ጽህፈት ቤቱ በኢንቨስትመንት ልማት ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ለባለድርሻ አካላት በወልቂጤ ከተማ መስጠቱን ተመልክቷል ።

የጉራጌ ዞን ኢንቨስትመንት ማስፋፊያ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዘነበ ደበላ በስልጠናው ወቅት እንደተናገሩት የዞኑ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ለማነቃቃት እየተሰራ ሲሆን በዚህም 20 ሺህ 7 መቶ 62 ለሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች የስራ እድል ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል።

እንደ ኃላፊው ገለፃ የኢንቨስትመንት ዘርፍ ለዜጎች የስራ እድል ተጠቃሚ ከማድረግ ባሻገር ፕሮጀክቶቹ በሚገኙባቸው አካባቢዎች የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች በመብራት፣ በውሃ፣ በጤና፣ በትምህርትና በመንገድ መሰረተ ልማቶች በመሳተፍ አበረታች ተግባራት እያከናወኑ ይገኛሉ።

ሀገሪቱ በከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ የምታስገባቸው የምግብ ውጤቶችና ሌሎች የፋብሪካ እቃዎች በሀገር ውስጥ ምርት ለመተካት እየተሰራ ሲሆን ባለሀብቶች አዳዲስና ምርትና ምርታማነትን የሚያሻሽሉ ቴክኖሎጂዎችን ማሸጋገር ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።

በዞኑ በግብርናው ዘርፍ ምርጥ ዘር በማባዛት ለክልሉ ምርጥ ዘር ድርጅት የሚያቀርቡና ለአርሶ አደር የሚያሸጋግሩ ፕሮጀክቶች እንዳሉም ገልጸዋል።

አያይዘውም አቶ ዘነበ በዞኑ በግንባታና በምርት ሂደትም በሚፈሰው ካፒታል፣ በሚከፈለው የመሬት ኪራይ፣ በገቢ ግብርና ከሰራተኞች ደመወዝ የስራ ግብር የዞኑ፣ የወረዳና የከተሞች የገቢ መጠን በማሳደግ ረገድ ጉልህ አስተዋጽኦ ያበረክታሉ ብለዋል።

ይሁን እንጂ በዞኑ በተለያዩ አካባቢዎች መዋዕለ ንዋያቸውን ለማፍሰስ የኢንቨስትመንት ፍቃድ አግኝተው ቦታ የተረከቡ አንዳንድ ባለሀብቶች በተሰጣቸው የኢንቨስትመንት ፍቃድ መሰረት ባለማልማታቸውና የተረከቡትን መሬት አጥረው የሚያቆዩ ባለሀብቶች በመኖራቸው በዘርፉ ውጤታማነት ላይ የሚኖረው ተጽዕኖ ከፍተኛ እንደሆነም ኃላፊው አስረድተዋል።

ስለሆነም ለልማታዊ ባለሀብቶች ድጋፍና ክትትል ለማድረግና ወደ ስራ ያልገቡ ፕሮጀክቶች ስራ ለማስጀመር የሚጠይቋቸው የመሰረተ ልማት ጥያቄዎች ለመመለስ ባለድርሻ አካላት ተገቢውን ድጋፍ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ገልጸዋል።

የስልጠና ሰነዱን ያቀረቡት አቶ ሰፋሁዲን ሸረፎ በበኩላቸው ባለድርሻ አካላት ለኢንቨስትመንት ዘርፍ ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር የዞኑ እምቅ ሀብት ጥቅም ላይ እንዲውል የድርሻቸውን እንዲወጡ ለማስቻል ያለመ ስልጠና ነው ብለዋል ።

በዞኑ በተለያዩ አካባቢዎች መዋዕለነዋያቸው ለሚያፈሱ ባለሀብቶች ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ጥበቃ እንዲያደርግላቸውና የኢንቨስትመንት ጠቀሜታ እንዲረዳ ሰልጣኞች ትኩረት ሰጥተው መስራት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።

አያይዘውም አቶ ሰፋሁዲን ኢንቨስትመን ጥበቃ እንዲደረግለት የተደነገገ በመሆኑ መሬት ለባለሀብቱ ርክብክብ ከተደረገለት በኋላ በሶስተኛ ወገን ጥቃት ሲፈጸምበትና ጣልቃ ገብነት ሲከሰትበት ችግሩ በአካባቢው መዋቅር ሊፈታ ይገባል ብለዋል።

በየደረጃው የሚገኙ የመንግስት አስፈፃሚ አካላት ለዘርፉ የሚያደርገው ድጋፍ አነስተኛ በመሆኑ በውጤታማነቱ ላይ ተጽዕኖ የፈጠረ ሲሆን በቀጣይ ለዘርፉ የሚሰጠው ትኩረት በማሳደግ የሚፈለገውን ውጤት ለማስመዝገብ ተቀናጅቶ መስራት ይገባል ብለዋል።

የስልጠናው ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት የዞኑ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ በሚፈለገው ደረጃ አለመጠናከር በዞኑ ሁለንተናዊ እድገቱ እንዲገታ አድርጎታል።

ዞኑን ከአዲስ አበባ ቅርብ ቢሆንም በተለያዩ ዘርፎች መዋዕለንዋያቸውን ለማፍሰስ ወደ ዞኑ የሚመጡ ባለሀብቶች ፈጣን አገልግሎት ባለማግኘታቸው ፕሮጀክቶቻቸው ወደ ሌላ አካባቢ እንዲቀይሩ ይገደዳሉ ብለዋል።

ይህ ደግሞ የዞኑ የገቢ አቅምና ማህበራዊ ተጠቃሚነት እንዲቀንስ ያደርገዋል ብለዋል።

እንደ ተሳታፊዎች ገለጻ ባለሀብቶቹ ለሚጠይቋቸው መሰረታዊ ጥያቄዎች ፈጣን ምላሽ ከመስጠት በተጨማሪ ሳያለሙ አጥረው የሚያቆዩና ከአርሶ አደሩ በማይሻል ደረጃ የሚያለሙ ባለሀብቶች ሙሉ አቅማቸው እንዲጠቀሙ ድጋፍ እንደሚያደርጉላቸው አስረድተዋል።

= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!

በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *