የደቡብ ክልል ውሃ፣ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ በሺንሺቾ እና ቡኢ ከተሞች በባስኬት ፈንድ ለሚያስገነባቸው የንፁህ መጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮጀክቶች የግንባታ ስምምነት ፊርማ ስነሥርዓት ከሁለት ውሃ ሥራ ተቋራጮች ጋር ፈፅሟል፡፡

በስምምነት ፊርማ መርሀ ግብሩ ላይ የተገኙት የደቡብ ክልል ውሃ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ ኃላፊ ኢንጂነር አክሊሉ አዳኝ እንደገለጹት የክልሉን ህዝብ የመጠጥ ውሃ ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ከመንግስትም ሆነ ከተለያዩ አጋር ድርጅቶች…

Continue reading

በነዳጅ ላይ የታየውን የዋጋ ጭማሪ ከግምት ውስጥ በማስገባት በአነስተኛና መካከለኛ የህዝብ አገልግሎት ሰጪ ተሽከርካሪዎች ላይ የትራንስፖርት ታሪፍ ማሻሻያ መደረጉም የጉራጌ ዞን ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ አስታወቀ።

የታሪፍ ማሻሻያው በመመሪያው መሠረት ተግባራዊ እንዲሆን ሁሉም ባለድርሻ አካላት የድርሻቸውን ሊወጡ እንደሚገባም ተጠቁሟል ። በሀገር አቀፍ ደረጃ የነዳጅ ዋጋ መጨመሩም ይታወቃል ይህንንም ታሳቢ በማድረግ በትራንስፖርት ዋጋ ላይ የታሪፍ ጭማሪ መደረጉም…

Continue reading

በስነጽሁፍ የዕድሜ ዘመን ተሸላሚ ፤ ሃያሲ፣ ደራሲ እና ተርጓሚ የክብር ዶክተር ሳህለ ስላሴ ብርሃነ ማርያም የምስጋና ስነስርዓትና በደራሲው የተዘጋጀ ‹‹የሺንጋ መንደር›› የተሰኘ መጽሃፍ ርክክብ መርሀ ግብር በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ተካሄደ፡፡

በስነስርዓቱ ላይ የታደሙት የዩኒቨርሲቲው የማኔጅመንት ካውንስል አባላት፤ከዞን ትምህርት መምሪያ የተውጣጡ የትምህርት ባለሙያዎች፤ ከተለያዩ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ የትምህርት ቤት ርዕሳነ መምህራንና ከአባ ፍራንሷ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተውጣጡ 50 ተማሪዎች ሲሆኑ…

Continue reading

አሸባሪው የህዋሀት ቡድን በሴቶችና ህጻናት እንዲሁም በሰላማዊ ህዝብ ላይ እያደረገ ያለው የጅምላ ጭፍጨፋንና ጥቃት የሚቃወም ዞናዊ የሴቶች ሰልፍ በጉራጌ ዞን በወልቂጤ ከተማ ተካሄደ፡፡

የዞኑ ሴቶች ከመንግስትና ከመከላከያ ሰራዊት ጎን በመሆን ከሚያደረጉትን ቁሳዊ ድጋፍ ባለፈ አስከ ግንባር ለመዝመት ቁርጠኛ መሆናቸዉን ተናግረዋል፡፡ የደቡብ ክልል ሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ቢሮ ም/ኃላፊ ወ/ሮ ኩሪባቸዉ ታንቱ በሰልፉ ላይ እንደገለጹት…

Continue reading

ህጻናት በዕዉቀትና በስነ -ምግባር እንዲታነጹ በማድረግ የሀገራቸውን ባህል በጠበቀ መልኩ እንዲያድጉ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ሀላፊነት እንዳለበትም የጉራጌ ዞን ሴቶችና ህጻናት ጉዳይ መምሪያ አስታውቀ፡፡

የዞኑ የህጻናት ፓርላማ 8ኛ ዓመት 15ኛ ዙር 1ኛ መደበኛ ጉባኤ በወልቂጤ ከተማ ከሁሉም ወረዳዎችና ከተማ አስተዳድሮች የተዉጣጡ የህጻናት ፓርላማ ተወካዮች እንዲሁም የጉራጌ ዞን ሴቶችና ህጻናት ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ መሰረት…

Continue reading