Month: October 2021
በጉራጌ ዞን በወልቂጤ ከተማ የክልሉ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በክረምት በጎ ተግባር አገልግሎት ያሰራዉን አዲስ የአረጋዉያን ቤት የርክክብና የምርቃት ስነ ስርአት በዛሬዉ እለት ተካሄደ ።
ወጣቶች በተለያዩ የስራ ዘርፎች እንዲሰማሩ በማድረግ ከኢኮኖሚ ጥገኝነት ተላቀው በሀገሪቱ ምጣኔ ሀብት እድገት አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ መስራት እንደሚገባ የደቡብ ክልል የስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ አስታወቀ፡፡
በጉራጌ ዞን ከትምህርት ገበታቸዉ የራቁ 38 ሺህ 960 ተማሪዎች ወደ ትምህርታቸዉ እንዲመለሱ በማድረግ ረገድ አመራሩ ፣ የትምህርት ባለድርሻ አካላቶችና ማህበረሰቡ በቅንጅት መስራት እንዳለባቸዉ የዞኑ ትምህርት መምሪያ አስታወቀ።
በዞኑ በመጀመሪያ ሩብ አመት ከመደበኛና ከማዘጋጃ ቤት 392 ሚሊየን 9 መቶ 73 ሺህ ብር በላይ መሰብሰቡን የጉራጌ ዞን ገቢዎች ባለስልጣን ዋና ቅርንጫፍ ፅ/ቤት አስታወቀ።
አዲሱ ዴልታ የኮሮና ቫይረስ በሽታ ለመከላከል የክትባት አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑ የጉራጌ ዞን ጤና መምሪያ አስታወቀ።
በዞኑ ለሚገኙ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎችና ለትምህርት ሴክተር ባለድርሻ አካላት የኮቪድ 19 ቫይረስ መከላከል ክትባት በዛሬ እለት በወልቂጤ ከተማ ተሰጥቷል። አዲሱ ዴልታ የኮሮና ቫይረስ በሽታ በከፍተኛ ደረጃ እየተዛመተ እንደሆነም ማህበረሰቡ አዉቆ…