ጧሪና ደጋፊ የሌላቸው የማህበረሰብ ክፍሎች ለመደገፍ የሁሉም እገዛ እንደሚያስፈልግ በጉራጌ ዞን የእኖር ወረዳ ወጣቶችና ስፓርት ጽ/ቤት ገለጸ።

ጧሪና ደጋፊ የሌላቸው አረጋውያንና አቅመ ደካሞች ለመደገፍ ባለሀብቱን ጨምሮ የሁሉም እገዛ እስፈላጊ መሆኑን ተገልጿል፡፡

በዛሬው ዕለት በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በመተባበር በወረዳው ሁረድ ቀበሌ ከ5 ህፃናት ልጆቻቸውና በህመም ላይ ከሚገኙት ባለቤታቸው ጋር ከጎረቤት ተጠልለው ይኖሩ የነበሩት የወ/ሮ ወሊያ ዘርጋ መኖሪያ ቤት መገንባት ችለዋል።

የወረዳው ወጣቶችና ስፖርት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ቸሩ ተካ እንደተናገሩት በበጋው የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት የአካባቢ ወጣቶችና ባለሃብቶች በማስተባበር እንዲሁም የወረዳው መንግስት ድጋፍ በማድረግ እስካሁን ከ18 በላይ የሚሆኑ የአረጋውያንና አቅመ ደካሞች ቤት መገንባት መቻሉን ገልጸዋል፡፡

አያይዘውም በበጋው የወጣቶች በጎ ፍቃድ አገልግሎት የተገነቡ መኖሪያ ቤቶች በቅርቡ የበርና መስኮት መግጠምና የማስተካከል ስራ መከናወኑንም ጠቁመዋል፡፡

አቶ ቸሩ አክለውም በበጋ የወጣቶች በጎ ፋቃድ አገልግሎት የአቅመ ደካሞችን ቤት ከመገንባት ባለፈ በደም ልገሳ፣ በከተሞች ፅዳትና የዘማች ቤተሰቦችን በመደገፍ ረገድ አበረታች ተግባራት መከናወኑን ጨምረው ገልጸዋል።

የዛሬው ቤት ግንባታ እውን እንዲሆን የቆርቆሮ ድጋፍ ላደረጉት የወረዳው ተወላጅ ባለሃብት አቶ ሙሉጌታ ዘለቀ እንዲሁም የሚስማር ድጋፍ ላደረገው ወርልድ ቪዥን ኢትዮጲያ ጉንችሬ ቅርንጫፍ ሐላፊው አመስግነዋል።

በመጨረሻም ቤት የተሰራላቸው ወ/ሮ ወሊያ ዘርጋ እንደገለፁት ይኖሩበት የነበረውን መኖሪያ ቤት ሙሉ በሙሉ በመፍረሱ ምክንያት ከነቤተሰቦቻቸው ከጎረቤት ጋር ተጠግተው ይኖሩ እንደነበር ጠቁመው የቤት ባለቤት በመሆናቸው መደሰታቸውን ገልጸዋል፡፡

በመርሃ ግብሩ ላይ የወረዳው የመንግስት ተጠሪ አመራሮች፣ የወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት አመራሮችና ሰራተኞች፣ የሴቶችና ህፃናት ጽ/ቤት እንዲሁም የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳዮች ፅ/ቤት ሐላፊዎችና ባለሙያዎች ተገኝተዋል ሲል መረጃው ያደረሰን የወረዳው የመንግስት ኮምዮኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው።

በመረጃ ምንጭነት ገፃችን ምርጫዎ ስላደረጉ እናመሰግናለን!

= ኢትዮጵያን እናልማ!
= የፈረሰውን እንገንባ!
= ለፈተና እንዘጋጅ!
በተጨማሪም እነዚህ ሊንኮችን በመጫን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
Facebook:- https://www.facebook.com/gurage1Zone
Website:- https://gurage.gov.et
Telegram:- https://t.me/comminuca
Youtub: -https://www.youtube.com/channel/UCzrcazGvvIO2tG7bQN

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *