ህዳር 29/2014
ከውጭ ሀገር በከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ የሚገባው የስንዴ ምርት በሀገር ውስጥ ምርት ለመተካት የበጋ ስንዴ መስኖ ስራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የደቡብ ግብርና ምርምር ማዕከል ገለጸ።

በጉራጌ ዞን ምስራቅ መስቃን ወረዳ የበጋ የስንዴ መስኖ ስራ መጀመሩን ተመልክቷል።

የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሐመድ ጀማል እንደተናገሩት ሀገሪቱ የገጠማት የውስጥና የውጭ ጠላት በኢኮኖሚው ዘርፍ የሚያሳድረው ጫና ለመመከት የበጋ ስንዴ መስኖ ስራ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት።

በህልውና ጦርነቱ ምክንያት የተፈጠረው የስንዴ ምርት እጥረት ችግር ለመቅረፍ መንግስት ለአርሶ አደሩ የስንዴ ዘር እና ሌሎች ግብዓት በማቅረብ ውጤታማ ተግባራት እያከናወነ ይገኛል ብለዋል።

እንደ ዋና አስተዳዳሪው ገለጻ የዞኑ አርሶ አደሮች በአመት ሶስት ጊዜ የማምረት አቅማቸውን በማጎልበት የምግብ በተለይም ስንዴ በስፋት በማምረት ወደ ገበያ በማቅረብ የህብረተሰቡ የምግብ ፍጆታ በራስ ለመሸፈን በትኩረት እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል።

በዞኑ ከ2 ሺህ አንድ መቶ ሄክታር በላይ መሬት በበጋ ስንዴ መስኖ ለማልማት እየተሰራ መሆኑንም ዋና አስተዳዳሪው አክለው ገልጸዋል።

የደቡብ ግብርና ምርምር ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱልሃሚድ ጀማል የተለያዩ የውሃ አማራጮች በመጠቀም የበጋ ወቅት የስንዴ መስኖ ስራ ውጤታማ ለማድረግ እየተሰራ ነው ብለዋል።

እንደ ዳይሬክተሩ ገለጻ ለሁሉም ዞኖች በቂ የስንዴ ዘር፣ የአፈር ማዳበሪያና የጀነሬተር ድጋፍ የተደረገላቸው በመሆኑ ያላቸውን አቅም ተጠቅመው መስራት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።

የበጋ ስንዴ መስኖ ስራ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ የበልግ ወቅት ስራ እንዲጀመር አርሶ አደሩ ጊዜውን በአግባቡ መጠቀም እንዳለበትም አመላክተዋል።

እንደ ዶ/ር አብዱልሃሚድ ገለጻ አሸባሪው የህወኀት ቡድን በከፈተው ጦርነት ምክንያት የተከሰተው የስንዴ ምርት አቅርቦት ችግር ለመቅረፍ የበጋ ስንዴ መስኖ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል።

ሀገሪቱ ከውጭ ሀገር በከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ የሚገባው የስንዴ ምርት በሀገር ውስጥ ምርት በመተካት ከፍጆታ ባለፈ ለገበያ በማቅረብ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸው ያሳድግላቸዋል ብለዋል።

አብዛኛው የሀገሪቱ ዜጎች ለምግብነት የሚጠቀሙት የስንዴ ምርት በመሆኑ ተፈላጊነቱ እየጨመረ በመምጣቱ በ2014 ዓ.ም እስካሁን መንግስት 4 መቶ ሺህ ኩንታል የስንዴ ምርት በከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ግዢ ፈጽሞ ማስገባቱን አስረድተዋል።

አያይዘውም ሀገሪቱ በስንዴ ምርት ራሷን እንድትችል ለማድረግ እና የውጭ ምንዛሬ ጫና ለመቀነስ ስለሚያስችል አርሶ አደሩ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ሊሰራ እንደሚገባ አሳስበዋል።

የምስራቅ መስቃን ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሻፊ ሁሴን በበኩላቸው በሀገሪቱ የምግብ ክፍተት እንዳይፈጠር እየተሰራ ሲሆን ከመደበኛ የመስኖ ስራ በተጨማሪ በዚህ የበጋ ስንዴ መስኖ 170 ሄክታር መሬት እንደሚሸፈን ገልጸዋል። በዚህም ከ7 ሺህ ኩንታል በላይ ምርት እንደሚሰበሰብ በመግለጽ።

በበጋ ስንዴ መስኖ የተሰማሩ አርሶ አደሮች በሰጡት አስተያየት ጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት የሀገሪቱ ህልውና ወደ ግንባር የዘመቱ ሲሆን አርሶ አደሮቹ ደግሞ በመስኖ ልማት በመሰማራት ድህነትና ረሃብ ለማሸነፍ በቁርጠኝነት እየሰሩ መሆናቸውን ገልፀዋል።

አርሶ አደሮቹ አክለውም የምግብ ዋስትና ችግር ለመቅረፍና በምግብ ራስን ለመቻል መንግስት እያደረገላቸው ያለው ድጋፍ አበረታች ሲሆን የበጋ ስንዴ መስኖ ውጤታማ ለማድረግና ይበልጥ ተጠቃሚ ለመሆን እንደሚሰሩ አብራርተዋል።

ድህነትና የውጭ ጣልቃ ገብነት በቃ በማለት በግብርናው ዘርፍ ድል ለመቀዳጀት እንሰራለን ማለታቸውን የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ዘግቧል።

  • አካባቢህን ጠብቅ!
  • ወደ ግንባር ዝመት!
  • መከላከያን ደግፍ!

በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36Cx

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *