም ቢሆን ተስፋ ሳይቆርጡ ትልቅ ደረጃ እስኪደርሱ መስራት ይኖርባቸዋል ብለዋል።

የጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ኃላፊ አቶ አበበ አሰፋ እንደተናገሩት በቂ ባይሆንም የበጀት ድጋፍ እንደሚደረግና ዘቢዳር አትሌቲክስ ክለብ አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ ማገኘት ያለበትን ነገረ አግኝቷል ማለት እንደማይቻል ገልጸዋል ።

አትሌቶች ልምምድ እያደረጉ ያሉት በተሟላ ትጥቅ አለመሆኑንና የዞኑን አቅምና የሀገሪቱን ወቅታዊ ሁኔታ በመረዳት ተስፋ ሳይቆርጡ እሩቅ በማለም ሊሰሩ ይገበዋል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ። በቀጣይ ዞኑ የተቻለውን ሁል ለማድረግና ለመደግፍ ዝግጁ መሆኑን በመግለጽ።

የጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ም/ኃላፊና የስፖርት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አደም ሽኩር እንዳሉት በዞኑ የተመሰረተው ዘቢዳር አትሌቲክስ ክለብ ሀገር አቀፉ ካሉ ክለቦች ተወዳዳሪ እንዲሆን በየወረዳና ከተማ አስተዳድሮች ያሉ አትሌቶችን በዛሬው ውድድር ላይ አቅማቸውን በማየት ምርጥና ተፎካካሪ አትሌቶችን ወደ ዘቢዳር አትሌቲክስ ክለብ ለማስገባት ያለመ እንደሆነ ተናግረዋል ።

በተጨማሪም በክለብ ውስጥ ያሉ አትሌቶችን አቅም መፈተሽ የሚያስችል ትልቅ ውድድር እንደሆነና በቀጣይ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሚካሄደው የወጣቶች ሻምፒዮን ለቅደመ ዝግጅት ስራ ይረዳል ብለዋል አቶ አደም።

አክለውም በየመዋቅሩ ያሉ የአትሌቲክስ መዋቅሮችም በዚህ ውድድር እንዲታዩና ምን ደረጃ ላይ እንዳሉ እንዲሁም እንዲነቃቁ ለማድርግ ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ብለዋል።
ለስፖርቱ ዘርፍ ድጋፍ እያደረጉ ያሉ ወልቂጤ ዩኒቨርስቲና ሌሎችም የመንግስት ተቋማትን አቶ አደም ሽኩር አመስግነው ቀጣይነት እንዲኖረውም ጠይቀዋል ።

አንዳንድ ያነጋገርናቸው የውድድሩ ተሳታፊዎች እንዳሉት ውድድሩ አበረታች እንደነበረና ለአትሌቲክስ ዘርፉ መንግስት ትኩረት እየሰጠው መሆኑን ማሳያ የሚሆን ነው ብለዋል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *