2017 ዓ.ም በሁሉም የ2ተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የስራና ክህሎት ስልጠና ትምህርት እንደሚጀመር የጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ አስታወቀ።

2017 ዓ.ም በሁሉም የ2ተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የስራና ክህሎት ስልጠና ትምህርት እንደሚጀመር የጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ አስታወቀ።

ስልጠናው ተግባራዊ ለማድረግ እየተሰሩ በሚገኙ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ከትምህርት ስትሪንግና ቴክኒክ ኮሚቴዎች ጋር የመግባቢያና የምክክር መድረክ በወልቂጤ ከተማ ተካሂዳል።

የጉራጌ ዞን አስተዳደር ልዩ አማካሪ አቶ ዳርጌ ተክሉ በመድረኩ ተገኝተው እንዳሉት በዞኑ በ2017 ዓ.ም በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ከ11ኛ ክፍል ጀምሮ የስራና ክህሎት ስልጠና ለመጀመር የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰሩ ይገኛል።

ለተማሪዎች በተግባር የተደገፈ ትምህርት መሰጠቱ ወደ የሚፈልጉት የሙያ መስክ ያላቸው ዝንባሌ በተገቢው እንዲጠቀሙ ያደርጋቸዋል ብለዋል።

በትግበራው ወቅት የሰው ሀይልና የግብአት ችግር እንዳይገጥም በየደረጃው ያሉ ጸጋዎችን በተገቢው መጠቀም እንደሚገባ አቶ ዳርጌ አንስተዋል።

በዞኑ የሙያ ትምህርት ትግበራው በተገቢው እንዲሰጥና ለውጤታማነቱ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ድርሻ ሊወጡ ይገባል ብለዋል።

የጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ መብራቴ ወልደማርያም በበኩላቸው በ2015/16 ዓ.ም በሀገር አቀፍ ደረጃ አዱሱ ስርአተ ትምህርት ተግባራዊ መሆኑን ገልጸዋል።

በዚህም ከስርአተ ትምህርቱ ውስጥ የሙያ ትምህርት አለመጀመሩ አስታውሰው በ2017 ዓ.ም በዞኑ በሁሉም 2ተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ከ11 ክፍል ጀምሮ የሙያና የስራ ትምህርት ለመጀመር የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰሩ ይገኛል ብለዋል።

በአዲሱ ስርአተ ትምህርት የተካተተው የሙያ ትምህርት ከክልል ጀምሮ ለማስጀመር ቴክኒክና ስትሪንግ ኮሚቴ በማዋቀር ተማሪዎች በሚፈልጉት ሙያ የመመዝገብና ግንዛቤ የመስጠት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

በዛሬው እለት የዞኑ ቴክኒክ ኮሚቴና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የሙያ ትምህርት ቅድመ ዝግጅቱ ላይ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች መገምገሙን ያነሱት ኃላፊው በቀጣይ የሙያ ትምህርት በዞኑ በተገቢው ለመስጠት ከቴክኒክና ስትሪንግ ኮሚቴና ከሌሎች ተቋማት በቅንጅት የሚሰሩ ስራዎች ለማጠናከር ያለመ መድረክ ነው ያሉት።

በቀጣይ እስካሁን እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ከማጠናከር ባለፈ የነበሩ ችግሮችን በማረም የተሻለ ስራ ለማሳካት እንደሚሰራ ነው።

የሙያ ትምህርት በተገቢው ለማስጀመር አስፈላጊ የሰው ሀይልና ግብአት ለማሟላት እንደሚሰራ ገልጸው የሰው ሀይል ችግር ለመቅረፍ በስትሪንግ ኮሚቴው ያሉ ተቋማት በትኩረት ከመስራት ባለፈ መምሪያው አስፈላጊውን እገዛ እንደሚያደርግ አመላክተዋል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች እንዳሉት በዞኑ የሙያ ትምህርት መጀመሩ ተማሪዎች በሚፈልጉት የሙያ መስክ እንዲማሩ እንደሚያደርግ ጠቅሰው ለዚህም ለትግበራው ውጤታማነት እንደሚተጉ ገልጸዋል።

አክለውም በትግበራዉ ወቅት የሰው ሀይልና የግብአት ችግር እንዳይገጥም በትኩረት እንዲሰራበትም አመላክተዋል ሲል የዘገበው የዞኑ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን መምሪያ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *