ፍትሃዊ የንግድ አሰራርና ዘመናዊ የግብይት ሥርአትን በመዘርጋትና መልካም አስተዳደርን በማስፈን የንግዱ ማህበረሰብና ሸማቹን ህብረተሰብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሁሉም ባለ ድርሻ አካላት ተሳትፎ እንደሚጠይቅ ተገለፀ።

ሰራርና ዘመናዊ የግብይት ሥርአትን በመዘርጋትና መልካም አስተዳደርን በማስፈን የንግዱ ማህበረሰብና ሸማቹን ህብረተሰብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሁሉም ባለ ድርሻ አካላት ተሳትፎ እንደሚ

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ንግድና ገበያ ልማት ጽህፈት ቤት ከባለድርሻ አካላትና ከንግዱ ማህበረሰብ ጋር ባጋጠሙ ችግሮችና በንግድ ማዕቀፎች ላይ ውይይት አደረገ።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ንግድና ገበያ ልማት ጽህፈት ቤት ሃላፊና የወልቂጤ ከተማ ምክትል ከንቲባ የሆኑት ወይዘሮ አሊማ ዲጋ እንደገለፁት ህገወጥ የንግድ ስርአትን ለመከላከል የሁሉም አካላት ጥረት እንደሚያስፈልግ ገልጸው።

የተለያዩ መድረኮች ተፈጥረው ውይይቶች ቢደረጉ ምህገ-ወጥነት ህጋዊ እስኪመስል ድረስ የተስፋፋበት ሁኔታ ይታያል።

በመሆኑም የመድረኩ አስፈላጊነት ህግን እያወቁ ህግን በሚተላለፉ ነጋዴዎች ላይ በተቀመጠው አዋጅ መሠረት እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን ለማሳወቅ ሲሆን ባለማወቅ ህግን ለሚተላለፉ ነጋዴዎች ግንዛቤ ለመፍጠርና በአዋጁ ላይ የተቀመጠው መመሪያ ለማስገንዘብ ታስቦ የተዘጋጀ መድረክ መሆኑን ገልጸዋል።

ከደረሰኝ ጋር ተያይዞ ማንኛውም ነጋዴ ለሸጠው እቃ ደረሰኝ የመስጠት ግዴታ እንዳለበት ሁሉ ገዢውም ለገዛው እቃ ደረሰኝ የመቀበል መብት እንዳለው ሃላፊዋ ተናግረዋል።

የጉራጌ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ሃላፊ አቶ መላኩ ብርሃኔ እንደገለፁት መመሪያው ከዚህ በፊት የነበረ ቢሆንም መወያየቱ የሚጠቅም መሆኑ ሥለታመነበትና ህግን ያለማክበር ሁኔታ እየሰፋ ስለመጣና እንዲሁም የከተማችን የንግዱ ማህበረሰብ የእርምጃ አወሳሰዱን ሁኔታ ሳያውቅ ችግር ውስጥ እንዳይገባ ለማድረግ እንደሆነ ገልፀው።

በየእለቱ እየተስፋፋ የመጣውን ህገ-ወጥ የመንገድ ዳር ንግድን አስመልክቶ ከዚህ በኃላ የተቀመጠውን ህግና ደንብ አክብሮ በማይገኘ ነጋዴ ላይ በአዋጁ መሠረት እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን አቶ መላኩ ገልጸዋል።

ከተሳታፊዎች የተነሱ አስተያየቶች እንደ ከተማችን ህገ-ወጥ የመንገድ ዳር እንግዶችን በተመለከተ እልባት ያልተገኘለት ጉዳይ በመሆኑ ሁሉም ባለድርሻ ተረባርቦ መፍትሔ ሊሰጠው ይገባል ሲሉ ገልጸዋል።

ህገ-ወጥ የመንገድ ዳር እንግዶችን በመበራከታቸው ህጋዊ ሆኖ ለሚሰራው ነጋዴ ከፍተኛ ፈተና የሆነ በመሆኑ በጉዳዩ ላይ ህጋዊ እርምጃ ሊወሰድ ይገባልም ብለዋል።

ወደ እርምጃ ከመገባቱ በፊት ነጋዴውን ሰብስቦ ማወያየቱ የሚበረታታ ሲሆን ህገወጥነትን ለመከላከል መተጋገዝ አስፈላጊ ነው።

ህገ-ወጥ የነዳጅ ንግዶችን በተመለከተ የሚመለከተው አካል ዝምታን ከመምረጥ ይልቅ በንግድ ማዕቀፋ ዙሪያ የሚወጡ ደንብና መመሪያዎችን በቅርበትና በፍጥነት ከነጋዴው ጋር በመገናኘት የመወያየት ስራ ሊሰራ ይገባል።

የነዳጅ አቅርቦትና ፍላጎትን በተመለከተ እንደከተማችን ያለመመጣጠን ችግር በመኖሩ ህገወጥ የነዳጅ ሽያጭ እንዲበራከት አድርጎታል።

ህገወጥነት የሚመጣው የንግድ ስርአትንና ደንብን ባለማወቅ ስለሆነ ውይይቱን ክፍለከተማ ድረስ በማውረድ የነጋዴው ማህበረሰብ እንዲያውቅ ቢደረግ ለውጥ ሊመጣ እንደሚችል ተሳታፊዎች ጠቁመዋል።

ከተሳታፊዎች ለቀረቡ ጥያቄዎች ከመድረክ ሰፊ ማብራሪያና ምላሽ ተሰጥቶበት መድረኩ ተጠናቋል።
መረጃው የወልቂጤ ከተማ ኮሚዩኒኬሽን ነው።

Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub:- https://youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN36CxQ
Tiwter https://4pvf.short.gy/bTJNNn

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *