16/02/2014 አርሶ አደሩ በከብት እርባታው ዘርፍ ውጤታማ ለማድረግ የተጀመረው የሲንክሮናይዜሽን ዘመቻ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የሁሉም ሰው ድጋፍ እንደሚያስፈልግ የጉራጌ ዞን ግብርና መምሪያ አሳወቀ።

ዞን አቀፍ የክላስተር የስንክሮናይዜሽን ዘመቻ ዛሬም በእዣ ወረዳ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

የጉራጌ ዞን ግብርና መምሪያ የእንስሳት ዓሳ ሀብት ልማት ዘርፍ አስተባባሪ አቶ መሀመድ ሙደሲር እንደገለፁት በእንስሳት ዘርፍ አርሶ አደሩ የኢኮኖሚ ተጠቃሚ እንዲሆን በዘለማድ የሚደረገው የከብት እርባታ በማስቀረት ዝርያቸው የተሻሻሉ ከብቶች እንዲራቡ ማስደረግ ያስፈልጋል ብለዋል።

አቶ መሃመድ አክለውም ይህን ታሳቢ በማድረግ ዘንድሮም በ15 ወረዳና ከተማ አስተዳደር እንዲሁም በ22 ክላስተር እስከ ህዳር የሚደረገው የሲንክሮናይዜሽን ዘመቻ ተጠናክሮ እየሄደ እንደሆነ አሳውቀዋል ።

በመሆኑም አርሶ አደሩ በከብት እርባታው ዘርፍ ውጤታማ ለማድረግ የተጀመረው ስራም ተጠናክሮ እንዲቀጥል የሁሉም ሰው ድጋፍ ያስፈልጋል ሲሉ መልእክታቸውን አስተላልፏል።

የእዣ ወረዳ እንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መሀሙድ አህመድ እንዳሉት በወረዳው በመደበኛ ሆነ በሲንክሮናይዘሽን ማዳቀል ተግባር በየወቅቱ እየተሰራበት ነው ብለዋል።

በወረዳው የመኖ ችግር እንዳይገጥም አርሶ አደሩ በኩታ ገጠም የመኖ ችግኝ እንዲተክል ተደርጓል ያሉት ኃላፊው አርሶ አደሮቹ የሚያነሱት የፉርሽካ አቅርቦት ችግር እንዲቀረፍ በትኩረት ይሰራበታል ሲሉ ጠቁመዋል ።

ዘመቻው በአንድ ቤት ተመሳሳይ ጥጆች እንዲኖሩ በማድረግ በአርሶ አደሩ ቤት ከፍተኛ ወተት እንዲያገኙ ታሳባ ተደርጎ በንቅናቄ እየተመራ መሆኑን አመላክቷል።

በአምና ደረጃ 1ሺ 2መቶ 24 ተዳቅለው 5መቶ 25 ጥጃ የተገኙ ሲሆን ዘንድሮ ደግሞ 2ሺ150 በመደበኛ ለማዳቀል እቅድ ተይዟል ነው ያሉት።

በአጠቃላይ በወረዳው በአሁን ሰአት 1መቶ 5ሺ 821 ዝርያቸው የተሻሻሉ ከብቶች እንዳሉ አሳውቀዋል።

በመደበኛ ማዳቀል፣ ሲንክሮናይዜሽን፣ የተሻሻሉ ኮርማዎች በማዳቀል ስራ የሚሰራ መሆኑን ጠቁመው በወረዳው አርሶ አደሩ ዝርያ ማሻሻል ላይ ገና ሚፈለገው አክል ውጤት አልመጣም ብለዋል።

የጉራጌ ዞን ግብርና መምሪያ የእንስሳት ዓሳ ሀብት ልማት የእንስሳት ጤና ጥበቃ ስራ ሂደት አስተባባሪ ዶክተር ኸይሩ እንዳሉት በዚህ ዞናዊ የስንክሮናይዜሽን ዘመቻ በጥንቃቄ መሰራት ያለበት ስራ መሆኑን አሳውቀው በዚህም የጤና ቡድን፣ የአዳቃዬች ቡድንና የእርባታ ባለሙያዎች ቡድን ከፊት አመራሮች ጋር በጋራ በመሆን በቅንጅት እየተሰራ እንደሆነ ገልጿል።

የእዣ ወረዳ እንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ጽ/ቤት አዳቃይ ባለሙያ አቶ ብዙነህ ጎይታቤ እንደገለጹት መጀመሪያ አርሶ አደሩ ለቴክኖሎጂ ቅርብ እንዲሆን ግንዛቤ እየተፈጠረለት እንዳለና ሞዴል አርሶ አደሮች ወተት ለከተሞች እያቀረቡ ተጠቃሚ እየሆኑ ይገኛሉ ብለዋል።

ምርትና ምርታማነትን ሲታሰብ የመኖ አጠቃቀም እና የጤንነት ሁኔታ ወሳኝነት ያላቸው ሲሆን ይህም ስራ በትኩረት እየተሰራበት እንደሆነ አመላክቷል።

የእዣ ወረዳ የዝርያ ማሻሻል ባለሙያ አቶ እልልታ ሹሙ በዚህ ወቅት እንዳሉት እንስሳቶች የጤና እክል ሲገጥማቸውና የኮርማ ፍላጎት ሲያሳዩ በፍጥነት ወደ አርሶ አደሮቹ ቤት በመድረስ አስፈላጊ የሆነ ሙያዊ ህክምና እንደሚሰጡዋቸው ተናግሯል ።

በአለም ደረጃ በወተት ምርት የሚታወቁ እንደ ሆለስቲያም እና ጀርሲም በአማካኝ ከ12 በላይ ሊትር ወተት የሚታለቡ በመሆኑ የአርሶ አደሩ ኑሮ እንደሚቀይሩ ግንዛቤ በመስጠት ስራው ተግባራዊ እየሆነ እንደሆነ አሳውቀዋል።

አርሶ አደር ሀያቱ መሀመድ አርሶ አደር ወ/ሮ ሽቱ ደንድር እና አለም ሟነንዴ በእዣ ወረዳ ዝርያቸው የተሻሻሉ ከብቶች የሚያረቡ አርሶ አደሮች ናቸው።ባህላዊ የከብት እርባታና ዝርያቸው የተሻሻሉ ከብቶች ማርባት ከፍተኛ ልዩነት መኖሩ አመላክተው ለአብነትም በባህላዊ ከብቶች 1ሊትር ወተት ብቻ የገኙ የነበረው በዘመናዊ ደግሞ እንደ አመጋገቡ ከአምስት ሊትር በላይ ወተት እንደሚያገኙ ተናግረዋል

የባለሙያዎች ምክር በመስማትና እንዲሁም በሚደረግላቸው ጥብቅ ክትትል ዝርያቸው የተሻሻሉ ከብቶች እየበዙ በመሆኑ ከፍተኛ ወተተት ይገኛል። አክለውም ከፍተኛ ወተት ባገኘን ቁጥር የኢኮኖሚ አቅማችንም እንድናሳድግ እረድቶናል ብለዋል።

አስተያየት ሰጪዎቹ አክለውም በከተማ ሱቅ የመክፈት፣ ልጆቻቸው የማስተማር፣ መኖርያ ቤት የመስራት ስራ እንድናከናው መነሻው ዝርያ ማሻሻሉ ላይ በመስራታችን ነው ብለው የበለጠም ለመስራት የፉርሽካ አቅርቦት እንዲመቻችላቸው ጠይቀዋ ሲል የዘገበው የጉራጌ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው።

በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *