ፈጣንና ቀጣይነት ያለዉ የኢኮኖሚ እድገት ለማስመዝገብ በየአካባቢዉ ኢኮኖሚዉ ያመነጨዉን ሀብት አሟጦ በመሰብሰብና በተገቢዉ ለልማት እንዲዉል ለማድረግ ባለድርሻ አካላት በትኩረት መስራት እንዳለባቸዉ ተገለጸ።

መየጉራጌ ዞን ገቢዎች መምሪያ የ2015 ዓ.ም የደረጃ “ሐ” ግብር ከፋዬች የዕለት ሽያጭ ገቢ ግመታ የማስፈጸሚያ ዕቅድ ላይ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በወልቂጤ ከተማ የምክክር መድረክ ተካሄዷል።

ፍትሃዊ የእለት ሽያጭ ግመታ በማካሄድ በዘርፉ የሚፈለገዉን ዉጤት ለማምጣት ባለድርሻ አካላቶች ከመቼዉም ጊዜ በላይ በቅንጅት መስራት ይኖርባቸዋል።

የጉራጌ ዞን ገቢዎች መምሪያ ኃላፊ አቶ ሙራድ ረሻድ መድረኩን በንግግር በከፈቱበት ወቅት እንዳሉት የታክስ ገቢ የህዝቡ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መሰረተ ልማት ፍላጎቶች ደረጃ በደረጃ ምላሽ ለመስጠትና የተረጋጋ ኢኮኖሚ በማስፈን ስራ አጥነትና የዋጋ ግሽበትን ለመከላከል፣ የሀብት ክፍፍል ፍትሃዊ ለማድረግ ፣ኢንቨስትመንት ለማበረታታተና ልማትን ለማፋጠን የሚጫወተዉ ሚና ከፍተኛ ነዉ ብለዋል።

ፈጣንና ቀጣይነት ያለዉ የኢኮኖሚ እድገት ለማስመዝገብ በየአካባቢዉ ኢኮኖሚዉ ያመነጨዉን ሀብት አሟጦ በመሰብሰብና በተገቢዉ ለልማት እንዲዉል ለማድረግ ባለድርሻ አካላት በትኩረት መስራት እንዳለባቸዉም ተናግረዋል።

የደረጃ ‘ ሐ’ ግብር ከፋዮች የእለት ሽያጭ ገቢ ግመታ ባለፉት ስድስት አመታት በክልሉ ባሉ አጠቃላይ ንባራዊ ሁኔታ ምክንያት በየሶስት አመቱ መካሄድ የነበረበትን የእለት ሽያጭ ግመታዉ ሳይካሄድ ቆይቷል ብለዋል።

ይሁንና ለታክስ አሰባሰብ ችግር እየፈጠረ እንደሆነና በዘንድሮ አመት ከ2015 እስከ 2017 ስራ ላይ የሚዉል የደረጃ ‘ሐ’ ግብር ከፋዮች የእለት ሽያጭ ግመታ ስራ የሚሰራ ሲሆን ለዚህም ስኬት ከሁሉም ወረዳዎች እና ከተማ አስተዳድሮች ጋር ዞን አቀፍ የምክክር መድረክ በማካሄድ በዘርፉ የታቀደዉን ገቢ ለመሰብሰብ በትኩረት እንደሚሰራም ጠቁመዋል።

የምክክር መድረኩ በየወረዳዉና ከተማ አስተዳድሮች ከነገ ጀምሮ የሚካሄድ እንደሆነም የተናገሩት አቶ ሙራድ የእለት ሽያጭ ግመታ ኮሚቴዎች በክልል ደረጃ ስልጠና እንደሚሰጣቸዉም አብራርተዋል።

ይህም ስልጠና በዋናነት የእለት ሽያጭ ግመታዉ ፍትሃዊ እንዲሆን እንዲሁም ማጭበርበር እንዳይኖርና አጠቃላይ ስራዉን በብቃት እንዲወጡ ያደርጋቸዋል ብለዋል።

የአሰራር ፣ የአደረጃጀት እና የህግ ማዕቀፍ ማሻሻያዎችን ተግባራዊ በማድረግ በአገልግሎት አሰጣጥ እንዲሁም በታክስ ፍትሀዊነት ላይ ይነሱ የነበሩ ቅሬታዎች ደረጃ በደረጃ እየቀነሱ እንዲመጡ ማድረግ የተቻለ ከመሆኑም ገቢ የመሰብሰብ አቀማቸዉም ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱም አመላክተዋል።

በመድረኩ የተገኙት የጉራጌ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ዋና አቶ መሰለ ጫካ እንዳሉት ግብር በአግባቡና በወቅቱ መክፈል የእድገትና የስልጣኔ መሰረት ሲሆን በየደረጃዉ ህዝቡ የሚያነሳቸዉ የልማት ጥያቄዎች ለመመለስ ግብር በወቅቱ መሰብሰብ እንደሚገባም አሳስበዋል።

የግብር ከፋዩ ማህበረሰብ ግንዛቤ ማሳደግ ይገባል ብለዉ የዕለት ሽያጭ ግመታ ላይ ፍትሃዊ በሆነ መልኩ መሰረት እንዳለበትም አመላክተዋል።

የደረጃ ‘ ሐ ‘ የእለት ሽያጭ ግመታ የተካሄደዉ በ2009 ዓመተ ምህረት መሆኑም ተናግረዉ ግመታዉ የሚካሄደዉ በየ ሶስት አመቱ ቢሆንም በተለያዩ ምክንያቶች ሳይካሄድ መቆየቱም አስታዉሰዋል።

አክለዉም ከዚህ በፊት በግመታ ወቅት የነበሩ ጉድለቶችን በማረም በቀጣይ ዉጤታማ ስራዎች መስራት እንደሚያስፈልግና የንግዱ ማህበረሰብም አስፈላጊዉን ትብብር ማድረግ እንዳለበትም ጠቁመዋል።

በመድረኩ የተገኙ አንዳንድ ባለድርሻ አካላት በሰጡት አስተያየት በንግዱ ማህበረሰብ ፍትሃዊ የዕለት ሽያጭ ግመታ በማካሄድ ዉጤታማ ስራ መሰራት አለበት ብለዋል።

ፍትሃዊነት ቁርጠኝነት ያለዉ አሰራር ስርአት በመዘርጋት የእለት ሽያጭ ግመታዉ በተገቢዉ ማከናወን ይገባል ብለዉ በግብር ከፋዩ ማህበረሰብ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮች ለመቅረፍ የአስተምሮቱ ስራ አጽኖት ተሰጥቶት በመሰራት በዘርፉ የሚፈለገዉን ዉጤት ለማምጣት በትኩረት እንደሚሰሩም ጠቅሰዋል ሲል የዘገበዉ የጉራጌ መንግስት ኮሚኒኬሽን መምሪያ ነዉ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *