ስራ አጥ ዜጎችን በተለያዩ የስራ ዘርፎች ላይ በማሰማራት የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት በትኩረት መሰራት እንዳለበት ተገለጸ። በጉራጌ ዞን አስተዳደር የስራ ዕድል ለመፍጠር እና የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ የቀጣይ 5 ወራት ክህሎት መር ልዩ የስራ እቅድ ፈጠራ ላይ ዞን አቀፍ የንቅናቄ መድረክ በወልቂጤ ከተማ አካሂደዋል ። የጉራጌ ዞን… Continue reading
በክልል የክለቦች ሻምፕዮና ጉራጌ ዞን ወክሎ እየተሳተፈ የሚገኘው የቡኢ ከተማ እግር ኳስ ቡድን የግማሽ ፍፃሜ ማለፉን አረጋግጧል። የቡኢ ከተማ እግር ኳስ ቡድን የ2015 ዓ.ም በጉራጌ ዞን የስፖርት ሻምፒዮና በ3ኛነት ደረጃ አጠናቅቆ የደቡብ ክልል ባዘጋጀው ውድድር ተሳታፊ መሆን ችሏል። በመሆኑም ግንቦት 21/2015 በ9:00 ቡኢ ከተማ ከብሩህ ተስፋ ቡድን… Continue reading
የስራ ዕድል ፈጠራ ስራዎችን በማስፋት በየአካባቢው ያሉትን ስራ አጥ ዜጎች ወደ ስራ እንዲገቡ ለማስቻል ተቀናጅቶ መስራት እንደሚገባ የጉራጌ ዞን ስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት መምሪያ አስታወቀ። መምሪያው የ2015 በጀት አመት የ10 ወራት እቅድ አፈጻጸም ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በወልቂጤ ከተማ የውይይት መድረክ አካሂዷል። የጉራጌ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የስራ ዕድል ፈጠራ ኢንተርፕራይዞች ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሙስጠፋ… Continue reading
የጉራጌ ማህበረሰብ አንድነት፣ ሰላምና ልማት ይበልጥ እንዲረጋገጥ የጉራጌ ሸንጎ ማጠናከር እንደሚገባ የጉራጌ ዞን አስተዳደር አስታወቀ። የጉራጌ ዞን አስተዳደር ከጉራጌ ዞን ባህል ቱሪዝም መምሪያ ጋር በመተባበር የጉራጌ የባህል ሸንጎ 2ኛ አመት መደበኛ ጉባኤ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በወልቂጤ ከተማ አካሂዷል። የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ… Continue reading
በጉራጌ ዞን በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ በ63 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነባው የጅማ ወለኔ የከንተዋት ዘቢደር የ38 ኪሎሜት መንገድ ግንባታ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት መደረጉን የደቡብ ክልል መንገዶች ባለስልጣን ገለፀ። የጉራጌ ብሔር በመንገድ ልማት ያለው የቆየ ልምድ በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አስታወቀ ።የደቡብ ክልል መንገድ ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር አበባየሁ ታደሰ እንደገለጹት በክልሉ በተያዘው በጀት ዓመት… Continue reading
በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ ከ15 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ በአካባቢው ህብረተሰብ እና ባለሀብቶች የተገነቡ የመንገድ ፕሮጀክቶች አገልግሎት መስጠት ጀመሩ። የአካባቢው ማህበረሰብ የልማት ተጠቃሚነቱን ለማሳደግ ተቀናጅተው እንደሚሰሩ የወረዳው ባለሀብቶች ተናግረዋል። የእዣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘውዱ ዱላ በመንገዶቹ ምረቃት ስነስርዓት ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር የጉራጌ ማህበረሰብ የራሱን አቅም፣ እውቀትና ገንዘብ… Continue reading