በጉራጌ ዞን በእኖር ኤነር መገር ወረዳ በመኸር እርሻ 4 ሺህ 1 መቶ 133 ሄ/ር መሬት ሰብል መሸፈኑን የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት አስታወቀ። የወረዳው ም/አስተዳዳሪና የግብርና ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ መላኩ ሳህሌ በቅኝት ወቅት እንደገለጹት አርሶ አደሮች የባለሙያዎች ምክረሀሳብ ተግባራዊ ማድረግ በመቻላቸው በዘንድሮ የመኸር ወቅት የተመዘገቡ ውጤቶች አበረታች መሆናቸውን ገልጸዋል። አቶ መላኩ በወረዳው የተለያዩ… Continue reading
መስቀል በጉራጌ” የንግድ ትርኢት ኤግዚብሽንና ባዛር በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ ተከፈተ። በዞኑ ወልቂጤ ከተማ የተከፈተው የንግድ ትርኢትና ባዛር የከተማዋ የንግድ እንቅስቃሴ እንዲነቃቃና ገጽታዋ እንዲጎላ ከማድረግ ባለፈ የህብረተሰቡን እሴት በማስተዋወቅ ረገድ ሚናው ከፍተኛ መሆኑን የጉራጌ ዞን አስተዳደር ገለጸ። የጉራጌ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና… Continue reading
በየደረጃው በሚገኙ የህዝብ ምክር ቤቶች የጸደቀውን በጀት በአግባቡ በማስተዳደር ለታለመለት አላማ እንዲውል በትኩረት እየሰራ መሆኑን የጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ አስታወቀ። መምሪያው የ2016 አመተ ምረት የተግባር አፈጻጸም ግምገማና የ2017 በጀት አመት እቅድ ላይ ያተኮረ ውይይት በወልቂጤ ከተማ አካሂዷል። የጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ኃላፊ አቶ አብዶ ሀሰን በመድረኩ ላይ እንዳሉት መንግስት ለፋይናንስ… Continue reading
ህብረተሰቡ ተገቢውን አገልግሎት እንዲያገኝ ታማኝ ፣ቅን፣ ታታሪ ሰራተኛ ማፍራት እና እውቅና መስጠት ወሳኝነት እንዳለው የጉራጌ ዞን አስተዳደር አስታወቀ። አመራሩና ፈጻሚው አካል የአገልጋይነት አመለካከት በመላበስ ለህብረተሰቡ የበለጠ ማገልገል እንደሚገባ የጉራጌ ዞን ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት መምሪያ ገልጿል። መምሪያው የ2016 በጀት አመት የእውቅናና ሽልማት ማጠቃለያ መድረክ በወልቂጤ ከተማ አካሂዷል።… Continue reading
የሀዋሪያት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን ለማሟለት እንዲቻል ለሚያግዙ አካላት ሁሉ ጥሪ ቀርቧል። የሀዋሪያት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አቅም ለማሳደግ #አዲስዓመት ለአዲስስኬት በሚል አጀንዳ #ለሆስፒታላችንእናዋጣለን❗️ በሚል መሪ ሀሳብ ከሀዋሪያት ከተማ ነዋሪዎች ጋር ማለትም ከንግዱ ማህበረሰብና ከመንግስት ሰራተኞች ጋር የምክክር መድረክ ተካሄዷል። በምክክር መድረኩ የተገኙት… Continue reading
በዞኑ በኢንቨስትመንት በሁሉም ዘርፍ ያሉ አማራጮችን በተገቢው በመጠቀም ውጤታማ ስራ ለመስራት በዘርፉ ያሉ ማነቆዎችን መፍታት እንደሚገባ የጉራጌ ዞን ኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ልማት መምሪያ ገለጸ። መምሪያው በ2016 ዓ.ም የኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ልማት መምሪያ የአፈጻጸም ግምገማ ግብረ መልስ፣ የኢንቨስትመንት አማራጮችና ሌሎችም ላይ ከወረዳው አመራሮች ጋር ውይይት አካሂዷል። የጉራጌ ዞን ኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ልማት መምሪያ ኃላፊ ወይዘሮ አመተሩፍ ሁሴን… Continue reading