20ኛው የጉራጌ ዞን የባህል ስፖርት ውድድር በወልቂጤ ከተማ በይፉ መካሄድ ጀመረ።

ጥር 4/2015 ዓ.ም

20ኛው የጉራጌ ዞን የባህል ስፖርት ውድድር በወልቂጤ ከተማ በይፉ መካሄድ ጀመረ።

የባህል ስፖርት ውድድር የዞኑ ባህል ወግና እሴቶችን ለማጉላትና ወድማማችነትን ለማጠናከር ጉልህ ሚና እንዳለው የጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ አስታወቀ።

የባህል ስፖርት በአዝጋሚ ለውጥ ከህብረተሰቡ እድገት ጋር እያደገና እየዳበረ የመጣ ብሎም ወግና ማእረጉን የሱነቱን መገለጫ ከሆኑ ቅርሶች ውስጥ አንዱና ዋነኛ ነው።

የጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ምክትልና የስፖርት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አደም ሽኩር እንደገለፁት የዞኑ የስፖርት ምክር ቤት ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራት ልዩ ልዩ የስፖርት ውድድሮችን በማዘጋጀት ዘርፉን የማጠናከር ስራ ይሰራል።

ስፖርት ሰዎች ከሚያደርጓቸው ቤተሰባዊ ፣ጎረ ቤታዊ፣ዞናዊ፣ሀገራዊና፣አህጉራዊ ብሎም አለምአቀፋዊ ግንኙነት ከማጠናከሩ ባለፈ አካላዊ፣መንፈሳዊና ስነ ልቦናዊ እርካታ ለማግኘት የሚያደርጉት የፉክክር ጨዋታ ነው ብለዋል።

በመሆኑም የባህል ስፓርት በገጠር የሚኖረውንን ህብረተሰብ አካላዊ ብቃቱ የሚያዳብርበት፣የተዳከመ አእምሮዉና የዛለ አካሉን የሚያነቃቃበትና በትርፍ ሰአቱና በበዓላት ቀናት ማህበራዊ ግንኙነትን የሚያጠናከርበት በመሆኑ ጥቅሙ የጎላ እንደሆነ አስገንዝበዋል።

የባህል ስፖርት ውድድር የዞኑ ባህል ወግና እሴቶችን ለማጉላትና ወንድማማችነትን ለማጠናከር ጉልህ ሚና እንዳለው አቶ አደም ተናግረዋ።

አክለውም 20ኛው የጉራጌ ዞን የባህል ስፖርት ውድድር በ8 የስፖርት አይነቶች ማለትም በትግል፣በገበጣ 12 እና 18 ፣በኮርቦ፣ሻህ፣ቡብ፣በፈረስ ጉግስና ሸርጥ ላይ የሚካሄድ ሲሆን የእያንዳንዱ ውድድር አሸናፊዎች ዞኑን ወክለው በክልል አቀፍ በሚካሄደው ውድድር እንደሚሳተፉ ገልጸዋል።

በመክፉቻ ላይ በተካሄደው የ63፣67 ምድብ የትግል ውድርር እኖር ወረዳ አበሽጌ ወረዳን 2ለ1 ሲያሸንፍ ጉመር ወረዳ ከቸሀ ወረዳ እኩል ቢለያዩም በኪሎ ግራም ጉመር ወረዳ አሸናፊ ሆኗል ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን መንግድት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

በመረጃ ምንጭነት ገፃችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን!

በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *