ፍርድ ቤቱ በ1ኛ ተከሳሽ መሳይ ኢተሳ 23 ዓመት ፣ በ2ኛ ተከሳሽ ረድኤት በላቸዉ በ19 ዓመት እንዲሁም በ3ኛ ተከሳሽ ያቦነህ ፍቅሬ በ19 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ዉሳኔ አስተላልፎባቸዋል።

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ.የወንጀል ህግ አንቀጽ 32(1) እና አንቀፅ 590(2) (ሠ) ስር የተደነገገውን በመተላለፍ የወንጀሉ ዝርዝር 1ኛ ተከሳሽ በምሁርና አክሊል ወረዳ የኮብልስቶን ንጣፍ ስራ በኮንትራት ወስዶ በመስራት ላይ እያለ የሰራውን ቁጥጥር የሚያደርገው የፕላን ኮሚሽን መስሪያ ቤት ባለሙያ ከሆነው አቶ አሰፋ ተስፋዬ ጋር የስራ ጥራት እና የክፍያ አፈፃፀምን በተመለከተ አለመግባባት በመፈጠሩ በ2015 ዓ.ም በተለያየ ጊዜ ልጁን አግትበታለሁ እያለ ሲዘት ቆይቶ በሚያዚያ 21 ቀን 2015 ዓ.ም በግምት ከቀኑ 9፡00 ሰዓት በሚሆንበት ጊዜ የግል ተበዳይ ህጻን ጠልፈዉ መዉሰዳቸዉ መዝገቡ ያስረዳል።

በጉራጌ ዞን ምሁርና አክሊል ወረዳ ሰላም ሰፈር እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የ4 ዓመት ህጻን የሆነውን የግል ተበዳይ ህፃን ባህራን አሰፋ የመኖሪያ ቤታቸው አካባቢ ከሌሎች
ህፃናት ጋር እየተጫወተ እያለ 2ተኛ ተከሳሽ አባብላዉ ወደ ቤቷ በማስገባት 3ተኛ ወስዶ ለ1ኛ ተከሳሽ አቀብለዋል።

ህጻኑን ሰርቀው(ጠልፈው) የወሰዱት በመሆኑ በፈፀሙት በዋና ወንጀል አድራጊነት ለአካለ መጠን ያልደረሰን
ልጅ በመጥለፍ በወንጀል ተከሰዋል።

በዚህ መሰረት ፍርድ ቤቱ 1ኛ ተከሳሽ እጁ ከተያዘበት ጊዜ ጀምሮ በሚታሰብ በ23 አመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል እንዲሁም 2ኛ እና 3ኛ ተከሳሾች እጃቸዉ ከተያዘበት በሚታሰብ እያንዳዳቸዉ በ19 ዓመት ጽኑ እስራት ተቅጥተዋል።

ፍርድ ቤቱ በትናንትናው እለት በዋለዉ ችሎት በሶስቱም ተከሳሾች ላይ የቅጣት ዉሳኔ አስተላልፏል ሲል የዘገበዉ የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን መምሪያ ነዉ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *